ቤተ መቅደሱን የተከላከለችዋ የሮዛ ገብረ ሚካኤል (ኢትዮጵያዊቷ ትዕማር) ምስክርነትና የእረኞቹ ክህደት
በአብዛኛው በባንዳ ልጆች የበላይነት የተመሠረተውና በርካታ የትግራይ ወጣቶችን አዕምሮ ሰልቦና አደንዝዞ ለዕኩይ አላማው መጠቀሚያ ሁልቆ መሳፍርት የሌላቸውን ጭዳ አድርጎ ሥልጣን ማማ ላይ የተፈናጠጠው ወያኔ በትግራይ ህዝብ የኦርቶዶክስ አማኞች ላይ ያደረሰው በደል በቃላት ለመግለጽ አይቻልም። ቀደም ሲል የወያኔ መስራች የነበሩት ዶ/ር አረጋዊ በርሄ እንዳጋለጡት ወያኔ የትግራይን ህዝብ ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት በመነጠል ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር ያለውን ትስስርና ቁርኝት በመቆራረጥ ለራሱ የሚመቸውን ትውልድ ለመቅረጽ በሸረበው ሴራ ክርስትናን ትግራይ ውስጥ እጅግ አዳክሞት፣ አርክሶትና አገልጋዮችንም በአብዛኛው በካድሪዎቹ የተካና አይመቹኝም ያላቸውን ያስወገደበት ሁኔታ ፈጥሯል። በዚህም መሠረት ወያኔ እንደ መፈክር ይዞ “ኦርቶዶክስና አማራ ይጥፉ” ብሎ 17 ዓመታት ጫካ በነበረባቸው ዓመታት እንዲሁም 27 ዓመት አገሪቱን በገዛበት ዓመታትና እንዲሁም ስልጣኑን ለኦ.ህ.ዴ.ድ. አስረክቦ ትግራይ ውስጥ ከመሸገበት ካለፉት 8 ዓመታት አንስቶ በአጠቃላይ ከ52 ዓመታት ዓመታት በላይ ኦርቶዶክስን እየተዋጋትና እየተናነቃት ይገኛል። ስልጣኑ ምስጥ እንደበላው እንጨት ተቦርቡሮ ቢያልቅም እሱ ግን ኦርቶዶክስ ላይ የሰበቀውን ጦር አሁንም አላነሳም። በቅርቡም “መንበረ ሰላማ” አንዳንዶች “መንበረ አሳማ” በመባል የሚጠሩትን የጨረቃ ሲኖዶስ አቋቁሞ የለመደውን ሸፍጥ ቀጥሎበታል። በዚሁ ወያኔ ባቋቋመው የክህደት ሲኖዶስ “መንበረ ሰላማ” ተብዬ የተሰየሙ ታጋይና ካድሬ “ጳጳስ” አቡነ አረጋዊ ዝሙት የመፈጸማቸው ወሬ በማህበራዊ መገናኛዎች ላይ ብዙ አስተያየት እየተሰጠበት ይገኛል።
“ቤተ መቅደሱን የተከላከለችዋ የሮዛ ገብረ ሚካኤል (ኢትዮጵያዊቷ ትዕማር) ምስክርነትና የእረኞቹ ክህደት” በሚል ቀሲስ አስተርአየ ጽጌና መምህር ፈንታሁን ዋቄ ያካሄዱትን ካለፈው የቀጠለ ውይይት አቅርበንላችኋል።