ተጎግራሲ በአፍሪካ (አለማየሁ ገብረማርያም)
ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም
(በሳምንታዊው አምዳቸው ላይ ካሰፈሩት በከፊል የተተረጎመ)
ዴሞክራሲ የሕዝብ ለሕዝብ በሕዝብ የሆነ መንግሥት ከሆነ ተጎግራሲ ደሞ የሌቦች ለሌቦች በሌቦች መንገስት ነው፡፡ተግታቶርሺፕ ባጭሩ በሞላጫ ሌቦች የሚመራ ህግ ነው፡፡አሁን እንደሚታየውና በግላጭ ፈጦ እንደሚታወቀው አፍሪካ በግል ንብረትነት ተይዛ ደም በጠማቸው ነፍሰገዳዮች የምትገዛ የተጎገራሲ አህጉር ናት፡፡
በተግታቶርሺፕ ስርአት ስልጣን ላይ እንደምንም ተቆናጦ ላለመልቀቅ ባለ ሃይልና ጉልበት ሁሉ ጨምድዶ የመያዝ ጥቅሙ፤ የግል ሃብትንና ንብረትን ለገዢው መደብ አባላት ጠቀሜታ ብቻ እንዲውል፤ ከሕዝቡ ላይ በመግፈፍ፤ በመስረቅና በመቀማት ማጠራቀም ሲሆን፤ ይህም የምስኪኑን ህዝብ ጉረሮ በመዝጋትና ጦም አዳሪ በማድረግ ለመከራ ማጋለጥ ማለት ነው፡፡
የእንግሊዝኛው ቃል ተግ ከህንዲ ቃል ታሀጋ ከሚለው የተወሰደ ሲሆን ትርጉሙም ‹‹ገዳይ›› ማለት ነው፡፡በሕንድ ታህጊዎች ከዓመታት በፊት በተደራጀ የመሳርያ ትጥቅ በመታገዝ፤ ያልጠረጠሩ መንገደኞችን በማንበርከክ፤ ገንዘብ ይዘርፉና ለመዝረፍም ይገድሉ ነበር፡፡አሁን ያሉት የአፍሪካችን ታጊዎች ደግሞ ከሕዝባቸው በመሰወርና ለሰላም፤ ለዴሞክራሲ፤ ለፍትህ፤ ለተጠያቂነት፤ሙስናን ለማጥፋት፤የህዝቡን ድሎትና እድገት የምናቅድና ተግባራዊ የምናደረግ ነን በሚል ቅጥፈት በተመላበት መሃላቸው፤ በማጭበርበርና ባስታጠቋቸው የግድያ አዋቂዎች በመታገዝ፤ የዋሁንና ምንም የሌለውን ህዝብ እንዳያልፍለት፤ ከሃገሪቱ ሊደርሰው የሚገባውን ይሰርቁታል፡፡ከዚህም ያሰባሰቡትን ሃብት በአውሮፓና በአሜሪካ ባንኮች ያከማቻሉ፡፡እነዚህ ለሕዝብ ቆመናል የሚሉ አውሬዎች፤ በሚገዘዋቸው ሃገራት ጎዳናዎች ላይ ባማረና ባሸበረቀ ትላልቅ ቦርድ ላይ ተጽፎ የሚነበበውና ለውጪው ዓለም ጎብኚዎችና ዓለምአቀፍ የኤምባሲ አባላት ማታለያቸው ‹‹ሙስናን እንታገላለን›› ‹‹ለሕዝብ የበላይነት ቆመናል›› ‹‹የሰብአዊ መብት ጥበቃ የህዝብ ዋስትና ነው›› ‹‹የብሔር ብሄረሰቦች መብት ይከበራል›› ‹‹ፍትሃዊነት የህዝብ ልእልና ነው›› ‹‹በእኩልነት ላይ የተመሰረተ አንድነት›› ‹‹ሕገመንግስቱን ማክበር የህዝብ ግዴታና መብትም ነው›› የሚሉት ናቸው፡፡
