“አርሲ ላይ በሰይፍ ከመሸነፍህ በፊት መጀመሪያ የተሸነፍከው በፕሮፓጋንዳ ነው” ዶ/ር መስከረም ለቺሳ

አርሲ ላይ በሰይፍ ከመሸነፍህ በፊት መጀመሪያ የተሸነፍከው፡ በፕሮፓጋንዳ ነው
ዶ/ር መስከረም ለቺሳ

ከፌስ ቡክ የተገኘ

አንተ ኦርቶዶክሳዊ ወጣት ሆይ!

ላንተ ገለልተኛ እንዲያውም ኦርቶዶክስ የሚመስሉህ ነገር ግን ጥልቅ ፀረ ተዋሕዶ ጥላቻና ዒላማ ያላቸው መናፍቃንና አሕዛብ ፖለቲከኞች የኾኑ ምሑራን፣ የስነ ጽሑፍ ሰዎች፣ ጋዜጠኞች፣ የታሪክ ተመራማሪዎች፣ ደራሲዎች፣ መጣጥፍና መነባንብ አቅራቢዎች፣ ኮሜድያኖች፥ የድርጅት ሥራ አስኪያጆች፣ አንባቢዎችና ፈላስፎች፣ ኹሉን አቃፊ የሚመስሉ የሶሻል ሚድያ ዜናና ወሬ አቅራቢዎች፣ በየራድዮው የምትሰማቸው መዝናኛ ፕሮግራም አዘጋጆች፥ ወዘተ… ለረዥም ጊዜ በአእምሮህ ሲስሉብህ የኖሩት፡ አንተና መሰሎችህ ኦርቶዶክሶች፡ እና አባቶቻችሁ፡ ሰው ስትገድሉ እንደኖራችሁ፥ ስትረግጡና ስትበድሉ፣ ስታፍኑ እንደኖራችሁ፣ ፈላሻውንና ሙስሊሙን፣ ካቶሊኩንና ጴንጤውን ስታሳድዱ እንደኖራችሁ፣ አሁንም በደማችሁ ያ ዝንባሌ እንዳለ፣ ኹሉንም በግድ ኦርቶዶክስ ለማድረግ ስትጫኑ እንደኖራችሁ፣ ረጋጭ እና ጨቋኝ ባሕሪ እንዳላችሁ፥ ሌላው ቀርቶ፡ ለእምነታችሁ እንኳ የምትቆረቆሩት፡ በመኃይምነትና በድንቁርና ምኑንም ሳታውቁትና እግዚአብሔርን ሳትወድዱት እንደኾነ አድርገው፡ በቀልድም በቁም ነገርም ሲነግሩህና በገዛ እምነትህ ላይ እምነት እንድታጣ፥ ኃይል ያለውም እንዳይመስልህ ሲሠሩ ነው የኖሩት።

ስለዚህ፡ አሁን ያንን ለማካካስ፡ ለስላሳ፣ ቅልስልስ መኾን እንዳለብህ፥ የሌላ እምነት ተከታዮችን ለማባበልና ለማስደሰት፡ የራስህን እምነት ጠንካራ አገልጋዮችን እንድትነቅፍ፥ “አክራሪ ናቸው” ብለህ እንድትወቅስ፥ ከኹሉም በላይ ደግሞ፡ የኹሉም እምነት ተከታዮች approval ያልሰጡትን የራስህን አገልጋይ እንዳትቀበልና የእውነተኛ መምህር/አገልጋይ መለኪያው ኹሉንም እምነቶች የሚወድና የሚቀበል መኾን እንዳለበት እንድታምን፥ እውነተኛ የሃይማኖት ሰው ማለትም ለኹሉም ሃይማኖቶች ጥቅም እኩል የሚሠራ እንደኾነ እንዲመስልህ አድርገው፡ የተልመጠመጠ መሥፈርት በየአጋጣሚው አእምሮህ ውስጥ ጠቅጥቀውብሃል። ያንን ለማውጣት በጣም ከብዶሃል። አሁን “ኦርቶዶክሳውያን በእምነታቸው ተለይተው እየተገደሉ ነው” ስትባል፡ ለራስህ እምነት መቆም ተሥኖሃል። “ኃጢአት ነው” ብለው ሲነግሩህ ኖረዋላ! “ወገንተኝነት ነው” ብለው ሲያንቋሽሹብህ ኖረዋላ! “ለራስህ ሃይማኖት ማዳላት ነውር ነው” ብለውሃላ! እና በየት በኩል ሙሴ ትኾናለህ? በየት በኩል የነኢያሱና የነሶምሶን፥ የነአስቴርና የነዮዲት፥ የነዳዊትና የነሰሎሞን፥ የሐዋርያትና የሰማዕታት በረከት ይደርብህ? እነሱ’ኮ የቆሙት አንዲት ብቻ ለኾነችው የእግዚአብሔር እውነት ነው?!

አደንዛዦችህ፡ “ወገንተኝነት ተው” የሚል ስብከት የሚነግሩህ፡ ላንተ ብቻ እኮ ነው?! እነሱ አያምኑበትም። የምትጠፋበትን መንገድ ብቻ ነው የሚቆምሩልህ። በያጋጣሚው፡ ፊት ለፊት በሽልማት በእውቅናና በምስጋና ፕሮግራም ሲያሞግሡና ሲያደንቁልህ የምታያቸው፡ ለአንተ አርአያ እንዲኾኑ የሚፈልጓቸውን መንፈሳዊ አቋም የሌላቸው መሃል ሰፋሪዎችን ነው። ለሃይማኖቱ የቆመ ሰው፡ በዚህ ዘመን “አደገኛ” እና “በኅብረተሰቡ መካከል ግጭት ለመፍጠር የሚሠራ” እንደኾነ አሳምነውሃል። አንተም ተቀብለኸዋል።

ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች ሆይ!

ብዙዎቻችሁ በማይመስሏችሁ ሰዎች የሶሻል ሚድያ account ሥር follower እና subscriber ኾናችሁ ተኮልኩላችሁ ሳያችሁ እጅግ ይገርመኛል። Atheist, መናፍቅ፥ ፀረ-ኦርቶዶክስ የኾኑ ገጾች ላይ ምን ትሠራላችሁ? የግድ የሚያስቅ ነገር ስለጻፈ እኮ follow ማድረግ አለባችሁ ማለት አይደለም፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*