እልል ተፈታሽ አልልም!
በቤተ መንግሥት ጦጣ ገብቶ
ህገ አራዊት መሥርቶ
ሲያጭበረብረሽ ሲያፌዝብሽ
ሲስቅ ሲላለቅ ሲፈርድብሽ
አይበገሬ ሠላማዊ
ነገደ ኩሽ ሴማዊ
እንኳን ተፈታሽ አልልም
መታሠርሽ አይቀርም።
መምረጥ መመረጥ ብርቅ ሆኖ
ኢትዮጵያዊነት ታፍኖ
በረከተ እንጅ እሥረኛው፣
ሰፋልሽ እንጅ ወህኒ ቤቱ፤
የታሠርሽበት ዕግረ ሙቅ፣
አሁንም አለ ሰንሰለቱ።
በቤተ መንግሥት ጦጣ ገብቶ
ህገ አራዊት መሥርቶ
እሠይ ተፈታሽ አልልም
መታሠርሽ አይቀርም።
ጠመንጃ ነካሽ ወሮበላ
የታሪክ ዝቃኝ አተላ
ዕንከፍ ባንድነት ዶልቶ
እያጠመድሽ መረብ ሰርቶ
ተብትቦ ይዞሽ ወያኔ
መቼ ተፈታሽ ብርቱካኔ?
ህገ አራዊት ተሽርሽሮ
እስከማይ ድረስ ተሽሮ
እልል! ተፈታሽ አልልም
መታሰርሽ አይቀርም።
በወርቁ ለገሠ (10/6/10)