‹‹ለዲያስፖራው የተመደበው …›› ክፍል 2
ከጆኒ ዋሽንግተን ዲሲ
የአሣ ግማቱ ከአናቱ
እንዲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆሻሻውን ሥራ የሚሰሩለት፤የራሳቸው ማንነት አለያም ምንነት የሌላቸውን መሰብሰቡን ከዋናው መሪያቸው ከአቶ መለስ ዜናዊ ከተሰጣቸው የአጭርም የረጂም ጊዜ ባዶ ትምህርታቸው ያካበቱት ነው፡፡
አቶ መለስ ከጫካ መጥተው፤የማያውቁትን ግን ሲመኙትና ባልደረቦቻቸውን እየገደሉና አያባረሩ፤ ለስደት እየዳረጉ ያገኙትን የቁንጮ ግፈኛ ገዢነታቸውን በሳቸው እምነት ለዝንተ ዓለም ይዘው ለመቆየት የሚያስችላቸውን ሸፋፋ ዘዴ ሲቀይሱ የሚከተሉት ጭባ መንገዳቸው በእውቀትም፤ በችሎታም፤በአመለካከትም፤ከሳቸው ያነሱትን ሰብስበው የሰጡትን የሚቀበል በማድረግ አሰልጥኖ ማሰልፍን ነው፡፡
አቶ መለስ ባነጠሱ ቁጥር በፓርላማ፤ በየመስሪያ ቤቱ፤ በየሚኒስትሩ መስሪያ ቤት፤ በየጦሩ ካምፕ፤ በፖሊስ ኮሚሽን ስር ያሉት፤በስለለው መዋቅር ያተሰገሰጉት፤በየወያኔ የግል ይንግድ ድርጅቶች ውስጥ የሚያሽቃብጡት፤እና በተለያዩ እዚህ ውስጥ በላተጠቀሱት ቦታዎች ያሉ ሁሉ ንፍጣቸው ይዝረበረባል፡፡ጌታቸው አንድ ቦታ እንዳነጠሱም ይገምታሉ፡፡
ከዚህ በመነሳት ነው፤መለስ ለእኩይ ተግባራቸው ማስፈጸሚያ አለያም የማይሆነውን ለኢትዮጵያ ይሆናል፤ ብለው ካለጥናት፤ ካለእውቀት፤ ካለችሎታ አምጥተው በሕዝቡ ላይ እንዲጭኑበት የሚያዙት ከላይ የተጠቀሱትን የሰጧቸውን የሚቀበሉትን ሕሊና ቢሶች ነው፡፡
ሕሊና ቢሱ ደሞ መቼም ቀፎ እራስ ነውና የማያውቀውን እንደሚያውቅ፤ የማይችለውን እንደሚችል አድርገው የፈጽም መመርያ ስለሚሰጡት፤ ለምን፤ እንዴት ብሎ ነገር በውስጡ ስለሌለው ያን የተባለውን ወስዶ በሕዝብ ላይ ይጭናል፡፡ሰራ አልሰራ የመለስም ሆነ የተላላኪው ጉዳይ አይደለም፤ የሚፈለገው ይህን አደረጉ እንጂ ምን ውጤት አስገኘ አይደለምና፡፡
ይህንንም የሚያስደርጉት ዓለም አቀፊ ሕብረተሰብ እንዲያየውና አደረጉ ብሎ እንዲያደንቅላቸው ነው፡፡ አብዛኛው የዓለም አቀፉ ሕበረተሰብ አባልም ቢሆን የመለስን እኩይነት፤ የተግባራቸውን ባዶነት፤የሕሩንምዝቡን በባዶ ተስፋ መታለልና ቢናገርም ሊደርስበት የሚችለውን ችግር አበክረው ቢያውቁትም ለራሳቸው በሃገር ውስጥ ለመቆየትና የማይፈለግ ተብለው በመባረር ሊደርስባቸው በሚችለው የሃገራቸው መስሪያቤት ችግር ጋር በማመዛዘን አይተው እንዳላዩ አውቀው እንደማያውቁ ማለፍን ለመቆያቸው የፈቃድ ወረቀት አድርገው ያዩትልና ትንፍሽ አይሉም፡፡ መለስም ይህንን ዝምታና አርፎ መቀመጥ በዓለም አቀፉ ሕብረተሰብ ውስጥ አጠናክሮ ለማረጋገጥ ትንሽ ትንሽ እንኳን እውነት የተናገሩትን ከሃገር ውስጥ በማባረርና ስማ በማጥፋት፤ በዝምታ ያለፉትን ደሞ የሥራ ዘመናቸውን ጨርሰው ሲሄዱ ወፈር ያሉ ስጦታዎችን በመሸለም፤ ከመመለሳቸውም በፊት በሃገር ውስጥ ባሉበት ዘመን ለድሎታቸውን ለደስታቸው አስፈላጊው ሁሉ እንዲደረግላቸው በማድረግ ጠፍረው ይይዟቸዋል፡፡ እነሱም አንድ ጊዜ ማኖ ከነኩ በኋላ ምንም ቢሆን ትንፋሽ አይሉም፡፡ ለመተንፈስ ገና ሃሰቡ እንዳላቸው ሲታወቅም በመለስ በኩል ስለተሰጣቸው ስጦታና ስለተዘጋጀላቸው መዝናኛ ሁኔታ እንዲያስታውሱት ስለሚደረጉ ዝምታን ይመርጣሉ፡፡
