“ዝክረ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ” በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ
“ዝክረ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ” በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ
“ዝክረ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ” ፓትርያርኩ አቡነ መርቆርዮስ ባረፉ ጊዜ ቀሲስ አስተርአየ ለመታሰቢያቸው እንዲሆን የተቀኙትን ቅኔ ነው፡፡ ቅኔው አቡነ መርቆርዮስ በዝምታ ያሳለፉትን ምሥጢር የታዘቡት ቀሲስ የራሳቸውን ትዝብት የገለጹበት ነው፡፡ ቀሲስ ያቀረቡት ቅኔ በአቡነ መርቆርዮስና በጠቅላይ ምንስቴር ዓቢይ የተካሄደውን ለሕዝብ ግልጽ ያልሆነውን ውይይት የተሸከመ ነው፡፡ ጥቅላይ ምንስቴሩ አጎንብሰው የሚታዩት በፓትርያርኩ ፊት ነው፡፡ ጠቅላይ ምንስቴሩ በፓትርያርኩ ፊት ማጎንበሳቸው እንጅ ትኩረታቸውም ንግግራቸውም ከሌላ ሰው ጋራ ነው፡፡
ፓትርያርኩም ትኩረታቸውን ሰጠው የሚመለከቱትንና የሚሰሙት በፊታቸው ያጎነብሱትን ጠቅላይ ምንስቴሩን አልነበረም፡፡ የሚመለከቱት ወደ ላይ ነው፡፡ ሁለቱም ጠቅላይ ምንስቴሩም አቡነ መርቆርዮስም ስሜታቸውም ትኩረታቸውም በሌላ ሶስተኛ አካል ተዘርፏል፡፡ ሁሉቱም ማንን ነበር የሚመለከቱት? የሚሰሙት? ፡፡ የሁለቱን ትኩረት የሳበው? ማን ነበር? ምን ነበር? ሁለቱም ፓትርያርኩም ጠቅላይ ምንስቴሩም ትኩረታቸውን ከየራሳቸው አንስተው ያሳረፉት በሌላ ከፍ ብሎ የቆመ በሚመስል አካል ነው፡፡
በዙሪያው የነበራችሁ አስታራቂወች ነን የምትሉ ጠቅላይ ምንስቴር ዐቢይ ማንን ነበር አንጋጠው የሚያዩት? በመካከል ገብቶ የሁለቱን ትኩረት የሳበው ማነው? ምን አለ ? ተብላችሁ ብትጠየቁ መልሳችሁ አንድ ይሆናል ተብሎ አይገመትም፡፡ በቃል ባይገለጽም የሁለቱም ስሜትና ትኩረት የሚሚገልጸው ፎቶው የሚጠቁመው ነገር አለ፡፡ በዚያ ወቅት የተፈጸመውን ዛሬ መለስ ብላችሁ ብታዩት ምን ይሰማችኋል? የቅኔው ይዘት ይገባችኋል? እነ አባ ፋኔልና በሳቸው የተካኑት ቄሶች ይገባቸዋል ተብሎ አይገመትም፡፡
ቀሲስ አስተርአየ “በፊታቸው ከቆምነው መካከል እውነትን የያዘ ስላልነበረ በብዙ ትዝብት ታፍነው የሞቱትን አቡነ መርቆርዮስን ጠጠር ጎርሶ ከሞተው ከአጋቶን ጋራ ማነጻጸር የሁለቱንም ታሪክ ያዛባ ነውና የቤተ ክርስቲያን ዝክረ ታሪክ አይቀበለውም” ብለው የደመደሙበትን ቅኔ በዚያች ሰአት በፓትርያርኩና በጠቅላይ ምንስቴር ዓቢይ የተካሄደውን የገለጹበት ይመስለኛል፡፡
እራስን ተዋናይ አድርጎ ከማቅረብ የራቀ የተመልካችን ቀልብ ስቦ ተጠቃሚ ከመሆን የሸሸና ቅኔውን የተረዳ እውነተኛ ቄስ በመካከል ቢኖር ይህችን የቀሲስን ቅኔ ፎክሮ ከማቅረብ የሚገታው አልነበረም፡፡ ቅኔውን የሚረዱ ቀሳውስት ቢኖሩም ራሳቸውን ስሊሚገርፋቸው አያነቡትም፡፡ እንዲነበብም አይፈልጉም፡፡ ይህን የመሳሰሉትን ደፍረው ለማቅረብ የሚሞክሩት መምህር ፋንታሁን ዋቄ ብቻ ይመስሉኛል፡፡ ለማንኛውም ከአምስት ዓመታት ገዳማ በፊት የለቀቅናትን ጽሑፍ በድጋሚ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። ዝክረ አቡነ መርቆርዮስ