10ሩ የጥሩ መሪ መመዘኛዎችና መለስ ዜናዊ

1 በራስ መተማመን

በራሳቸው የሚተማመኑ ሰዎች የሚመረጡና የሚያኮሩ ተአማኒነትም ያላቸው የሚቀናባቸውም ናቸው፡፡ይሀ ደግሞ በአመራር ላይ ላሉት እጅጉን የሚያስፈልግና ሊኖራቸውም የሚገባ ነው፡፡አንድ በራስ የመተማመን ብቃት ያለው ሰው፤ሌሎችም በራሳቸው የሚተማመኑበት ብቃት እንዲያዳብሩ ያነሳሳል፡፡አንድ መሪ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሲያደርግም ሆነ በድርጅታዊ የሥራ ሂደት በራስ መተማመን ያለውና ያን ደግሞ በተግባር የሚያሳይ መሪ አብረውት ካሉት ተአማኒነትን ያገኛል፤ለድርጅታዊ ሥራውም ሂደት ረዳት ነው፡፡

በሳል መሪ
ይህን በሚገባ የሚያሟላ ሲሆን ከእድሜ አኳያም ከስህተት ሳይሆን በሌሎች ስት ተምሮ ያን ላለመድገም ጥንቃቄ እያደረገ በራሱ መተማመንን የበለጠ ለያጎለብት መቻሉን በተደጋጋሚ ያረጋግጣል፡፡

መለስ
በጭራሽ በራስ መተማመን ብሎ ነገር ስላልፈጠረባቸው መተማመኛቸው ጠብመንጃ፤በጦሩ ጉያ ተሸጉጠው ሃገርና ሕዝብን ለእልቂት ለረሃብ ለመከራ የሚያበቁበትን ቆመውም ተቀምጠው ተኝተውም ማውጠንጠን ነው፡፡

አብረዋቸው ያሉትም በራሳቸው እንዳይተማመኑ፤ በሳቸው እንዲያምኑ፤ከሳቸው ቃልና መመርያ እንዳይወጡ፤እሳቸው ያሉት ሁሉ የጻድቅ ቃል እንደሆነ እንዲቀበሉ ስለሚያደርጉ ቋሚ አገልጋይ አድርገዋቸዋልና በራሳቸው የማይተማመኑ ግኡዛን ናቸው

2 ተነሳሽነት

ግልጽ የሆነና በእውነት ላይ የተመሰረተ ተነሳሽነት ተላላፊ ነው፡፡በመሆኑም ተነሳሽ የሆኑ መሪዎችም በሥራቸው ላይ ተሳታፊ የሆኑትን የድርጅታቸውን አባላት በማነሳሳትና ለዘለቄታውም በተነሳሽነት እንዲለከፉ ማድረግ ለራሱም አመራር ሆነ ለድርጅቱ ከፍተኛ ውጤት የሚያስገን ሲሆን በተለይ አመራር ላይ ያለውን ሰው እንደፈላጭ ቆርጭ አለቃ ሳይሆን እንደ ሥራ ባልደረባ እንዲቀበሉትና ለአንድ ዓላማ ለአንድ ግብ መቆማቸውን ያረጋግጥላቸዋል፡፡

በሳል መሪ የማንንም ሃሳብ ሳየይቅ የምያዳምጥና ጠቃሚና ጎጂውን የሚለይ ብቻ ሲሆን በራሱ ተነሳሽነት ስላለው ይህንንም የተነሳሽነት ባህል አብረውት ላሉት ለማስተላለፍ ብቃቱ የታየና የተፈተነበት ነው

መለስ ተነሳሽነት ሲባል የሚታያቸው ጠመንጃ ማስወልወል፤ ጥይት ማስጉረስ፤ ለመተኮስ ማነሳሳት፤ ለማስገደል ማኮብኮብ ነው፡፡ የመለስ ተነሳሽነት በአካባቢያቸው የኮለኮሏቸውን ጅሬዎቻቸውን ከባርነት ቀንበር እንዳይላቀቁ ሃጢያታቸውን በማብዛት ማስፈራራት፤የስም ታርጋ እየለጠፉ ማዋረድ ነው፡፡ ተነሳሽነት ለሳቸው ያለው ትርጉም ከኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ጥፋትና ርግማን ጋር የተያያዘ ነው