ባለፈው መጣጥፌ ለዲያስፖራው ስለተሸመው አደራዳሪና ዲያስፖራውን አሳምኖና አስፈላጊውን እንደሚደረገላቸው በመግለጽግ ተቃውሟቸውን ትተዉ ወደ ሃገር እንዲመጡ ለማድረግ የተቋቋመው ኮቴ ሊቀመንበር ይስሃቅ አብዱላሂ፤ ጸሃፊ ደሞ ያው የታወቀው በኖረበት መንግሥት ሁሉ መቀላመድ ባህሉ የሆነውን ታደለ ይመርን በተመለከተ የማውቀውን እውነት አቅርቤ ነበር፡፡ ዛሬ ደሞ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተሰጠኝ ብሎ ስለሚያስወራው ‹‹የሠላም ራዕይ›› አምባሳደር ማዕረጉ ሰምቼ የተገረምኩበትን ላድርሳችሁ ብዬ ነው፡፡
አክስቴ በሚቀጥለው የፋሲካ በዓል ላይ ወደ ኢየሩሳሌም ትሄዳለችና በጠቅላላ ጉባኤው ስብሰባ ላይ ልትገኝ ሄዳ እንደነበር ወደ ሃገር ቤት ስደውል ተነገረኝ፡፡እኔም ስትመጣ እደውልላታለሁ ብዬ ስልኬን ዘጋሁ፡፡ያን ስብሰባ የሚመራው የያው ታደለ ይመር እንደሆነ አስቀድማ ነግራኝ ስለነበር ምን እንዳለም ለመስማት ልቤ ለወሬ ቆመ፡፡አውቀዋለኋ!!
ወደ ማታ ገደማ ደግሜ ስደውል አክስቴን አገኘኋትና ‹‹ቅድም ደውዬ ነበር አጣሁሽ ደህና ነሽ አታለም›› ስላት፤ ‹‹ኢሩሳሌም ስብሰባ ሄጄ ነዋ›› አለችኝ፡፡ ‹‹ምን አሏችሁ›› ስላት አይ የሂሳብ ሪፖርት ሰማን ደሞ ስለሆቴላችን ነገሩን…ደሞ ያ አቶ ታደለ ተሸመ እኮ›› ስትለኝ፤ አለነገሩ ጀጆሮዬን አላሳከከኝም አልኩ፡፡ ወዲያው ‹‹ምን ሹመት›› ስላት ‹‹የሠላም አምባሳደር ተብያለሁና ይሀንኑ አሳውቁልኝ ተብዬ ነው›› ብለው የቦርዱ ሊቀመንበር ጨዋ ሰው ናቸው እንዲህ እንዳይመስሉ እሳቸው፡፡ አቶ ዓለማየሁ ናቸው እና ነገሩን›› ነገሩ ግራ ስለሆነብኝ የምን ሰላም›› ስላት ‹‹የሰላም ራዕይ አምባሳደር አሉ ምን አውቄ፤ የዘመኑን ቋንቋ ለማወቅ አንዳንድ ጊዜ ት/ቤት መግባት ሳያስፈልግ አይቀርም እኮ›› ብላ ሳቀች፡፡ ወዲያው ሰላምታዬን አቀራርቤ ስለ መንገዱ የሚያስፈልጋትን ተነጋግረን ተለያየን፡፡
ሹመቱ የሠላም ራዕይ አምባሳደር›› የተባለው እንግዲህ ቀደም ብሎ ሲዘባርቅበት በነበረው የዲያስፖራው ጉዳይ ኮሚቴ ጸሃፊነቱ ሳቢያ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተሰጠው መሆኑ ነው፡፡ ይህን ደሞ በራሴ ማፈላለጊያ ቀመር ሳስበው ሹመቱ የተባለውን እንዲህ አገኘሁት፡፡
1. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤቱና ሚኒስትሩ የዚህ ጉዳይ ፈጻሚ ቢሆኑ ውጤቱ ምንም ይሁን ምንም ሌላው ቢቀር የንግዱን ሕብረተሰብ ስለሚያሳምኑልንና ለዚህ የሚሆነውን የኮሚቴውን የጉዞና ሌላም ወጪ አፍንጫውን እየሰነጉ በማስፈራራትና በማስገደድ ስለሚያስከፍሉት ለኛ አደረግን ለማለት ጠቃሚ ነው ብለው በማሰብ በኮሚቴው ውስጥ የተካተቱትን ቅጥር ተዋጊዎች በጅምላ ‹‹የሰላም ራዕይ አምባሳደሮች›› ብለው ወረቀት ሰጥተዋቸዋል
