እኛ ኢትዮጵያውያን ለምንድነው ፍርሀትን የማንፈራው?
ዋለልኝ መኮንን
ወያኔ መንግስት የኢትዮጵያን ህዝብ አመኔታና ይሁንታ ሳያገኝ ላለፉት 21 አመታት አገርና ህዝብን በጠመንጃ ሀይል እያተራመሰና እየዘረፈ ቢቆይም በአሁኑ ሰአት ከወትሮው በተለየ መልኩ በህዝቡ ላይ የሚያደርሰው ኢስባዊና ኢፍታዊ ድርጊቶች ህዝቡ መሸከም ከሚያቅተው በላይ ስለደረሰበት የተለያዩ የፍትህ የኩልነትና የነፃነት ጠያቄዎች ከሁሉም አቅጠጫ ስላመጡበት በከፍተኛ ስጋት እና የመረበሽ መንፈስ ውስጥ ሆኖ ህዝቡን በርሀብ ፤ በማስፈራራት ፤ በእስር ፤ በስቃይ ፤ በስደት ፤ በግድያ፤ በእርስ በእርስ ግጭትና ሁከት እየፈጠረ በጠመንጃ አስገድዶ የባንዳነትና የሌብነት ተግባሩን እየፈፅመ ይገኛል::ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ አስፈራርቶና አጭበርብሮ በስልጣን ላይ ለመቆየት የሚጠቀምባቸው ብዙ ድብቅና ገሀድ የወጡ እስትራቴጂዎች አሉት::
ትልቁና ዋነኛው የወያኔ የማስፈራርያና የማጭበርበሪያ መሳሪያ ህዝቡን በመረጃ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ማስፈራራት፤ ውሸት የሆነውን የወያኔን የሁለት አሀዝ እድገትን በግድ እንዲዋጡለትና ማድረግና፤ ወያኔ ከስልጣን ከወረደ ኢትዮጵያ ዋጋ እንደሌላት እድርጎ የራሱን ስራዎችና ካድሬዎች ብቻ ቅዱስ አድርጎ ማቅረብ ዋነኛ የወያኔ ሬዲዮና ቴሌቢጅን ተግባራቸው ነው::በወያኔ የሚተዳደሩ ሁሉም የመገናኛ ብዙሃን ሙሉ በሙሉ በቀጥታም ሆን በተዘዋዋሪ የወያኔአዊ አመለካከትና የፓርቲ አቁም ማራመጃ እንጂ ታክስ እየከፈለ መገናኛ ብዙሃን ለገነባው ለኢትዮጵያ ህዝብ ጠቃሚ መረጃ ማሰማት ይቅርና ማስፈራሪያና ዛቻውንም በተወናበደና በተጭበረበረ መልኩ ብቻ ነው የሚያገኝው:: የኢህአዴግ መንግስት በሀገራችን የሚከሰቱ ማንኛውም ችግሮችንና የችግሮችን መንስኤ በወቅቱ ተረድቶ ስለችግሩ አግባብነት ያላቸውን መረጃዎች ለኢትዮጵያ ህዝብ ማቅረብ ባለመቻሉ ወይንም ህዝቡ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚከሰቱ ችግሮችንና የችግሮቹን መንስኤ ሆን ተብሎ እንዳያውቅና እንዳይሰማ ስንደረግ ወገኖቻችን ላይ የደረሱትን ችግሮችንና የችግሮቹን መንስኤ አስቀድመን የምንሰማው ከመንግስትና እሱ ከሚያስተዳድራቸው የመረጃ ተቃማት ሳይሆን ከሌሎች በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በፈጠሩቸው የመረጃ ተቀማት እና በአለም አቀፍ የመረጃ ምንጮች ነው፡፡
ሌላ የወያኔ የስልጣን እድሜ ማራዘሚያ ዘዴ የኢትዮጵያን ህዝብ በኢኮኖሚ የወያኔ ጥገኛ ማድረግ ነው::ወያኔ እየተከተለ ያለው የድህነት ማጥፋት ፖሊሲና እስትራቴጂ ላለፉት 21 አመታት ተጨባጭ የሆነ ለወጥ ማምጣት አልቻለም ለዚህም ውጤት አለመገኝት ዋነኛ መንስኤዎቹ የሀገሪታን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ ፖሊሲና እስትራቴጂ ፤ያስፈፃሚው አካላቶች የችሎታ ማነስ ፤ የህዝብ አሰራሮችን ከፓርቲ አሰራር ለይቶ አለማስኬድና፤ ስር የሰደደ ሙስና ናቸው፡፡ የኢትዮጰያ ማዕከላዊ ስታቲስቲክሰ ኤጀንሲ በ2003 ዓ.