“ወይ ጊዜ ስንቱን አሳየን?” በአያልነሽ ድልነሳሁ
“ወይ ጊዜ ስንቱን አሳየን?” በአያልነሽ ድልነሳሁ
ወ/ሮ አያልነሽ ድልነሳሁ የተባሉ የድረ ገጻችን ተከታታይ አብይ አህመድ ህዝብን አጨናብሮ የስልጣን ማማ ላይ ከተቆናጠጠ ጊዜ አንስቶ በአገራችን ፖለቲካ ውስጥ የታዘቡትን ነገሮች በገላጭ ስንኞች ቋጥረው አቅርበውልናል። አብይ አህመድ የሚግታቸውን እንቶ ፈንቶ እንደ ትክክለኛ ነገር በመቁጠር በደጋፊነት የተቸነከሩ ሰዎች በአገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ያደረሱት ጉዳት በቀላሉ የሚገመት አይደለም። በአብይ አህመድ ፍቅር የወደቁ በተለይም በዲያስፖራ የሚገኙ ሰዎች ለመደገፍ የተሰለፉበት ምክንያት ተቀይሮ በአፍ ጢሙ ቢደፋም እነሱ ግን አሁንም በደጋፊነት ተቸክለው ቀርተዋል። ምን አይነት አፍዝ አደንግዝ ቢያስነካቸው ይሆን ወይንስ የጎሳና የመንደርተኝነት አባዜ ተጸናውቷቸው ነው እንደዚህ ያበዱት? ወይንስ ኢትዮጵያ ለመመላሰስና በደሃው ወገናችን ላይ ለመሳለቅ ፍቃድ እንዳይከለከሉ ይሆን? ለማንኝውም ከአብይ አህመድ ጋር እራሳቸው ስላጣበቁና የወገናቸው መጨፍጨፍ ግድ የማይላቸውን ሆዳሞች የሚነቅፈውንናና የሚገስጸውን ወ/ሮ አያልነሽ ድልነሳሁ የላኩልልን ግጥም ከዚህ በታች አቅርበንላችኋል።
ወይ ጊዜ ስንቱን አሳየን?
ስንቱን አሰማን?
እንዲህ የተከፋፈልነው፣
ስንቱን አሰማን?
እንዲህ የተከፋፈልነው፣
የተለያየነው የተራራቅነው
በአሰሱ በገሰሱ፣
በጥቃቅንና ትንንሹ፣
በአሰሱ በገሰሱ፣
በጥቃቅንና ትንንሹ፣
በማያስፈልገው በማይረባው፣
ቅንነት ጠፍቶ አይሎ ሴራው፣
ቅንነት ጠፍቶ አይሎ ሴራው፣
በጣም የሚገርመው፣
ጥቅመኛውና አጭበርባሪው፣
ጥቅመኛውና አጭበርባሪው፣
በውጭ ያለው፣
ያ ጉደኛ ዲያስፖራው፣
ያ ጉደኛ ዲያስፖራው፣
የባዕድ አገር ዜግነት የያዘው፣
የአገር ቤቱ ጥይቱና ገጀራው የማይነካው፣
ገዥንና ገዳይን በጭፍን የሚደግፈው፣
ገዥንና ገዳይን በጭፍን የሚደግፈው፣
በስሜት ሰክሮ የሚያናፋው፣
እርስ በርሱ ሲቃረን ለዓመታት የኖረው፣
ብዙ አልን ብዙ አወራን ቀባጠርን፣
አወይ እራሳችንን እያታለልን፣
የሀሳብ የበላይነት ያገኘን እየመሰለን፣
የምንሰማውንና የምናየውን ማመን እያቃተን፣
አስመስለን ኖርን፣
እርስ በርሱ ሲቃረን ለዓመታት የኖረው፣
ብዙ አልን ብዙ አወራን ቀባጠርን፣
አወይ እራሳችንን እያታለልን፣
የሀሳብ የበላይነት ያገኘን እየመሰለን፣
የምንሰማውንና የምናየውን ማመን እያቃተን፣
አስመስለን ኖርን፣
እያጨናበርን እያታለልልን፣
ሌባን ሌባ! ገዳይን ገዳይ! ማለት እያቃተን፣
ሌባን ሌባ! ገዳይን ገዳይ! ማለት እያቃተን፣
በሌሎች በማይመለከታቸው እያላከክን፣
ምን ብለን እንጥራው ይሄንን፣
የአእምሮ መደንዘዝ ነዉ ያጋጠመን?