2. የኮሚቴው ስብሰባና ኮሚቴው ሊያደርግ የሚገባውን፤ እስከ ዛሬም ስለተደረገው ሂደት ለመነጋገር በሚኒስትሩ መስሪያ ቤት ሲገኙና ስብሰባው ሲጀመር ምናልባት ሰብሳቢው ሲደልላቸው ‹‹እናንት የሰላም ራዕይ አምባሳደሮች!›› ብሎ እንደመግቢያ ንግግር ስለተጠቀመበት አጅሬ ታደለ ሆዬ ‹‹አምባሳደር ተብያለሁ›› ብሎ ሊሆን ይችላል፡፡
ያም ሆነ ይህ ‹‹አምባሳደር››ታደለ ለስሙ ማንጠልጠያ አገኘ፡፡ እንግዲህ በሃገራችን ባደረጉት ከፍተኛና ዓለማ አቀፋዊ አስተዋጽኦ ‹‹የዓለም ሎውሬት›› አለያም በሚሰጣቸው የሙያ እውቅና ‹‹የክብር ዶክትሬት ሲሰጣቸው ሰምቷልና እራሱን በዚያ ደረጃ ለማስቀመጥ የሚያበቃ ቀርቶ ፍላጩም እውቀት ስለሌለው በዚህ ማካካሱ ነው፡፡በነገራችን ላይ ታደለ ትምህርታዊ ብቃቱ የ3ኛ ክፍል በመሆኑ፤የተባለውን ተቀብሎ እንደአለብላቢት ማክለብለብ እንጂ ሌላ እውቀትም ችሎታም የለውም፡፡ በዚህ ጨርሶ አይታማም፡፡ አቶ መለስና ጭፍሮቻቸው ደሞ እነዲህ አይነቶቹን ሰዎች እንደእቃ መጠቀምን ያውቁበታል፡፡ እንዲህ በድንገት ወደሕዝብ አይን የገቡ ደካሞች ደፋርና ይሉኝታ ቢስ ስለሆኑ ለሚያደርጉት ሁሉ የሚያስቡበት ህሊና ስለሌላቸው ታስቦ፤ተወስኖ፤አልቆ ነው የሚሰጣቸው፡፡
የዚሁ ኮሚቴም ሰብሳቢ ተብሎ የተጎለተው ሌላው ‹‹አምባሳደር›› ይስሃቅም ቢሆን እርግጥ ትምህርት ያለው ቢሆንም ግን በራሱ ማሰብና በራሱ ችሎታ መመራት ያስቸግረዋል፡፡ በራሱ የሚያስበውም ሆነ በራሱ ችሎታ መመራትን የሚያውቀው በሸር ሃብት ለማግኘት፤ አለሁ ብሎ ሳይጠራ አቤት ለማለት፤ጥቅሙን ሳያስነካ፤ግን የንግዱን ሕብረተሰብ እየጠቆመና እያሰለፈ መዋጮ እንዲያደርጉ፤ለወያኔ ፓርቲ ድጋፍ እንዲሰጡ፤ ግብዣ በንግዱ ሕብረተሰብ ስም እየተዘጋጀ ወደማያውቁት አጀንዳ እንዲገቡና አስፈላጊ ነው ተብሎ የተጣለባቸውን መዋጮ በግዴታ እንዲከፍሉ ለማስደረግ ሲጥር ብቻ ነው፡፡ ይህን ደሞ በተደጋጋሚ ሲያደርግ ታይቷል፡፡ በ97 ምርጫም ሆነ ባለፈው የቅርቡ ምርጫ፤ዋናው አቀንቃኝ አላሙዲን ጋር ተሰልፎ ነጋዴውን ያስበዘበዘውና ‹‹ለምን?›› የሚል ጥያቄ ያነሱትንም ለእስር የዳረገው ይስሃቅ አብዱላሂ ነው፡፡
እነዚህ ናቸው እንግዲህ ‹‹የሠላም ራዕይ አምባሳደር›› የሚል ተቀጥላ የተሰጣቸው፡፡ እነዚህ ናቸው፤የዲያስፖራውን ጉዳይ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ሆነው የሚያስፈጽሙት፡፡ እነዚህ ናቸው ዲያስፖራው ዓላማውን ትቶ፤ራዕዩን ዘንግቶ ከወያኔ ጋር እንዲቆም በየሃገሩ በመዞር ሊያግባቡ እቅድ ያወጡት፡፡
ወያኔ ግራ ገብቶት ሜዳው ሁሉ ገደል በሆነበት ሰአት፤በቅድሚያ ክህደቱ አያሌውን ‹‹በታትን፤ አጣላ፤ አጋጭ›› ብሎ ልኮ ያ ሳይሳካ ቀረ፡፡ ክህደቱም ማጣፊያው ሲያጥረው፤ ወደ ሰለጠነበት ስድብና ስም ማጥፋት ገባ፤ሆኖም እውነት አሸነፈችውና ከሄደበት የውርደት ካባውን ተከናንቦ ወጣ፡፡የነዚህም የተልእኮ ውጤት አስቀድሞ ማብቂያው እየታየ ነው፡፡
ለዛሬው በዚህ ላብቃና፤ቀጣዩን ከአዲስ አበባ ኢሩሳሌም አክስቴ ሄዳ ስትመለስ አቀርባለሁ