3 ሚዛናነዊነት

ሚዛናዊ የሆኑ መሪዎች ምንግዜም የሕዝብ አመኔታ አላቸው፡፡ስለዚህም ሚዛናዊ የሆኑ መሪዎች ከሁሉም ጋር ያላቸው መሪዎች ሥራቸውን ያከናውናሉ እንጂ በመተዋወቅ ወይም በመቀራረብ፤ አለያም አብረው በመብላትና በመጠጣት ላይ ያተኮረ ሥራ አያካሂዱም፡፡የእያንዳንዱን አብረውት ያሉትን እንደብስለትና ቅለቱ ሥራቸውን ይለካል እንጂ አድሎአዊ አይሆንም

በሳል መሪ ዓላማው ከራሱ በፊትና በላይ ሕዝብና ሃገርን ማስቀደም ስለሆነ፤ አደራውንም የተቀበለውና መልሶም የሚያስረክበው ለሕዝብ መሆኑን ስለሚያምን ከምንም በፊት ሚዛናዊነት መመርያው ነው

መለስ ሚዛናዊነት ሊኖራቸው ቀርቶ በአጠገባቸውም አልፎ አያውቅ፡፡ ለመለስ ሚዛናዊነት ማለት ወርቅ መመዘኛው ሚዛን፤ ብር መቁጠርያው ሚዛን፤ ጥቅማቸውን መለኪያው ሚዛን ነው፡፡ ለሳቸው ሚዛናዊነት ማለት እራሳቸውን ከፊት ከፊት አገልጋዮቻቸውን ኋላ ኋላ እያስከተሉ ሃገርን ወደማትወጣበት መከራና ስቃይ ለማስገባት መመዘኛ እያወጡ ጥፋትን ማፋጠን ነው፡፡

በሳል መሪ አዳዲስ ባህሎችን የመቀበል ጉልበት አለው፤ ፍቃደኝነቱ አለው፤ለመማርም ዝግጁ ነው፤ሁሉን አወቅ ንፍገትም የለውምና በራሱ የፈጠራ ችሎታ ብቻ ሳይወሰን የሌሎችን ጠቃሚ አዳዲስ ፈጠራዎችን ተቀብሎ በማዛመድ ለመተግበር ዝግጁ ነው፡፡

4 የፈጠራ ችሎታ

ጠንካራ መሪዎች ዘወትር አዳዲስ ሃሳብ ይፈጥራሉ፡፡ሁል ጊዜ ከተለመደው ውጪ ያስባሉ፡፡ስለዚህም የሚያጋጥሟቸውን ችግር ሁሉ እያሸነፉ ቀደም ሲል ያልታየውን መንገድም ይተልማል፡፡

መለስ የፈጠራ ችሎታቸውን ማሳየት የሚፈልጉትና እምነታቸውም ስንት ሰው ተገደለልኝ፤ በአንድ ጥይት በርካታዋችን መጨረስ አችንዴት እንችል ይሆን፤ ለተራበው ጥይት፤ ለተጠማው መርዝ ለመጋት ነው ፈጠራቸውን የሚጠቀሙበት፡፡ ፈጠራ ሲባል ተንኮል ፈጠራ ሲባል አሲዳምነት ነው የሚታያቸው፡፡

5. ፍቃደኛነት

ጠንካራ መሪ ሁል ጊዜ አዳዲስ ሃሳቦችን ከሌሎች ለመቀበል ዝግጁ ነው፡፡ምንም እንኳን እነዚህ ሃሳቦች የመጨረሻ መፍትሄ ባያመጡም የሁሉም አባላት ተሳትፎ እንዲዳብር ስለሚረዱ ሃሳቦቹ ይደመጣሉ፡፡

