ወያኔ ፈረጠጠ! ቢባልስ? መቼም አይቀርለት
አይሆንምን ትተሽ ይሆናልን ያዢ ። አለ ያገሬ ሰው።
*
ካንዱ ዝፍ፤ ሌላኝው ትዘላለች ጦጣ
አገር አፍራሽ ሄዶ፤ ቤት አፍራሹ መጣ
ማን አለ እንደ ሕዝብ፤ ባሳብ የባዘነ
ሃቅ አጥቶ ባገሩ ከልቡ እያዘነ።
*
ስሞኑን አንደ የቅርብ ወዳጄ አገርቤት ሲደወል የጥንት ጓደኛውን አገኘቶ ልቡ እያዘነ ያጫወተውን እንዲህ ሲል አጫወተኝ። ሃሎ፤… ብዬ…እንዴት……ነህ ,…. ደህና ነህ ወይ ? ስለው….. አይ… ደህንነት …. መጠየቅ እኮ…ቀርቷል።.
ነብስህ…አለ…..ወይ……ነው……የሚባለው።……ብሎ… ቢመለስልኝ ሳላስበው እንባዬ ዱብ ዱብ አለ።
ብሎ ሲያጫወጠኝ እኔም ልቤ ትክን ድብን ብሎ ብዕሬን አዋደድኩ።
ወገኖቼ የነፃነት ጥያቄ ጉዳይ በምንም በማንም ቸል የሚባልበት ጉዳይ እንዳልሆነ በቅጡ ልንገነዘብ ይገባል። ደህና ነሽ ወይ፤? ደህና ነህ ወይ? መባል ከቆመና ፤ ነብስህ አለ፤ ነብስሽ አለ? ከሆነ ነገሩ፤ ወያኔዎቸ ሳይውሉ ሳያደሩ ይፈርጥጡ ይሽቀንጠሩ።
በመቀጠልም ፡ ደዋይ….. እንደው ሕዝቡና የወያኔ እንቅስቃሴ እንዴት ነው? ብሎ ሲጠይቀው ምን ብሎ እንደመለሰለት ታውቃላችሁ? እንዲህ ነበር ያለው፦…… እንዲህ፦…. የደነበረ ጥንቸል አይተህ ታውቃለህ? አለኝ አለ…. እሱም …. ሲመልሥ….. ልቤን ሳቅም …ሲቃም…. ሞልቶት…..አዎ ….. በደንብ እንጂ አልኩት..አለ።
እሱን ካወቅክ…ወያኔ… ባሁኑ…ሰአት…… የደነበረ ጥንቸል…. ሆኖል። ..ካለ..በኋላ፤ ምንም ይሁን….ምንም…. ይምጣ..ወያኔ… መፈርጠጡ…. የማይቀር,…ነው። በማለት ስጋቱን እንዲህ ሲል ገለጸ፦እንዲህ፦
እኔንና መሰሎቼን ግን በቅጡ የሚያሣስበንና በርካታ ዜጎችም እየተመካከሩበት ያለው ጉዳይ፤ ግን የተከፈለውን መስዋትነት ከፍሎ ወያኔን ማስፈርጠጡ አይደለም። ወያኔ ከፈረጠጠ በኋላ ማን ነው ፤አገርን ተግባብቶና ተቻችሎ ሕዝብ ወደ ሚፈልገው የዲሞክራሲ ስረአት ሊመራ የሚችል የሚለው ነው።
በማለት ስጋቱን ከገለፅ በኋል አስከትሎም እንዲህ አለ፦ እንዲህ፦ ያሉት የፖሎቲካ ድርጅቶች ያልገባቸው ነገር የሕዝብ ስጋት ወያኔንና የወያኔን አጋዜን በተባበረ ክንድ ማስወገድ አይደለም። ሆኖም የሕዝብን ስጋትና ጥማት በግልጸ የተረዳ የፖሎቲካ ድርጅት በውስጥም በውጭም በአንድነት አለመደራጀቱ እንጂ ነው ያለው።
እናንተም እውጪ ያላችሁ (OLF) እና (ONLF) ከሚባሉ አፍራሽ አካሎች ጋራ ድርድሩን አቆማችሁ በአንደነት ኢትዮጵያን አስቀድማችሁ ለ ኢትዮጵያ ቁሙ:: ሲል ስጋቱን ገልፆል። ስልኩን ከመዝጋቱም በፊት ኢትዮጵያዊ አይደለንም ላሉት በራሳቸው ቋንቋ እንዲህ በሏቸው አለ። እንዲህ፦ (ካና ፊካ ቀዳዳን መኮሮኒን ኬሳ ዎሎቅቴ) በማለት፡ ምን ማለት ነው ብሎ ሲጠይቀው፤ ለዚህ ነዋ በመኮሮኒ ቀዳዳ የሾለካችሁት፤ ማለት ነው ብሎ ፤ያዘንኩትን ያሀል በመጨረሻው ቃል ስቄ ስልኩ ተዘጋ ሲል አጫወተኝ እላችኋለሁ።
የኔም ይሁን የብዙ እትዮጵያዊያን ጥያቄ ለመሆኑ ማነው Dር ብርሃኑን ለ85 ቱ ሚሊዎን ሕዝብ ተወካይ ያደረገው ነው ። ኢትዮጵያዊ አይደለንም ብለው ባደባባይ አዋጅ ከመቱት (OLF) እና (ONLF) ጋር ተደራዳሪ ሆኖ መቅረብስ ምን ለማለት ይሆን ?