ወይስ የአስተሳሰብ መዝቀጥ?
ወይስ ሆድን ለመሙላት መርመጥመጥ!
ምን ብለን እንጥራው ይሄንን፣
የአእምሮ መደንዘዝ ነዉ ያጋጠመን?
ወይስ የአስተሳሰብ መዝቀጥ?
ወይስ ሆድን ለመሙላት መርመጥመጥ!
ወይስ በጎሳ፣ በቋንቋና በብሔር መሸቀጥ?
ምንድን ነው የሆንን?
ስም የለውም ህመማችን፣
ምንድን ነው የሆንን?
ስም የለውም ህመማችን፣
መድኃኒት የለውም በሽታችን።
ምን ተሰማችሁ አሁን?
እኛ ማነን?
አቅም አለን?
ለመተቸት ያለፈውን የአባቶቻችንን የጥንቱን?
አስተውሎ የሚሰማ አይንና ጆሮ ከሰጠን፣
የሚያዝን የሚቆረቆር ሰብአዊነት ካደረብን፣
ምን ያልተፈፀመ አለ በእኛ ክፍለ ዘመን፣
በተወለድንባት በአደግንባት በአገራችን፣
ስንቶቻችን ጆሯችንን ደፈንን፣
ከሩቁ ጊዜያዊ ሰላማችንን ምቾታንን መርጠን፣
ምን ተሰማችሁ አሁን?
እኛ ማነን?
አቅም አለን?
ለመተቸት ያለፈውን የአባቶቻችንን የጥንቱን?
አስተውሎ የሚሰማ አይንና ጆሮ ከሰጠን፣
የሚያዝን የሚቆረቆር ሰብአዊነት ካደረብን፣
ምን ያልተፈፀመ አለ በእኛ ክፍለ ዘመን፣
በተወለድንባት በአደግንባት በአገራችን፣
ስንቶቻችን ጆሯችንን ደፈንን፣
ከሩቁ ጊዜያዊ ሰላማችንን ምቾታንን መርጠን፣
እንደልባችን ኢትዮጵያ መመላለሱ እንዳይቀርብን!
ወይስ በተብለጭልጯ ከተማችን ተማረክን?
ወይስ በተብለጭልጯ ከተማችን ተማረክን?
ኮሪደሩን መናፈሻው ግርግሩ አጃጀለን?
ህዝቡን ከቤቱ ያፈናቀለውን፣
አዲስ አበቤን እርስቱን ቅርሱን የቀማውን፣
ሰንደቁን ቅርሱን ማንነቱን ያረከሰውን፣
ማተቡን ጥለቱን በጫማ የረገጠውን፣
እናትና ልጆቿን በጅብ ያስበላውን፣
ይህንን የመከራና የአሳር ዘመን፣
የግራኝን ዘመን ያስታወሰንን፣
አልን በለፀግን ሰለጠንን፣
ታሪክ ይፍረድብን የንጹሃን የዕንባ ጎርፍ ይውሰደን፣
የስንቶችን ቤት ሲፈርስ የዘመናት ድካም ሲጨልም፣
በምን ሂሳብ በምን ካሳ ብለን፣
አልጠየቅንም እራሳችንን፣
ምን አዚም ነው አፋችንን ያስለጎመን?
በምን ሂሳብ በምን ካሳ ብለን፣
አልጠየቅንም እራሳችንን፣
ምን አዚም ነው አፋችንን ያስለጎመን?
የግል ድሎት አገር ቤት ሽርሸሩ እንዳይቀርብን፣
አስጨፈጨፍን፣ አሰደደን፣ አፈናቀለን፣ እረ ስንቱን።
ግፈኛው፣ አረመኔው፣ ጎሰኛው የውሸት ንጉስ፣
አስጨፈጨፍን፣ አሰደደን፣ አፈናቀለን፣ እረ ስንቱን።
ግፈኛው፣ አረመኔው፣ ጎሰኛው የውሸት ንጉስ፣
ሰሜን ጠሉ ኦርቶዶክስ ጠሉ፣ ታሪክ ሲገዘግዝ ስንቱን
አለፈ የስንቱ ምስኪን ህይወት፣
ስንቱን ሰደደ ወደ እስር ቤት፣
በዚህ በ21ኛው ክፍለ ዘመን፣
ከሰውነት ወጣን ተዋረድን፣
ሁሉን በገሀድ ተጫወቱብን፣
ተበቱብን አፌዙብን፣
በስንት አይነት ስሞች ጠሩን፣
ሁሉ የኔ የሚሉ ስግብግቦች መጡብን፣
ለባዕዳን ለጠላቶች ተሸጥን፣
በጀግንነት አባቶቻችን ያስረከቡንን፣
እኛ በፈቃዳችን ያለንን ሁሉ አስረከብን፣
ምን ቀረን? እረ ምን የለም የቀረን?