በሳል መሪ በራሱ የሚተማመን በመሆኑ ከማንኛውም የአመራር አባልም ሆነ አባል የሚቀርበውን አዲስ ሃሳብ ይቀበላል፡፡ በራሱ መንገድ መስራት አለመስራቱን ይፈትናል፡፡ምንም እንኳን እነዚህ ሃሳቦች ጥቅም ላይ ባይውሉም ሃሳቦች በአባላት መሃል መተላለፉ ጠቀሜታው ከፍተኝ ነው ብሎ ስለሚያምን ሃሳቦችን አያገልም

መለስ ጆሯቸው ላይ የተኙ በመሆናቸው ከራሳቸው ንግግር ውጪ ሌላ አይሰሙም ቢሰሙም አይጥማቸው፡፡ለሳቸው አዲስ ሃሳብ ማለት እንደቤተ ተሞክሮ የሰው ልጅ የማይችለውን ለኢትዮጵያዊያን ለማሸከም ማቀድ ነው፡፡አዲስ ሃሳብ ለሳቸው በሌላው ሃገር ያልሰራውን በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ላይ በመሞከር የዓለምን ህዝብ ለማሳመን መሞከር ነው፡፡የሳቸው ፍቃደኝነት መሬትን ለባዕድ ለመስጠት፤ ድንበርን ለማስደፈር፤ ሰበብ እየፈለጉ ጠንካራ የፖለቲካ ተቀናቃኞቻቸውን ማሰር፤ ለስደት መዳረግ፤ መግደል ናቸው፡፡

6. ታማኝነት

ጥሩ መሪ ዘወትር ታማኝና በሁሉም መልኩ ጠንካራ ነው፡፡ይህን ካልሆነ ግን የሌሎችን እምነት አያገኙምና ሊመሩም አይችሉም፡፡ጥሩ መሪ በአባላቱ ለመሪነቱ ተቀባይነት ለሃሳቡ ተፈጻሚነት ውሁድ የሆነ እሺታ ይኖረዋል፡፡ጠንካራ መሪዎች የሌሎችን ፍላጎት በማወቅ ችግሩ የሚፈታበትን አብሮ ከህዝቡ ጋር ይተልማል፡፡

በሳል መሪ ምንግዜም ለቃሉ፤ ከሁሉም በላይ ግን ለሃገርና ለወገን ታማኝ መሆኑን ደጋግሞ ያረጋግጣል፡፡ስለዚህም አመኔታ ስላገኘ ለመሪነት ብቃት አለው፡፡ጠንካራ በመሆኑ የሌሎችን ሃሳብ ለማዳመጥና ለማወቅ ችግር የለበትም፡፡ የሚያጋጥመውንም ችግር ከሕዝቡ ጋር ሆኖ ለመፍታት ዝግጁ ነው፡፡

የመለስ ታማኝነት የሚለካው ለሱዳን በሚያቀርቡት የመሬት ዳረጎት፤በሶማልያ አለጉዳያቸው በመግባት ሶማሊያዎችን መጨረስ፤ በታማኝ ወታደሮቻቸው እያስገደዱ ማስደፈር፤ለኤርትራ የሚጥማትን ማደረግ፤የእርዳታ ለጋሽ ሃገሮችን የሙጢኝ በማለትና በማታለል በሚያደርጉት የዳረጎትና የመለማመጫ ፖለቲካ፤ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን በከፋ የግፍና የመከራ አለንጋ መግረፍና ህዝቡን እርስ በርሱ ማናቆር፤ሃገርና መቆራረስ ነው፡፡

