እድር የረሳው ሬሳ – ለሰሎሞን ተካልኝ
ከጋቹዬ አቹሌ
ምን ፈርስ ቢነፋው -ሆዱን እንደ ኩንታል፣
ሰው እንዴት በቁሙ-እንደዚህ ይሸታል?
ምን ዶማ ራስ ቢሆን -ከዲንጋ’ ማይሻል፣
ሰው እንዴት በሜዳ -ብስና ያቀረሻል?
ምን የጅል ጅል ቢሆን -አጎዛ ሙሀቻ፣
እንዴት ሰው ይሆናል – ዕቃ መጫዎቻ?
ምን ሆዱ ቢሰፋ -ከምንቸት ከቶፋ፣
እንዴት ነው በአፉ – ሰው ንፍጥ የሚተፋ?
ምን ቆለጥን ቢሆን – ሁልጊዜ አጨብጫቢ፣
እንዴት ሰው ይሆናል – የሰው ካካ አጣቢ? …
እያልኩኝ ስገረም – ነገሩን ሣስሰው፣
ለካ ሰው አይደለም -ሙት ነው የምወቅሰው።
በቁሙ የሞተ-ዳግም ላይነሳ፣
እድሩ ሳይቀብረው – የረሳው ሬሳ።