እውነትን ካድን ምቾት ሰለበን፣
በሀብት በንብረት ተደላደልን፣
ሆንን ላለመስማማት የተስማማን፣
ቅንነት የጠፋብን፣
ሁሉም ለበጎ ነዉ እያልን፣
አለፈ የስንቱ ምስኪን ህይወት፣
ስንቱን ሰደደ ወደ እስር ቤት፣
በዚህ በ21ኛው ክፍለ ዘመን፣
ከሰውነት ወጣን ተዋረድን፣
ሁሉን በገሀድ ተጫወቱብን፣
ተበቱብን አፌዙብን፣
በስንት አይነት ስሞች ጠሩን፣
ሁሉ የኔ የሚሉ ስግብግቦች መጡብን፣
ለባዕዳን ለጠላቶች ተሸጥን፣
በጀግንነት አባቶቻችን ያስረከቡንን፣
እኛ በፈቃዳችን ያለንን ሁሉ አስረከብን፣
ምን ቀረን? እረ ምን የለም የቀረን?
እውነትን ካድን ምቾት ሰለበን፣
በሀብት በንብረት ተደላደልን፣
ሆንን ላለመስማማት የተስማማን፣
ቅንነት የጠፋብን፣
ሁሉም ለበጎ ነዉ እያልን፣
በጎ ስራ ግብረገብ የሌለን፣
ከአምላካችን ያሳዘንን ያስቀየምን፣
ኧረ ልበል ስንቱን…፣
ሰው መሆን ጠፋብን።
ኧረ ምንድን ነን?
መልስ የለንም ምንም፣
የሌላውን ሕመም አልተሰማንም፣
አቤቱ እርዳን፣
ትንሿን መፍትሔ ስጠን፣
እርዳን እንድንሞክራት ይህችን፣
መጀመሪያ እንታረቅ ከራሳችን፣
እንድንጠይቅ ውስጣችንን፣
ማን ነኝ?
ምን አደረኩኝ?
እንፈልግ እውነትን፣
ስህተታችንን አምነን፣
ጠይቀን ምህረትን፣
ከአምላካችን ያሳዘንን ያስቀየምን፣
ኧረ ልበል ስንቱን…፣
ሰው መሆን ጠፋብን።
ኧረ ምንድን ነን?
መልስ የለንም ምንም፣
የሌላውን ሕመም አልተሰማንም፣
አቤቱ እርዳን፣
ትንሿን መፍትሔ ስጠን፣
እርዳን እንድንሞክራት ይህችን፣
መጀመሪያ እንታረቅ ከራሳችን፣
እንድንጠይቅ ውስጣችንን፣
ማን ነኝ?
ምን አደረኩኝ?
እንፈልግ እውነትን፣
ስህተታችንን አምነን፣
ጠይቀን ምህረትን፣
ተማጸንን ቸርነትህን፣
ይቅር ብለን፣
ንስሀ ገብተን፣
የተከፋዉን አፅናንተን፣
የተበደለውን ክሰን፣
ትክክለኛ ፍርድን ተቀብለን፣
ከጥፉታችን ተምረን፣
እንደ በደላችን ታርመን፣
ስንፈልግ ያልታበየ ሰላምን፣
ይታረቀናል ፈጣሪያችን፣
አቤቱ ማረን፣
አቤቱ ይቅር በለን፣
አሜን አሜን አሜን………..
ይቅር ብለን፣
ንስሀ ገብተን፣
የተከፋዉን አፅናንተን፣
የተበደለውን ክሰን፣
ትክክለኛ ፍርድን ተቀብለን፣
ከጥፉታችን ተምረን፣
እንደ በደላችን ታርመን፣
ስንፈልግ ያልታበየ ሰላምን፣
ይታረቀናል ፈጣሪያችን፣
አቤቱ ማረን፣
አቤቱ ይቅር በለን፣
አሜን አሜን አሜን………..