ም ባወጣው መረጃ መሰረት በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ ውስጥ በከተሞች ያለው የስራ አጥነት በመቶኛ 18 እንደሆነ ያሳያል፡፡ ድህነትም ከዛሬ አምስት አመት ከነበረበት 39% ወደ 29.6% ዝቅ እንዳለ የመንግስት መረጃዎች ያሳዩናል፡፡ እነዚህ ቁጥሮች አሁንም አገሪቱ ውስጥ አስከፊ ችግሮች እንዳሉ ቢያሳዩንም፤ ትልቁ ጥያቄ ግን እነዚህ መረጃዎች ምን ያህል ልክ ናቸው የሚለው ነው:: ምክንያቱም የወያኔ የዜናና የመረጃ ድርጅቶች የሜያወጡቸው አሀዞች ሀዝቡ በአይኑ ካየውና የአለም አቀፍ ድርጅቶች ክሚያወጡት እጅግ በጣም የሚራራቅ ነው፡፡ ሌላው ምክንያት የምዕራቡ አለም ወያኔ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በአመት 3 ቢሊዮን ዶላርና 400 ሺ ቶን የምግብ እህል እርዳታ ለኢትዮጵያ ይለግሳሉ:: እጅግ የሚገርመው የወያኔ ቅጥፈት የተሳሳተ የኢኮኖሚ ፖሊሲውና የራሱ ካድሬዎች የፈጠሩትን የኑሮ ውድነት በነጋዴው ህብረተሰብ ላይ ማላክኩ ሲሆን በጣም አሳፋሪው ቅጥፈት ደግሞ የባንክ ብድር እንደፈለጉና በርካሽ የሚወስዱትን ፤ ግብርና መዋጮ ከማይከፍሉትንና ፤ ገበያውን እንደፈለጉ የሚጨፍሩበትን የወያኔን የንግድ ድርጅቶችን እንደምክንያት አለመጥቀሱ ነው ።
ወያኔ ለለውጥ ዝግጁ አለመሆኑንና ኢትዮጵያ ውስጥ ስልጣን በህዝብ ድምፅ ሳይሆን በጠመንጃ አስፈራርቶና እርስ በእርስ አባልቶ ለመቆየት ያለውን አላማ በገሀድ አሳይቶናል:: ለምሳሌም በተለያየ በከፍተኛ የውሳኔ የሚሰጥባቸው የስልጣን ቦታዎች፤ ለሙስና የተጋለጡ መስሪያቤቶች፤ የህግ ክፍተት ያላቸውና፤ ብዙ የህዝብ ገንዘብ የሚንቀሳቀስበት ቦታዎች ላይ መቶ በመቶ በሚያስብል መልኩ በትግራይ ብሄር ተወላጆች ብቻ መያዙ እጅግ ትንሽ የሆኑ የከፍተኛ ስልጣን ቦታዎች በሌሎች የብሄር ተወላጆች ቢያዙም ከአሻንጉሊትነት የዘለለ የመወሰን ስልጣን የላቸውም:: ለምሳሌ በወያኔ መከላከያ ሠራዊቱ ውስጥ ያለው ከፍተኛ የአዛዥነት ቦታዎች ከሞላ ጎደል በትግራይ ተወላጆችና ለጥቂት ለሆዳቸው ባደሩና ታማኝ የሌሎች ብሄረሰብ ተወላጆች መያዙና የፌደራል ፓሊስን፤ የከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ ቴሌ ኮሙኒኬሽን ፤አየር መንገድ፤ በተለያዩ የታክስና የጉምሩክ ገንዘብ መሰበሰቢያ ቦታዎች ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ስልጣን በትግራይ ተወላጆች ከዘጠና በመቶ በላይ የተያዙ ናቸው::
ሙስና በኢትዮጵያ ታሪክ አሁን ያለበት ዘግናኝ ደረጃ ደርሶ አያውቅም:: ወያኔ እንከን የለሽ ብሎ እድሜልኩን የሚፎክርበት ነገር ግን ምንም ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ያቃተው የልማትና የእድገት ፖሊሲዎችና እስትራቴጂዎች ወያኔዎችንና ጥቂት ለሆዳቸው ያደሩትን አጫፋሪዎቻቸውን ቢሊየነርና ሚሊየነር የሚያደርጉ ሲሆን በተቃራኒው ደግሞ በመካከለኛና በድህነት የኑሮ ደረጃ ይኖር የነበረውን ህዝብ እጅግ ወደከፋ የድህነት አረንቅ ከተውታል:: ይህም በከፍተኛ ሁኔታ አዳዲስ የተራቡ ሌቦችንና በብዛት የሚላስ የሚቀመስ ያጡ ድሆችንም ፈጥረዋል፡፡ የወያኔ አባላቶች የቀረዑት ፖሊሲና መንግስታዊ አሰራር ሆን