አውራምባ ታይምስ የመረጃ ምንጩን እንዲያሳውቅ በመንግስት ታዘዘ
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ደስታ ተስፋው በቁጠር 9.2/308 በዛሬው ዕለት ለአውራምባ ታይምስ ዝግጅት ክፍል በላኩት ደብዳቤ ጋዜጣው ለዜና ዘገባ የሚጠቀምባቸውን የመረጃ ምንጮች እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2002 ዓ.ም ድረስ እንዲያሳውቅ ጠይቀዋል፡፡
በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት መሠረት አንድ ጋዜጠኛ ለፍርድ ቤቶች ሳይቀር የመረጃ ምንጭ የማሳወቅ ግዴታ እንደሌለበት በግልጽ የተደነገገ ቢሆንም ብሮድካስት ባለስልጣን በ‹ሬጉላቶሪ› ሽፋን ሕገ መንግስቱን የሚጥስ ጥያቄ መጠየቁ የጋዜጣው ባልደረቦችን አስገርሟል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በአዋጅ ከተሰጠው ሀላፊነት ውጪ ጋዜጣው ከሽያጭና ከማስታወቂያ የሚያገኘውን የፋይናንስ ሪፖርት እንዲያሳውቅ የጠየቀ ሲሆን ይህን የመጠየቅ ኃላፊነት የተጣለበት የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን መሆኑ እየታወቀ ብሮድካሰት ባለስልጣን ይህንን መጠየቁ ብዙዎችን አስገርሟል፡፡