7 ትኩረት

ጠንካራ መሪዎች የሩቅ ዓላማቸውን ዘወትር በቅርብ እያሰቡት ይንቀሳቀሳሉ፡፡በተጓዳኝም ይህን የሩቅ ዓላማቸውን ተግባራዊ ለማድረግ እንዲችሉ የሚቻለውን መጠን ለይተው በትንንሹ እየተወጡት ያከማቹትና ገጣጥመው አንድ ወጥ ያደርጉታል፡፡የአጭርና የረጂም ጊዜ እቅዳቸውን በመጠን ለክተው በቅደም ተከተል አስቀምጠው እንደየአስቸኳይነቱ ይጠቀሙበታል፡፡ይህን እያደረጉም ለወዲፊቱ ራዕያቸው ግባት ማሰባሰባቸውን አይዘነጉትም

በሳል መሪ አዳዲስ ጠቃሚ ፈጠራዎችን ያምጣል፤ ይወልዳል፤ ያሳድጋል፤ አብረዋት ያሉትም የዚህ አካል እንዲሆኑ ይገፋፋል፡፡ ፈጠራው ለሃገርና ለወገን የሚበጀውን ለማግኘትና ሁሉንም የግኝቱ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡ከተለመደው ውጪ ሲያስብም ያረጀውንና ያፈጀውን ጎጂ ባሕል በማስወገድ በአዲስ ለመተካት፤ሰላም እንዲሰፍን፤ ግድያ እንዲያበቃ፤ለጥይት የሚውለው የሃገሪቱ ገንዘብ በልማት ላይ እንዲውል ለማድረግ፤ ለበሳል መሪ ፈጠራ ሲባል እድገት፤ ልማት ጤና ብልጽግና ነው፡፡

8 ጥንካሬ

ጥሩ መሪዎች አላስፈላጊና ጥቅም የለሽ ጉዳይ ላይ ጊዜያቸውን አያጠፉም ግን ለወደፊት ጠቃሚ ነው ብለው ካመኑበት ያንንም አላስፈላጊ የሚመስለውን ለወደፊት ጠቃሚ ፍሬ ሊያፈራ የሚችልበትን ሁኔታ ከማመቻቸት ፍርሃትና ጥርጣሬ አያግዳቸውም፡፡ይህን በሚያደርጉበት ወቅትም የሚገጥማቸውን ፈታኝ ተግባር ሁሉ የመቋቋም ብልሀትና ችሎታ አላቸው፡፡

መለስ

ጥንካሬ ስለሌላቸው በሌላው ጉልበት የሚጠቀሙ ጊዜያቸውን አላስፈላጊና ጥቅም የለሽ በሆነው ተንኮል ላይ ነው የሚያጠፉት፡፡ለነገ ማነው የሚያሰጋኝ፤ ማነው የሚቀናቀነኝ፤ በሚል ራስ ወዳድነት ላይ ነው ጥንካሬያቸው፡፡ለወገንና ለሃገር ነገ መልካም ፍሬ ከማምረት ይልቅ የተመረተው ሁሉ እንዲደርቅና ሃገሪቱ ለበረሃነት ሕዝቡም ለረሃብ የሚጋለጥበትን ነው ሲያስቡና ሲያቅዱ ጊዜያቸውን የሚያጠፉት፡፡

በሳል መሪ እያንዳንዷን ደቂቃ ለወገንና ከሃገር በሚጥም ተግባር ላይ ያውላል፡፡ ጥርጣሬና ፍርሃት ስሌለበት ማንኛውንም ነገር በበጎ በመመልከት ለጥቅምና ለፍሬ የሚበቃበትን ያሰልች፡፡ተንኮል ራስ ወዳድነት ምን ያህል ጎጂ እንደሆኑ ስለሚረዳ መልካምን ብቻ ይመኛል፡፡ለወገንና ለሃገር እድገትና ብልጽግና ስለሚመኝ ያን በተግባር ለማድረግ የሚያስችለውን ያቅዳል፡፡

በሳል መሪ

ሁለተኛ ደረጃን በምንም መልኩ ቢሆን ምርጫቸው አያደርጉም፡፡በሳል መሪዎች ድርጅታቸውም ሆነ አባሎች ከከፍተኛው ላነሰ ደረጃ አይጥሩም ይልቅስ ቢኖር ኖሮ ከከፍተኝው የበለጠም ተመኝተው የሚያስመኙ የትጋትና የጥረት ፋብሪካዎች ናቸው

