“ጅግና ይፈጠራል እንጂ አይወለድም” በ G9 ስብሰባ

ዋለልኝ መኮንን

ወንድሞቼ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስቴር መለሰ ዜናዊ በ21 አመት የአምባገነን የስልጣን እድሜቸው እንደዚህ ያለ ውርደት ሲገጥማቸው አይቼም ሰምቼም አላውቅም:: ከፍተኛ ግፍ:በደል:ጭቆናና ውርደት በሕዝቡ ላይ እያደረሱ ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ልክ እንደ ልማት ሰራተኛና ሰላም ወዳድ እራሳቸውን አስመስለው የኢትዮጵያንና የአለምን ማህበረሰብ በውሸት ሲያደነቁሩን ይሀው 21 አመት ሊሞላ ቀናቶች ቀራቸው::

ጠቅላይ ሚኒስቴሩ የስልጣን ዘመናቸው እየረዘመ በመጣ ቁጥር በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚፈፅሙት የወንጀል መጠንም በአይነቱም ሆነ በይዘቱ እጅግ እየጨመረ ይገኛል ጥቂቶቹን ብናስታውስ
-ህዝቦችን በዘር: በብሄር: በቋንቋ: በሀይማኖት: በቀለም: ብሎም በጎጥ እንዲለያዩ ማድረግና ክፍተኛ የጥላቻ ፖለቲካ ቅስቀሳ በህዝቡ ዘንድ ማሰረጨት::

-በርካታ የህዝብን ተፈጥሮዊና ህገመንግስታዊ መብቶችን፧የመናገር:የመፃፍ:የመሰብሰብ:በቡድን የመደራጀት:ሀሳብን በአደባባይ ወጥቶ የምግለፅ: በሀገሩ ላይ የመሬት ባለቤት መሆን: የፈለገውን እምነት መከተልና የመሳሰሉትን በኢትዮጵያ ተፈፃሚ እንዳይሆኑ ማድረግ::

-የተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎችን: አባላቶችን: ደጋፊዎችን: ምሁሮችን: መምህራኖችን: ጋዜጠኞችን: ዘፋኞችን: ነፃ አሳቢ ዜጎችንና በተለያዩ የዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ላይ የሚሳተፉ ግለሰቦችን ማስፈራራት:በእስር ማሰቃየት: በአካላቸውና በስነልቦናቸው ላይ ጉዳት ማድረስ:ንብረታቸውን መውረስ መዝረፍ ማውደም: አስፈራርቶ ከሀገር እንዲሰደዱ ማድርግ: የት እንደደረሱ እንዳይታወቅ ማድረግ: መግደልና ሌሎችንም የመሳሰሉ ወንጀሎችን በመፈፅም ሀገር የማፈራረስ ህዝብንና ሀገርን የማዋረድና የባንዳነት ተልኮውን መወጣት::

-ስለ ሰባዊ መብት መልካም አስተዳደር የህግ የበላይነትን ለህዝቡ በማስተማርና በማስረፅ ላይ የተሰማሩትን መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች: ነፃ ጋዜጦች: የራዲዮና የቴሌ ፕሮግራሞችን ሆን ብሎ የተለያዩ አፋኝና ሰንካላ ሰላማዊዮቹንና የብዙሀኑን መብት የሚያቀጭጩ የሌቦችንና የጥቂቶችን ቡድኖችን ስልጣን የሚያፋፋ ህጎችንና መመሪያዎችን አውጥቶ ለህዝቡ እንዳይደርሱ ማድርግ:: ህዝቡም መብቶቹን እንዳያውቅና እንዳይጠቅም ማድረግ::

-የኢትዮጵያን ህዝብ የሀገር የመሬትና የንብረት አልባ አድርጎ የወያኔ አባላት ብቻ የመሬትና የንብረት ባለቤት እንዲሆኑ ማድርግ:: ሀገርንና መሬትን ለባእዳን መሸጥና ለጎረቤት ሀገሮችም ትላልቅ መሬቶችን ቆርሶ በመስጥትን በመሸጥ አሳልፎ መስጠት::

-በብሄርና በጎጥ የተደራጁ ጥቂት የወያኔ ማፊያዎች የሌብነት ተግባራቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ለማስፈፅም ወንበዴ ዘራፊ ድርጅት ማቋቋምና ህዝቡንና ሀገሪቱን መዝረፍ: ማደህየት: ማስራብ: የበዪ ተመልካች ማድረግ::

