የወያኔ በሃይማኖት ጣልቃ ገብነትና አሞራዎች ጅግራ ሆነው መታየት ቀጥለዋል
ዋለልኝ መኮንን
የወያኔ መንግስት ለስሙ ሀይማኖትና መንግስት ጣልቃ አይገባቡም እያለ ጆሮችንን በየቀኑ ያደነቁረናል ነገር ግን በኦርቶዶክስና በእስልምና እምነት ድርጅቶች ውስጥ በቀጥታ እጁን አስገብቶ በመጀመሪያ ለዘመናት ተቻችለውና ተከባብርው የኖሩትን ከላይ የተጠቀሱትን የሁለቱን እምነቶች ተከታዮችን ጣልቃ በመግባት እርስ በርሱ እንዲተላለቁ ለማድረግ ብዙ ስራዎች ተሰርተው ነበረ ነገር ግን ህብረተሰቡ ይህ ተግባር የወያኔ አኩይ ስራ እንደነበረ ስለተረዳ በትዝብት ተመልክቶታል:: በሁለተኛ ደረጃ ወያኔ በእምነቶች ውስጥ ጣልቃ መግባቱ ገሀድ የወጣበት በኦርቶዶክስ እምነት ውስጥ የሚገኙትን ከፍተኛ የስልጣን ቦታዎችን የፈጣሪን የሚመለክባቸው ሳይሆን የወያኔን ጥቅም ለሚያስከብሩ ከአንድ ብሄር ለተሰበሰቡ ግለሰቦች አስረከበ::
የሰሞኑ የወያኔ ትልቅ ቅሌት ደግሞ በእስልምናም እምነት ውስጥ እያደረገ ያለው ድራማ ነው:: አዲስ የእስልምና እምነት ከውጭ እንዳስመጣ በጉልበትም ካልተቀበላቹ እያለ እያስፈራራ አያሰረ እየገደለ እንደሆነ እያየን ነው:: አንቀበልም ያሉት ደግሞ አሸባሪ እየተባሉ ነው:: የኢትዮጵያ ህዝብ በተደጋጋሚ መንግስት እጁን ከእምነቶቻቸው እንዲያወጣ ከፍተኛ ግፊት እያደረጉ ቢቆይም ይባስ ብሎ ሰሞኑን የወያኔ ዛር የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ እምንት ነፃነት ጥያቄ የሚያነሱትን ህዝቦች ፅረ ሰላም ፅረ ልማት ፅረ ዲሞክራሲና ፖለቲካ እንደ ወንጀል ተቆጥሮ የፖለቲካ አጀንዳ ያላችው ጥቂት ግለሰቦች ናቸው በማለት የመላው ኢትዮጵያን ህዝብ ጥያቄ በትእቢትና በንቀት ሲያጣጥሉት አይተናል::
ከትላንት በስቲያ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ለወያኔ ፓርላማ እንደተናገሩት ህዝቡ ስልክ ፌስቡክና የመሳሰሉትን የመገናኛ ቴክኖሎጂዎች አመፅና ሽብር ለማስነሳት እየተጠቀሙባቸው ነው ሲሉ ተደምጠዋል (ሊበሉዋት የፈለጉዋትን አሞራ ጅግራ ነች ይሉታል ይሄ ነው):: የዚህ ንግግር መልክት በቅርብ ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያ ህዝብ የነዚ,ለስሙ የኢትዮጵያ ህዝብ ንብረት የተባሉት የመገናኛ አውታሮች ቲቪ፣ ሬድዮ፣ ስልክ፣ኢንተርኔት የመገናኛ ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚ እንዳይሆን እንደሚደረግ በግልፅ ነግረውናል:: በ1997 ምርጫ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ብዙ የምርጫ ቅስቀሳዎችን በሞባይል መልዕክት አካሂድው ከፍተኛ የህዝብ ድምፅ አግኝተው ወያኔን አሸንፈው መንግስት ሌመሰርቱ ቢሞክሩም ወያኔ ስልጣን የጨበጥኩት በጠመንጃ ስለሆነ እናንተም በጠመንጃ ሞክሩ አላቸው:: ተቃዋሚዎቹን የመረጠውም ህዝብ ድምፄ ተሰረቀ ብሎ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ በሞባይል መልዕክትና በፌስቡክ በመጠቀም በአጭር ግዜ ውስጥ ተሰባስበዋል:: ነገር ግን ስልጣን ላይ ያለው መንግስት ወዲያውኑ የወሰደው እርምጃ የኢትዮጵያ ህዝብ ምንም አይነት መልዕክት በሞባይል መላላክ እንዳይችል ማድረግ ነበር::
ከዚህ በፊት እንዳየነውየሀገራችንም ሆነ የሌላው አገር አምባገነኖች የህዝብን ጥያቄ መመለስና ቁጣው ማብረድ ሲያቅታቸው እንደዚ ያሉ የመገናኛና የመረጃ ቴክኖሎጂዎችን ማፈንና እርስ በእርሱ መረጃ እንዳይለዋወጥ እድርጎ ትግሉን ማኮላሸት ነው:: እነዚህ የሀገርና የህዝብ ሀብቶች ህብረተሰቡን ማገልገል ሲገባቸው የስርዓቱ የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ከመሆን አልፈው ህዝብን ማስፈራሪያ የማፈኛ፣ የማሸበሪያ ከሆኑ ሰነበቱ::
የወያኔ መንግስት ህዝባዊ አመፅ የሚያስነሱ ናቸው በማለት በውሸት በተቀነባበረ ክስ በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሀን ዜጎች የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት አባላቶች ደጋፊዎች የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች በሰብአዊ መብትና በማህበረሰብ ልማት ላይ የተሰማሩትን መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የግል ጋዜጣ ባለቤቶችና አምደኞች በየእስር ቤቶቹ እያጎረ ነው። እነዚህ በየማጎሪያ ቤቶቹ የሚገኙትን እስረኞች ቁጥር በእጅጉ ከመጨመሩም በላይ ታስረው በሚገኙበት ቦታ የሚፈጸመው እንግልት እና ስቃይ እጅግ በጣም ተባብሷል::
አሁን የወያኔ አባላቶችና ደጋፊዎች የሚይዙትን የሚጨብጡትን ያጡበት ሰአት ላይ ይገኛሉ። ትልቁ ችግራቸው እስካሁን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያደረሱትን ወንጀሎች ኢተፈጥሮአዊና ኢሰብአዊ ድርጊቶች የሀገርና የህዝብ ሀብትና ንብረት ዘረፋ ብሎም የግለሰቦችን የብሄርንና የሀገርን ስምና ታሪክ ማጥፋትና ማበላሸትና የመሳሰሉ የውንብድና ተግባሮቻቸውን እንዴት ማጥፋት እንደሚችሉ የሚቻላቸውን ሁሉ ጥረት እያደረጉ ነው። ነገር ግን የሄ የመንግስት የሀይል እርምጃ ፉከራ ድንፋታ መደነባበር የህዝባችንን የፍትህ የእኩልነትና የነፃነት ትግል ማቆም አያስችለውም::