መለስ

ሰውየው ሃሳባቸው ጥሩ የሆነ፤ህዝብን የሚመለከት የሆነ፤ እንደሆነ አደጋ አለው ብለው ስለሚፈሩ እኩይ ተግባራትን ነው የሚያውጠነጥኑት፡፡ሃገርና ህዝብ የሚሉት ስለሌላቸው ምኞት ሃሳባቸው ሁለ፤ ለራሳቸው ነው፡፡ለሃገር አያስቡም፡፡ ለወገን አይጨነቁም፡፡ አስተዳደር ሳይሆን ጨቁኖ መግዛትን ነው መመሪያ ያደረጉት ስለዚህም አንደኛውን ሳይሆን ዝቃጩን ነው ለሃገርና ለወገን የማያልሙት፡፡

በሳል መሪዎች

ከምንም በላይ ሃገር ከምንም በፊት ወገን ብላ ለሕዝብ ልእልና ለሃገር እድገትና ብልጽግና የቆመ ነው፡፡በምንም መልኩ ሃገር እንዲጎዳ ህዝብ ለችጋርና ለችግር እንዲጋለጥ አይፈቅድም፡፡ሌት ተቀን ስለ መልካም ነገር ስለሚያስብ ለሃገሩ የገባቸውን ቃል ለህዝብ ያሳደረውን ተስፋ በተግባር ያውላል፡፡ስለዚህም አንደኛውን እንጂ ከዚያ ያነሰ ለሃገርና ለወገን አይገባውም ባይ ነው፡፡

10 በሳል መሪዎች

የአባሎቻቸው ችሎታ የሚፈቅደውን ሁሉ እንደየአስፈላጊነቱ እያስወጡ በማሰራት እነሱ ራሳቸው ያላቸውን ጥንካሬና ትጋት ብስለትና ታማኝነት ንቃትና ቆራጥነት ለአባሎቻቸው ያስተላልፋሉ፡፡ለአባሎቻቸው መሃል ለመሪነት ብቃት ያላቸውን እየመረጡ ለወደፊቱ ተተኪነት ለማዘጋጀት ፈቃደኝነቱና ፍላጎቱ አላቸው፡፡በዚህም ድርጅታቸውን ጠንካራና የተዋጣለት ያደርጉታል፡፡

መለስ

አባሎቻቸው በራሳቸው ህሊና ሳይሆን አቶ መለስ በሚሉት ምንም ይሁን ምንም ሳይመዝኑና ጥቅምና ጉዳቱንም

ሳይለካ

እንደወረደ በመቀበል እንደቴፕ መድገም ነው፡፡ለአባሎቻቸውም ተጧሪነትን፤በሰው መመራትን፤አገልጋይነትን እንዲቀበሉ ሆነው እንዲቀረጹ ነው የሚያዘጋጇቸውም የሚያሰማሯቸውም፡፡መለስ ተተኪ መፍጠር ማለት ተቀናቃኝ ማዘጋጀት ነው ብለው ስለሚያምኑ ይህን ማድረግ ሳይሆን ማሰብመን አይፈልጉም፡፡ድርጅታቸውም ከሳቸው ውጪ ሰው ብሎ ነገር አልተፈጠረም በሚል የኩበት ግንብ የተገነባ ነው፡፡

ስለዚህም የመለስ መሪነት በባለበት ሂድን ብቻ የሚያውቅ አሁንም ከትግል ጅማሮው ዘመን ፎቀቅ ያላለን ከጠመንጃ ቃታ ውጪ ምንም የማያውቅ፤ ሕዝብ ማለት ጥቂት የአካባቢያቸው አለን ባዮችና የወ/ሮዋ ቤተሰቦች ውጪ የማያካትተ ዝግ ችሎት ሊባል የሚችል ነው፡፡