ዛሬ የሊቢያው ተግታቶር ሙአመር ጋዳፊ ከሕዝብ በተዘረፈ፤በተቀማና በተሰረቀ በሃገር ንብረት፤ በሕዝብ ሃበት እየተጠቀመና ጉልበተኛ በመሆን፤ ቴጎግራቲክ መንግስቱን ሊጠብቅና ጊዜ ባለፈበትና ሕዝብ በተፋው ስልጣኑ ላይ ለመቆየት፤ ከሃገር በዘረፈውና በውጭ በስውር በየባንኩ ባካበተው የዘይት ሽያጭ ገንዘብ፤ እየተንደፋደፈ ነው፡፡ በቅርቡ የእንግሊዝ መንግስት በለንደን ባንክ የተጠራቀመውን የጋዳፊን 20 ቢሊዮን ፓውንድ እንደሚያግድ ተናግሯል፡፡የስዊዝ መንግስትም በስዊስ ያለውን የጋዳፊንና የግብረአበሮቹን 613 ሚሊዮን የስዊስ ፍራንክ እንደሚያግድ ይፋ አድርጓል፡፡ይህም ማለት 658 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ነው፡፡በ2008 በተጋለጠው የጋዳፊ ልጅ ቅሌትና፤ በቁጥጥር ስር ከመዋሉ በፊት በስዊስ የሚገኘው የጋዳፊ ንብረት 5.7 ቢሊዮን በጥሬ ገንዘብ፤812 ሚሊዮን ፍራንክ ደሞ በተለያየ ማትረፊያ ገበያ ላይ ነበር፡፡በ2006 የሊቢያ መንግስት ኢንቬስትመንት 70 ቢሊዮን ነበር፡፡የአሜሪካን መንግስት በትሪፖሊ የሚገኘውን ኤምባሲውን ከዘጋ በኋላ የሊቢያን ጠቅላላ ንብረት አግዶ ነበር፡፡
የ42 ዓመታት የግፍ አገዛዝ በቃኝ ብሎ የተነሳን ሰላማዊና አንዳችም መሳርያ ያልያዘ ሕዝብ፤ጋዳፊ የአምባገነን መንግስቱንና ስላጣኑን ይዞ ለማቆየት ሲል የዓየር ኃይሉን በማዘዝ በቦምብና በሌላም መሳርያ እንዲደበደብ አዘዘ፡፡ የግፈኛውና የአምባገነኑ ጋዳፊ ልጅም ሳይፍ አል ኢስላም ‹‹አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ›› ነውና ሃገሪቱን ወደማያልቅ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ በማስገባት ለሚቀጥሉት 30 ወይም አርባ ዓመታት እንደማተወጣም በድፍረትና በሕዝብ ንቀት ይናገራል፡፡ አባቱና ቤተሰቡ በሚያዝበት ቴሌቪዥን ላይ የሊቢያው ወጣት ተግ በሰጠው መግለጫና ማስፈራርያ ‹‹ሊቢያ የደም ጎርፍ ትሆናለች፤እስከመጨረሻው ጥይትና እስከመጨረሻው ደቂቃ አዋጋለሁ፡፡ እስከመጨረሻው የደም ጠብታዬ ድረስ እታገላለሁ ከማለትም አልፎ፤ድንፋታሙ አል ኢስላም ለዓለም ህዝብ በገባው ቃል መሰረት፤በሊቢያ ኖሬ ሊቢያ ውስጥ ህይወቴ ታልፋለች፤ሌላው አማራጭም በሊቢያ ኖሮ በሊቢያ መሞት፤ ሌላው አማራጬም በሊቢያ ኖሮ በሊቢያ መሞት ነው ብሏል፡፡ አንድ በመንግስት ስልጣን ውስጥ አንዳች ቦታ የሌለው ሰው እንዲህ ያለ የጥጋብ ንግግር ማድረግ እጅጉን አሳፋሪና አሳዛኝም ነው፡፡
