የሁቲ አማፂያን በሳዑዲ አረቢያ ሪያድ የሚገኝ የነዳጅ ማከማቻ ማጥቃታቸውን አስታወቁ

የሁቲ አማፂያን በሳዑዲ አረቢያ ዋና ከተማ ሪያድ የሚገኘውን የነዳጅ ማከማቻ በተወንጫፊ ሚሳዔል እና ድሮኖች ማጥቃታቸውን አስታወቁ። ሳዑዲ አረቢያ ጥቃቱ ስለመፈጸሙ ወዲያውኑ ማረጋገጫ አልሰጠችም። የሁቲ ታጣቂዎች ጥቃቱን የፈጸሙት ሳዑዲ በሰነዓ እና ሌሎች የየመን ግዛቶች ላይ ለፈጸመቻቸው የአየር ድብደባዎች ምላሽ መሆኑን ተናግረዋል።