-የኢትዮጵያ ህዝብ ትክክለኛ እውነተኛና ሚዛናዊ መረጃዎችን እንዳያገኝና በኢኮኖሚ: በማህበራዊ: በፖለቲካ: በዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ እንዳይሆን ማድረግ:: እኔ አውቅልሀለው የምነግርህን ብቻ ተቀበል ብሎ ህዝብን በወያኔ የመረጃ ማሰራጫዎቹ ማደንቆር:: ትክክለኛ እውነተኛና ሚዛናዊ መረጃዎችን ለህዝቡ የሚያደርሱትን የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የመረጃ ተቃማትን የግል ጋዜጣዎችን ራዲዮዎች ቴሌቪዥን እና ድህረ ገዕች መረጃዎችን ለህዝቡ እንዳያደርሱ ለማድረግ አታሚ ድርጅቶችን መዝጋት: ፈቃድ መከልከል: ባለቤቶቹን ማስፈራራት: ማሰር: ከሀገር እንዲሰደዱ ማድረግ:: በራዲዮና የቴሌቢጅን የሚሰራጩትን መረጃዎች ከፍተኛ ገንዘብ በማውጥት ሞገዳቸውን ማፈን::

እንግዴ እነዚህን ሁሉ ወንጀልና ውሸት የያዘችው እንስራ ሞልታ መፍሰስ ከጀመረች ዘገየች ነገር ግን ልክ እንደ ሌሎቹ የአፍሪካ መሪዎች ጠቅላይ ሚንስትሩም መማር አልፈለጉም ነበርና አንደኛ ደረጃ የውርደት ካባ በ May 18 2012 የG-9(አንዱ አበበ ገላው ነበረ) ስብሰባ ተሸልመዋል:: ጠቅላይ ሚንስትሩ እንደዚ አይነት ውርደት ይገጥመኛል ብለው እስበው ስልማያውቁ ሲደነግጡና አንገታቸውን ሲደፉ ታይተዋል:: ምክንያቱም ጠቅላይ ሚንስትሩ እንደዚ አይነት ደፋር ኢትዮጵያዊ እንዳይኖር ለማድረግ ላለፉት 21 አመታት ያልፈነቀሉት ድንጋይ ያላፈሰሱት መዋለንዋይ ያላንኩዋኩት በር ያልቆፈሩት ጉድጋድ የለም ነገር ግን የተጨቆነን የህዝብ ድምፅ ማስቆም የሚችል ሰዋዊ ፍጥረት እንደሌለ ስለማያውቁ ለማፈን እንሞክራለን ብለው በተደጋጋሚ የውርደት ካባ እየተሸለሙ ይገኛሉ

በአሁን ሰአት ጠቅላይ ሚንስትሩ አስራ አንደኛ ሰአት ላይ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ ህዝብ ባገኝው አጋጣሚ ሁሉ ሲነግራቸው ቆይቶአል አሁንም ባገኝው አጋጣሚ እየነገራቸው ይገኛል ::ትላንትናም አቶ አበበ ገላው በአለም አቀፉ የ G9 (አንዱ አበበ ገላው ነበረ) ስብሰባ ላይ የተናገሩት በአንድ በኩል የኢትዮጵያ ህዝብ ምን ያህል በአምባገነኖች ቀንበር ስር እንዳሉ ሲሆን በሌላ በኩል የአለም አቀፍ እርዳታ ለጋሽ አገሮች የአምባገነኖችን በዜጎቻቸው ላይ የሚፈፅሙትን ኢሰብአዊና ኢፍታዊ ድርጊቶችና ወንጀሎች መሸፋፈናቸው አስፈላጊ አለመሆኑን ነበር:: በጣም የሚያሳዝነው ግን በህዝብ ትግል ተሸንፈው ተዋርደውና ተጎትተው ከወንበራቸው እንደተጣሉት እንደ ብዙዎች የአፍሪካ መሪዎች የህዝብን የፍትህ የኩልነትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ቸል ማለት አለማድመጥ ይባስ ብሎም አሸባሪ በማለት ህዝብን ሰላማዊ ዜጎችን ፤ለነፃነታቸው የሚታገሉትን ግለሰቦችና ቡድኖች፤ ስለ ነፃነት ፍትህና እኩልነት የሚፅፉትንና የሚያዜሙትን በአሸባሪነት እየተፈረጁ ለተለያዩ ስቃዮችና እንግልቶች መዳረግ የተለመደ ተግባራቸው ነው::

በኢሀዲግ ፓርላማ ብርቅዬው የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካይ የተናገሩትን( በሁዋላ አልሰማንም አላየንም የለም ተናግረናል) ንግግር ጠቅላይ ሚንስትሩ በደንብ ደጋግመው ሊያጤኑት ይገባ ነበረ ግን ልክ እንደ ሙሃመድ ጋዳፊና ሌሎችም የአፍሪካ መሪዎች በስድብና በንቀት አለፉት አሁን ግን ጌቶቻቸው ፊት ነው የማስጠንቀቂያ ደውል እንዲሰሙ የተደረጉት አሁንም ካልተማሩ …………..