ጋዳፊም ቢሆን የገባው ቃል ተዋግቶ እንደ ጀግና ለራሱ ተጎግራሲ ለመሰዋት ዝግጁ መሆኑን ነው፡፡በአረንጓዴው አደባባይ የተሰበሰቡትን ደጋፊዎቹንና አገልጋዮቹን ትግላችሁን አጠናክራችሁ ‹‹ለህዝብ ስትሉ ተዋጉ››በማለት አውጇል፡፡ ተነሱባቸው! ተነሱባቸው! በማለት እያንባረቀ መመርያ ሰጠ፡፡አሁን በጭፈራና በዘፈን እራሳችንን እናዘጋጅ፡፡ዝፈኑ! ጨፍሩ! ጊዜው ሲደርስ የመሳርያ ግማጃ ቤቶቻችን ተከፍተው ለደጋፊዎቻችን በቂና አስፈላጊ የሆነውን መሳርያ እናድላለን፡፡ሊቢያን ለመጠበቅና ለማዳን ተዘጋጁ! ዘይታችንን እናድን! የህዝቡን ክብርና ነጻነትን እናድን! ጊዜው ሲደርስ ሁላችሁም መሳርያ ይኖራችኋል፤ ሁሉም መሳርያ ይይዝና ሊቢያ በእሳት፤ በጥይት እሳት ትቀላለች!፡፡
ለጋዳፊና ለአገልጋዮቹ ላለፉት 42 ዓመታት የተካሄደው የግፍ አገዛዝ አልበቃቸውም፤ አሁን የሚያቅዱት ጠቅላላ ሃገሪቱንና ሕዝቡን ጨርሰው ሃገሪቱ የአመድ ማጠራቀሚያ እንድትሆን ነው፡፡‹‹እኔ ከሞትኩ ሰርዶ ይብቀል›› እንዲሉ፡፡
የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሃፊ ባንኪሙን እንዳሉት አይቮሪ ኮስትም ወደ እርስ በርስ ጦርነት ለመግባት ጠርዝ ላይ ነች ብለዋል፡፡የአውሮፓ ዩኒየን፤የስዊስና የአሜሪካ መንግስታት በየሀገራቸው ያለውን የባግቦን ንብርትና ሃብት እንዳይነቀሳቀስ አግደዋል፡፡
መለስ ካለምንም ይሉኝታና ሃፍረት፤በግንቦት 2010 ምርጫውን በ96.6 በመቶ አሸንፌያለሁ አለ፡፡የአውሮፓ ሕብረት ታዛቢዎች የምርጫው ሜዳ ያደላና ለአንድ ወገን ብቻ የተሰመረ ነበር የዓለም አቀፍን የምርጫ ደንብ አላሟላም በማለት ልክ ባገቦ ላይ እንደተባለው አይነት፡፡ ‹‹የተሰረቀ የምርጫ ሂደት›› ለማለት የተሰጠ አስተያየት ነው፡፡የአውሮፓ ሕብረት በ2005 ባወጣው የምርጫ ዘገባ ላይ ‹‹የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ የሚመራውና የተያዘው የኢህአዴግ ንብረት በሆኑ የንግድ ድርጅቶች ነው፡፡እንደ ዓለም ባንክ ዘገባም ቢሆን የሃገሪቱ ከግማሽ በላይ የሚሆነው የኤኮኖሚ ይዞታ የሚገኘው የኢህአዴግ በሆኑ እንደኤፈርት ባሉት የንግድ ድርጅቶች ነው፡፡
የኤፈርት ህልቆ መሳፍርት የሌለው የትራንስፖርት ኩባንያ፤የግንባታ ኩባንያው፤የመድሃኒት ፋብሪካው፤እነዚህ ሁሉ የኤፈርት ስብስቦች የንግድ ድርጅቶች ናቸው፡፡እነዚህ ድርጅቶች ደግሞ ወፋፍር ድጋፍ ከውጭ ድርጅቶች ይጎርፍላቸዋል፡፡ ገዢው ፓርቲ ራሱ ባዋቀረው የሙስና ኮሚሽን ሪፖርት መሰርት በ2008 16 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚያወጣ የወርቅ ጥፍጥፍ በጠራራ ጸሃይ ከባንክ መሰስ ብሎ መውጣቱን ይፋ አድረጓል፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ደግሞ እራሱ መለስ ዜናዊ ካላንዳች ሃፍረትና ይሉኝታ ‹‹ለውጭ ገበያ የተዘጋጀ 10000 ቶን ቡና ከመጋዘን የት እንደገባ አልታወቀም›› ማለቱ ይታወሳል፡፡ ነጋዴዎቹን ሰብስቦ በቪዲዮ የተቀረጸውን ንግሩን አስደመጠ፡፡‹‹በዚህ በ10000 ቶን ቡና መሰወር የሁላችንም እጅ ስላለበት ይቅር እላቸዋለሁ፤ከእንግዲህ ግን ቡና ሲሰርቅ የተገኘውን እጁን እቆርጣከን›› አለ፡፡
