ለኰሎምብስና ለአካባቢው ነዋሪዎች

ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዉያኖች።

ጉዳዩ፦ ለአምስተኛ ጊዜ የአምባገነኑ የመለሰ ዜናዊ መንግስት፤ ለማፈን የሚጥረዉንና ለኢትዮጵያ ህዝብ ብቸኛ የመረጃ ምንጭ የሆነዉን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቭዥን (ESAT) ስለመርዳት ነው።

ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርነው አምባገነኑ የይህአደግ መንግስት የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን (ESAT) ለማፈን የኢትዮጵያ ህዝብ የመረጃ ጥማቱ እንዳያገኝ የሚያደርገዉን እንቅስቃሴ ለማቆምና “ኢሳት” ተጠናክሮ ለኢትዮጵያ ህዝብ የመረጃ ምንጭ እንዲሆን የበኩላችን ድርሻ እንወጣ።

ስለ ወቅታዊ የሀገር ጉዳይ ማብራሪያ ይሰጣል።

የአካባቢው የኢሳት ኮሚቴ እና ተጋባዥ እንግዶችም ንግግር ያደርጋሉ።

በዚህው ዕለት ተገኝተን ስለ ሀገራችንና በሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታዎች እየተወያየን በገንዘብ፥ በዕዉቀት በምንችለው ሁሉ ኢሳትን ለመርዳት ኢትዮጵያዊ ግዴታችን ለመወጣት ፌብሩዋሪ 26 እንድንገኝ የኢሳት አስተባባሪ ኮሚቴ ጥሪው ያስተላልፋል።

ቦታ፡ 402 N.Hamilton
ሰዓት፡2፡00PM
ቀን፡ February 26/2011

“ኢሳትን በመደገፍ ኢትዮጵያንና ህዝቧን እንታደግ።”

“ኢሳትን መርዳት በየቤትዎ የሚደርስ የቴሌቭዥን ስርጭት ከማግኘት በላይ የገዘፈ ትርጉም አለው።ኢሳትን በመደገፍ ባስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኝን ሀገርንና ህዝብን መታደግ ነው።”

የኢሳት የነጻነት መንፈስ ለዘላለም ይኑር!