የካሱ ይላላ የመዝረፊያ ቀዳዳ

ነሃሴ 24 2010 ኢትዮጵያን ሪቪው ለንባብ ያበቃው ዜና ከወያኔ ማጅራት መቺዎች አንዱ የሆነው ካሱ ይላላ ገንዘብ የሚዘርፍበትን መንገድ መጠቆም ችሎአል። ከአልአሙዲ በመቀጠል በኢትዮጵያ ውስጥ ተከታዩ ሃብታም መሆኑ የሚነገርለት የሰንሻይን ኮንስትራክሽን ባለቤት ሳሙኤል ታፈሰ ከሚስቱ ጋር የተጋባበትን 25ኛ አመት በአል ለማክበር ዋሽንግተን ዲሲ ገብቷል። በርካታ የተጋበዙ የወያኔ ባለስልጣንትም አስረሽ ምቺው ለመጨፈር፣ እግረመንገድ ደግሞ ለልጆቻቸው የሚያወርሱትን ቪላዎች ለመገዛዛት ወደ ዋሽንግተን ዲሲ በማምራት ላይ ይገኛሉ።

የሚቀጥለው ቅዳሜ ነሃሴ 28፣ 2010 ሌሊት ከዲሲ ውድ ቦታዎች አንዱ የሆነው ማንዳሪን ኦርየንታል ላይ “ቅንድቡ ያማረው” የተባለው ለመለስ ዜናዊ የተዘፈነው ዘፈን ሊጨፈርበት ዝግጅቱ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ 200 ሺህ ዶላር ወጪ ተደርጎበታል ተብሎ የሚገመተውን ድግስ እንዲካፈሉ ከመላ አለም በርካታ የወያኔ እንግዶች ዋሺንግተን ዲሲ ገብተዋል።

በአዜብ መስፍንና በሳሙኤል ንብረትነት የሚታወቀው ሰንሻይን ኮንስትራክሽን በርካታ የመከላከያ ሚኒስቴር የግንባታ ኮንትራቶችን ያለውድድር እየወሰደ በሚሊዮናት የዛቀ ኩባንያ ሲሆን፣ በኩባንያው የሚገነቡ የሲቪልና የወታደራዊ ግንባታዎችን የጥራት ደረጃ መቆጣጠር በማይቻልበት ደረጃ ከስራው ጋር ያልተመጣጠነ ትርፍ ሲዝቅ ቆይቶአል። 25ኛ አመት የጋብቻ በአሏ በከፍተኛ ወጪ የሚከበርላት ሴት የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የካሱ ይላላ እህት ስትሆን፣ ካሱ ይላላ ከዚሁ ኮንስትራክሽን ድርጅት ከፍተኛ ገቢ ያገኛል።

(ምንጭ – ER)