በ2005 መለስ ግዛቱን ከሙስና አጸዳለሁ በማለት ቃል ሰጠ፡፡መለስ እራሱ ያዋቀረው አጣሪ ኮሚሽን ደሞ በመለስ የሚታዘዙት የጦር አባላት ከሱ በተሰጠ መመርያ መሰረት 193 ንጹሃንና በሰላማዊ መንገድ ባዶ እጃቸውን ለአቤቱታ የወጡ ኢትዮጵያዊያንን ጨፈጨፉ፤ከ800 በላይ የሁኑትን አቆሰሉ፤ከ30000 በላይ የሆኑትን ወደ ወህኒ አወረዱ፡፡
ከ2010 ምርጫ በፊት ሃገሪቱን ለጎበኘው ከፍተኛ የአሜሪካ ቡድን መለስ፤‹‹ምርጫውን የሚሞግቱ›› ሃይላትን ምን እንደሚያደርጋቸው በግልጽ ነገሯቸዋል፡፡ ተቃዋሚዎች የምርጨውን ውጤት ላለመቀበል ሕዝብን ለማነሳሳት ቢሞክሩ ባለ በሌለ ሃይላችን ተጠቅመን ልካቸውን እናሳያቸዋለን፡፡ እንደብርቱካን ሚዴቅሳ በወህኒ አንዲጠወልጉ እናደርጋቸዋለን፡፡ ብሏቸው ነበር፡፡ምርጫን ላለመቀበል አቤቱታ የሚያቀርቡትን እንዲህ ለማድረግ ከወሰነ ስልጣን በቃህ ልቀቅ ለማለት ቢነሱ ምን እንደሚያደርግ ከዚህ መገመት ይቻላል፡፡
በ2010 ኦማር በሺርም ልክ ይህንኑ ነው ያደረገው፤ ለማድረግም አቅዶት የነበረው፡፡በ2008 ሮበርት ሙጋቤም ከዚህ የተለየ አልሆነም፡፡የኬንያው ኪባኪም የቀደሙትን አራፕሞይን እንዳልወቀሰና እንዳልከሰሰ ሁሉ፤ እራሱም ምርጫውን በዚያው በተወቃሹ ስልት አስኬደው፡፡
በአፍሪካ የሚታየው የሙስና ሁኔታ እጅጉን አሳፋሪና አሳዛኝም ነው፡፡ ገዚዎች ለህዝቡ የረሃብ ማቅለያ ተብሎ በእርጥባን መልክ የሚመጣውን ሳይቀር ነው የሚሰርቁት፡፡ከሕዝቡ የዘረፉትን መልሰው አርዳታውን ወደ ሰጠው ሃገር ባንክ በስማቸው በማስቀመጥ ይከብሩበታል፡፡የቀድሞው የናይጄርያ ፕሬዚዳንት ሳኒ አባቻ በስዊስ መንግስት በህግ የወንጀለኛ ቡድን አባልነቱ የታወቀው ከሃገሩና ሕዝብ ላይ 500 ሚሊዮን የስዊስ ፍራንክ መስረቁን ይፋ አድረጓል፡፡
በቅርቡም የቱኒዚያው ቤን አሊ፤ የግብጹ ሙባረክ፤ በስዊዘርላንድ በመቶ ሚሊዮንና ከዚያም በላይ ገንዘብ እንደታገደባቸው ሰምተናል፡፡የአፍሪካን ሕዝብ ሲገዙና ሲዘርፉ የነበሩት ሌሎች ደግሞ፤ የናይጄሪያው ባባንጊዳ፤የጊኒው ላንሳን ኮንቴ፤የቶጎው ኢያዴማ፤ የጋቦን ቦንጎ፤የኤኳቶርያል ጊኒው ኦቢያንግ አንጉማ፤የቡርኪና ፋሶው ኮምፓዎሬ የኮንጎ ብራዛቪል ዴኒስ ሳሶ ኢንጉሶ ይገኙበታል፡፡
ነፍስ አባቶችና አፍሪካዊያን ተጎግራሲስ