ተብሎ እድሜልካቸውን የህዝብና የሀገርን ሀብት እየዘረፉ እንዲኖሩ ተደርጎ ሲሆን በስልጣን በቆዩባቸው ዘመናት ምንም አይነት ህጋዊና ተጠያቂነት ያለው የስራ ባህል ስላላዳበሩ ፤በስልጠናና በዘመናዊ ትምህርት እራሳቸውን ብቁ ስላላደረጉ ከዘረፋ ውጭ ሌላ የህይወታቸውን ማቆያ የማይታያቸው ለሀገርና ለህዝብ ሸክም የሆኑ ዜጎች ሆነዋል፡፡ እንደውም ህዝብን ጉድ ያሰኛ የአንድ ወቅት ከስተት የነበረው ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንድን ባለሀብት ልማታዊ ባለሀብት ብለው በአደባባይ ሸልመው ሲያበቁ በነጋታው ወዲያው ዞር ብለው ያንን ወርቅ የሸለሙትን ግለሰብ ሌባ ነው ያዙልኝ ብለው በአንድ ለናቱ በሆነው የወያኔ ቴሌቢጅን ሲጮሁ ነበር:: ከምርጫ 97 በሃላ የታየው ህጋዊ የመሬት ዘረፋ የወያኔ ሌብነት እርቃኑን የታየበት አጋጣሚ ነበረ::ወያኔ ሌብነት ዋነኛ አላማው እንደሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብ መናገረ ለቀባሪው አረዱት ቢሆንም ቀላሉ መረጃ ግን ላለፉት 21 አመታት አንድም የትግራይ ተወላጅ ወያኔ በሙስና ለፍርድ ቀርቦም ተፈርዶበትም አይተንም ሰምተንም አናውቅም ነገር ግን የሌሎች ብሄር ተወላጅ የሆኑ የወያኔ ካድሬዎች ባስፈለገ ግዜ ሙሰኛ ተብለው እስርቤት ይገባሉ በሌላ ጊዜ ደግሞ በብሄር ተዋጾ ስም የሞግዚት ስልጣን ይሰጣቸዋል::
በሃገራችን በደልና ምሬት እጅግ በዝቷል፤ ስር የሰደደ ሰው ሰራሽ ድህነትና ጉስቁልና ከመቸውም በባሰ በመላው አገሪቱ ተንሰራፍቷል፤ እስርና ሰቆቃ የኢትዮጵያውያን የለት ተለት ከስተቶች ሆነዋል። ህገመንግስቱን በሀይል ለመናድ ሲያሴሩ ደርሼባቸዋለው በማለት የውሸት ክስ ይመሰረትባቸውና በውሸት የተቀነባበረ የሰው የቢዲዮና የፅሁፍ ማስረጃና ምስክር ቀረቦ እስር ቤት መወርወር እንደ መደበኛ የህይወት እንቅስቃሴ ከተቆጠረ ሰነበተ:: ሰላማዊ ዜጎችን ፤ለነፃነታቸው የሚታገሉትን ግለሰቦችና ቡድኖች፤ ስለ ነፃነት ፍትህና እኩልነት የማፅፉትንና የሚያዜሙትን በአሸባሪነት እየተፈረጁ ለስቃይ መዳረጋቸው ዘወትር በወያኔ የመገናኛ ብዙሀን በየቀኑ የምንሰማውና የምናየው ድራማ ሆኖል:: በከተማችን የሚከሰቱ ከባድ ወንጀሎችና ሽብሮች በወያኔ ደህንነቶች ሆን ብለው የተቀነባበሩ መሆናቸውን ዓለም የመሰከረውና ጸሀይ የሞቀው ጉዳይ ነው። ዛሬ የኢትዮጵያውያን በሃገራቸው ላይ እንደዜጋ መንቀሳቀስና በመረጠት ቦታ ህይወት መስርቶ መኖር የማይቻልበት ስርአት ላይ እንገኛለን:: የመለስ ዜናዊ አገዛዝ ስልጣን በጠመንጃ ሀይል ከያዘ ጊዜ ጀምሮ የስልጣንና የዘረፋ እድሜውን ለማራዘም በኦርቶዶክስ ሃይማኖትና ቤተርስቲያን ላይና በእስልምና እምነትና አማኞች ላይ በንቀትና በድፍረት የማያቋርጥ ጥቃት እየፈጸመ እንደሚገኝ የሰሞኑ አሳፋሪ ድርጊቶች ናቸው::እነዚህን ሁሉ በወያኔ እምባገነንና ዘራፊ ቡድኖች የሚፈፅሙትን ኢሰብአዊና ኢፍትህአዊ ድርጊቶች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ በኢትዮጵያ ህዝብ የተነሱትን የፍትህ የኩልነትና የነፃነት ትግሎችን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መተባበርና መሳተፍ ይጠበቅብናል::