እንዲህ አይነቱ ድረድርስ መልካምና ለሃገር የሚበጅ ነው ተብሎ ከአንዳንድ አገር ወዳዶች እንደሚስማው በ እርግጥ ገንቢነት ካለው ምነው ሌሎች የፖሎቲካ መሪዎች እንዲጋሩት አልተደረገም ትላላችሁ?። ማለትም በውስጥም በውጪም ያሉት ለምን አልተጋሩትም? ሌላውና አንገብጋቢው፤ ሕዝብስ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም ካለ አካል ጋር ድርድር አያስፈልግም እያለ ሲወተውት ጆሮ ዳባ ልበስ ማለቱ ተገቢ ይሆንን?። “ጉድ እስከ እሁድ ማለት ይሏችኋል ይሄ ነው”።
እንደ እኔ መረዳት ወያኔም (TPLF) ብሎ የዲሞክራሲን ስም እየጠራ ለሃያ አመት ገፋን። ሕዝብን እያስጨነቀና በአገር ላይ ያመጣውን የተንኮል ሴራ እያስፋፋ በአይናችን እያየንና የአለም ሕዝብም ጉድ እያለ ባለበት በዚህ ጊዜ ምን ጥቅም ለማስገኘት ታስቦ ይሆን ድርድሩ Dር ብርሃኑ እስቲ ይመልሱልን?።
የ (OLF) እና (ONLF) መሪዎችስ ምነው እትዮጵያዊ ነን ለማለት ከበዳቸው? በርግጥ በዛች ምደር ሳይወለዱ ፤ሳይማሩ ፤ ማረና ወተቷን ሳይጠጡና እትብታቸው ሳይቀበር ቀርቶ? ወይስ እንደው ምን ታመጣላችሁ አይናችንን አፍጥጠን አላማችንን አናሳካለን ተብሎ በማሰብ?። “ጉድ እስከ እሁድ ማለት ይሏችኋል ይሄ ነው”።
ይልቅ ቀናውና ደስ የሚያሰኝውን እኔ ልንገራችሁ። የሚባለው አዎ የ ኢትዮጵያ ችግር ገብቶናል እኛም ከሁሉም ችግራችን በፊት እትዮጵያን እናስቀድማለን፤ በቀድሞዎቹ ስረአት ተፈጽሙ የተባሉት ስህተቶች በሙሉ ደግመው በማንም ላይ እንዳይፈጸሙ ፍላጎታችን ነው። ሕዝብ በእኩልነት ተባብሮና ተከባብሮ የሚኖርባትን ኢትዮጵያ በጋራ ለመመስረት ጨቋኝና አፈራሽ የሆነውን ወያኔን ገርሥስን ጥለን አዲሲቱን ዲሞከራቲክ እትዮጵያን በተባበር የሕዝብ ክንድ እንገነባለን ብትሉ፤ አቤት ሲያምርባችሁ ሕዝብም ባጨበጨበላችሁ ነው የምለው።
እንደው እናነተስ ስታስቡት ኢትዮጵያ እኮ ወላጅ እናት ማለት ነች። ወላጅ እናቱ የበደለችው ስው ሽምግሉኝ ብሎ ቢመጣ አልወለድሽኝም ብሎ ክዶ ነው እንዴ? አይመስለኝም። ካሁን በኋላ እማዬ አለልሽም ብትሉ እንኳን እኔንጃ ምን እንደምትባሉ ሕዝብ ይፍረደ።
ከዚህ ውጪ ግን እንደው የፈለግነውን እንድንናገር መድረክ አዘጋጅቶልናል ማ ቢባል Dር ብረሃኑ ። ብላችሁ እንደፈለጋችሁ የመሆን መብት ግን ሕዝብ አይስጣችሁምና እናንተም Dር ብርሃኑም እንደገና አካሄዳችሁን አስተካከሉ አያልኩ በእዝች አጭር መጣጥፌ የዜግነት ምክሬን እንሆ እላለሁ።
በአፍሪካ ምደር እየተንቦለቦለ የመጣው እሳት ወያኔን ከመቀመጫው አስነሰቶት በተራመደበት ቦታ ሁሉ ወላፈኑ እየለበለበው በመሆኑ መፈርጠጡ አይቀሬ ነው። የ ኢትዮጵያ ሕዝብ ግን አንገቱን የደፋ ቢመስለም ቀና ያለ ለታ ከወያኔ ጋር መፋጠጡ ስለማይቀር በግዜ ማምለጡ ወይ መፈርጠጡ ለወያኔዎችና ቡችሎቻቻው ሳይበጃችው አይቀርም እላለሁ። ወያኔ ሲፈረጥጥ የተቦካው እንዳይቆመጥጥ!
“የኢትዮጵያ ሕዝብ መቼም ቢሆን አገሩን ለደርድር አቅርቦ አያወቅም ወደፊትም አያቀርብም” !
“ወያኔ ፍረጠጠ መቼም አይቀረለት ማለቴም ለዚሁ ነው”።
በቸር ይግጠመን
ሎሚተራተራ