የአፍሪካ መሪዎች ተግባር ሥሪቱ ሙስና ነው፡፡የአፈሪካ ገዢዎች ስላጣናቸውን የሙጢኝ ብለው ጨምድደው የሚይዙት የሃገራቸውን ንብረትና ሃብት ለመስረቅ በማሰባቸው ነው፡፡እነዚህ የአፍሪካ ‹‹ገዢዎች››የወንጀለኞች ነፍስ አባቶች አለያም የወንጀለኞች ቁንጮ አለቆች ናቸው፡፡እንደማንኛውም የተደራጀ የወንጀል ድርጅት ሁሉ የአፍሪካ ተጎግራሲዎች የፓርቲያቸውን ስርአት፤ቢሮክራሲውን፤ወታደሮቻቸውንና፤የፖሊስ ሃይላቸውን ያካበቱትን የሃብት መንግስታቸ መውን አደላድሎ ለማቆየት ይጠቀሙበታል፡፡
የአሜሪካን መንግስት ለመጀመርያ ጊዜ ‹‹የተዘረፈን ንብረት›› የማስመለስ ፕሮገራም ባወጣበት ወቅት ዋናው አቃቤ ህግ ኤሪክ ሆልደር ለአንድ ሙስናን ለሚዋጋ ድርጅት ሳይሆን በካምፓላ በተካሄደው የአፍሪካ አንድነት መደበኛ ጉባኤ ላይ በመገኘት ነበር የተናገረው፡፡ሆልደር ለተሰብሳቢዎቹ የአፍሪካ ተግታቶሮች፤ ‹‹ዛሬ በመሃከላችሁ ተገኝቼ የአሜሪካን መንግስት ያዋቀረውን አዲስ ከሕዝብና ከሃገር የተዘረፈን ንብረት የማስመለስና ለባለቤቶቹና ለታቀደለት ተግባር እንዲውል የማድረግ ደንብ ስናገር በደስታ ነው፡፡ትኩረታቸውን በዚህ ጉዳይ ላይ የሚያደርጉ አቃቤያን አሰባስበን አሰልፈናል፡፡የነዚህ አቃቤያን ተግባርም እነዚህን የተዘረፉ ንብረቶችና የሃገርና የሕዝብ ሃብት ተከታትሎ በማስመለስና ዘራፊዎቹንም ለፍርድ ለማቅረብ መንቀሳቀስ ነው፡፡ በዚህም የህዝብንና ሃገርን ንበረት በመጠበቅ ዘራፊዎቹንም ለሕግ ማቅረብ እንችላለን፡፡
ሆልደር ይህን ንግግር ያደረገው በአሜሪካና በሌሎችም ዓለማት ለተሰማሩት የማፍያ ጥርቅሞች ሳይሆን በካምፓላ አዳራሽ ለተሰበሰቡት የዓለም የማፍያ ስብስብ ተመሳሳይ ለሆኑት የአፍሪካዎቹ ገዢዎች ነበር፡፡
እልቂት፡- የተግታቶሮች የኑክሌር ማስፈራርያ
ተግታተሮች ስልጣናቸውን ለማቆየትና ወንበራቸውን ላለማስወሰድ የሚጠቀሙበት የተለመደ ማስፈራሪያቸው፤‹‹የማያልቅ እልቂት›› በማለት የሚለፍፉት ውትወታቸው ነው፡፡ከዘመናት በኋላ ከስልጣናቸው የተነሱ እንደሆነ፤‹‹ሰማይ ተደፍቶ ምድርም ተሰንጥቃ ሕዝቡን ትውጣለች›› የሚለው ማስፈራሪያቸው ነው፡፡
ተግታቶሮች በሕዝቡ ህሊና ውስጥ ፍርሃትን ዘርተው ወኔ ቢስ በማድረግ፤ ግንዛቤውን እንዲያጣ፤ ሚዛናዊ አመለካከቱ እንዲጠፋበት በማድረግ ስነልቡናውን ይሰርቁታል፡፡ የጋዳፊ ስሪት የሆነው ልጁም አባቱና ቤተሰቡ ከተነኩ ‹‹ሃገሪቱ ልትወጣው ወደማትችለው የእርስ በርስ ጦርነት ትገባለች የሃገሪቱም መዋቅር እስከመጨረሻው ይፈራርሳል›› በማለት ነበር የማስፈራርያ ጩኸቱን ያንባረቀው፡፡ በዚህም አልበቃውም፡፡ ‹‹ሊቢያ የደም ጎርፍ የሚፈስባት ትሆናለች፤ይህ የተቃዋሚዎች እንቅስቃሴ ነው የሊቢያን አንድነት ለማጥፋት የተነሱ የተገንጣዮች እንቅስቃሴ ነው፤ እስከመጨረሻው ጥይት እንዋጋለን፤ እያንዳምዱን ተቃዋሚ እናጠፋለን፤ ሁሉም መሳርያ ይዞ ከተነሳም የሲቪል ጦርነት ይሆንና እርስ በርስ እንጨራረሳለን›› አለ፡፡
