ህብረተሰቡ ወያኔ በሚጠይቀው መዋጮ ተማሯል
የወያኔ/ኢህአዴግ አገዛዝ ያወጣውን የአምስት አመት የዕድገትና የትራንስሮሜሽን እቅድ ለማሳካት በሚል እየሄደት ያለው መንገድ ህብረተሰቡን እያማረረ ነው፡፡ መንግስት እቅዱን ለማሳካት ከሚያስችለው የገንዝብ መጠን ውስጥ 65 በመቶ ያህል የሚሆነውን ከህዝብ ለመሰብሰብ ማቀዱ ይታወሳል፡፡ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ በሰፊው በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኘው የኢህአዴግ መንግስት ከህረተሰቡ እየጠየቀ የሚገኘው መዋጮ የህብረተሰቡን አቅም ያላገናዘበ መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡
በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡን የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑ አንድ አዛውንት እንደገለጹት ዕቅዱን ለማሳካት በሚል በዚህ ወቅት መንግስት ከአንድ ቤተሰብ እስከ 1000.00 ብር የሚደርስ መዋጮ ይጠይቃል፡፡ አዛውንቱ ጨምረው “መዋጮው በኑሮ ውድነቱ ላይ ተደምሮ ህይወታችንን እያናጋው ይገኛል፡፡ ይህንን ሀቅ በግልፅ ለመናገር የደፈረ ሰው እንደ ፀረ ልማት ስለሚታይ ጾማችንን እያደርንም ቢሆን እያዋጣን ነው፡፡” በማለት ሁኔታውን ገልፀዋል፡፡
የአዛውንቱንና የሌሎችም ነዋሪዎችን ምሬት የበለጠ የከፋ ያደረገው ደግሞ የሚሰበሰቡ ገንዘቦች ለግለሰቦች ጥቅም እየዋሉ መሆናቸው ነው፡፡ የዜና አገልግሎት ከፍላችን መረጃዎች እንደሚጠቀሙት እስካሁን የአራዳ ክ/ከተማ 8 ቀጠና አስተባባሪዎችና 4 የኮልፌ ቀራንዮ የቀጠና አስተባባሪዎች ከህብረተሰቡ የተሰበሰበውን መዋጮ ይዘው ተሰውረዋል፡፡ የተጠቀሰውን ገንዘብ እንደያስቀርበት ስጋት የያዘው መንግስት የየወረዳ የጽ/ቤት ሀላፊዎችን ከስልጣን በማውረድ በአዲስ በመተካት ላይ ይገኛል፡፡
ለዝግጅት ከፍላችን ሀሳባቸውን የገለጹ ነዋሪዎች እንደሚያስረዱት ከሆነ ግን አዲሶቹ ተሹዋሚዎችም ቢሆኑ በሰነምግባራቸውና ብቃታቸው ሳይሆን የፓለቲካ ታማኝነታቸው እየታየ ወደ ስልጣን የመጡ በመሆናቸው ከበፊቱ በተሻለ ታማኝ ይሆናሉ ተብሎ አይጠበቅም፡፡