መለስም ስለዘር ማጥፋትና እልቂት በተደጋጋሚ ተናግሯል፡፡ በ2005 ለመታዘብ የተሰማሩት የአውሮፓ ህብረት አባላት መለስንና አጋር አገልጋዮቹን ስለእርስ በርስ መተላለቅ በከረረ መልኩ ሕዝቡ ህሊና ውስጥ በመክተት እርስ በርስ እንዲጫረስ እያዘጋጁት እንደነበር መስክረዋል፡፡
የመጨረሻው የምርጫ ክርክር እጅጉን በተጋጋለበት ሰአት ፓርቲዎቹ እርስ በርስ የምርጫው ህግና ደንብ መሰረቱ እየተናጋ እንደሆነ በተደጋጋሚ በማንሳት ተወነጃጀሉ፡፡የዚህ የከፋው ውንጀላ ደሞ የተሰማው በሚያዝያ 15 በመለስና በአዲሱ ለገሰ መራራ የሆነውን የኢንተርሃምዌይን እልቂት ምሳሌ በማድረግና ተቃዋሚዎችን የዚያ አካል መልእክተኝች በማለት ውንጀላ ሰነዘሩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግንቦት 5 መግለጫ ላይ የቅንጅትን ፓርቲ በተመሳሳይ መልኩ ኢንተርሃምዌይን በሃገሪቱ ላይ ሊተገብሩ የተሰለፉ በማለት ለፈፉ፡፡ የኢህአዴግ ገዢ ፓርቲም በነጻ በሚጠቀምበት የመገናኛ ቅስቀሳው ላይ ይህንኑ ደገመው፡፡ አንድ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ያውም ‹‹እንከን የለሽ›› የሆነ ምርጫ አካሂዳለሁ ከሚል አካል ጨርሶ የማይጠበቅ ነበር፡፡
መለስን የማስፈራርያ ዲስኩር በሃገሩ ሰዎች ላይ ለማድረግ የሚቀድመው ጨርሶ የለም፡፡ሲናገርም ይሉኝታም፤ ስነስርአትና ኢትዮጵያዊ ጨዋነትም አያውቅም፡፡ አንድ ሃገርን እገዛለሁ ከሚል ሰው የማይጠበቀውን ንግግር ሲያደርግ የሚሰማው ኢትዮጵያዊ ነው የሚሸማቀቀውና የሚያፍረው እንጂ፤ ለመለስ ደንታም አይሰጠው፡፡ይህ ደግሞ በሃገር ውስጥ ብቻ ሳይወሰን ድንበር አልፎም የሚደመጥ ነው፡፡
የአሜሪካን ድምጽ ሬዲዮን ወደሃገር ውስጥ በሚያስተላልፈው ዜናና የተለያየ ፕሮግራም የተነሳ መለስ፤ የአሜሪካን ድምጽ ሬዲዮን በ1944 በሩዋንዳ የተፈጸመውን እልቂት ካነሳሳው ሬዲዮ ሚሌ ኮሊነስ ጋር አመሳሰሎ መግለጫ ሲሰጥ እየተሸማቀቁ ያዳመጡት ኢትዮጵያዊያን ነበሩ፡፡
የአፍሪካ ገዢዎች ከአንድ እናት ማህጸን የወጡ መንትዮች ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ ዘረፋቸው አንድ አይነት፤ ግድያቸው ተመሳሳይ፤ ክህደታቸው አንድ አይነት ሁለንተናቸው አንድ ስሪት ነው፡፡ ልዩነታቸው በተለያየ ሀገር መኖራቸው እንጂ አንድ ናቸው፡፡ልዩነታቸውን ተግባራቸው ያቀራርበዋል፡፡ የክህደት፤ ሸፍጥ፤ ማህደሮች ናቸው