ግንቦት 7ቶች መጽሃፋቸውን ናቸው – ገላነው ክራር
ከገላነው ክራር
ኢትዮጵያዊያን የገጠመንን አበሳና እየገባንበት ያለውን መቀመቅ በማሰረዳት የመጀመሪያውንና ዋና ዋና ጉዳዮችን የዳሰስ፣ ነገር ግን እጥር ምጥን ያለና፣ ስጋት የለቀቀብኝ፣ ተስፋም ያጫረብኝ መጽሃፍ ቢኖር የዶ/ር ሰለሞን ይርጋ “ህልውና” ነበር። ኢትዮጵያዊያን የበሽታ፣ ህዝብ ብዛት፣ የትምህርት ቀውስ፣ ችጋር … ወዘተ በአጠቃላይ የከፋ ድህነትና ኋላ ቀርነት በዘር ፖለቲካ ሲታሽ ወዴት እየሄድን እንዳለን የተዘገበበት ነው። ተስፋው ደግሞ፣ ደራሲው በዚሁ መጽሃፉ ያቀረባቸው የመፍትሄ ሃሳቦች፣ ከገባንበት አዘቅት ለመውጣት የሚያስችል ራእይና ችሎታውም ያላቸው ሰዎች ያሉን መሆናችን ነው።
ሁለተኛውና በድርጅት ስም የታተመው መጽሃፍ የግንቦት 7ቱ “ነጻነት ፍትህ ዲሞክራሲና አንድነት” ነው። በመጽሃፉ ቅርጽ ላይ፣ ለምሳሌ ደራሲው (ግንቦት 71)፣ አልፎ አልፎ ረጃጅም አረፍተ-ነገሮችን በመጠቀሙ፣ አንዳንዴ እንደገና ተመልሼ ማንበብ የሚያስፈልገኝ መሆኑ … እና ወዘተ በመሳሰሉትና ኢምንት በሆኑ ጉዳዮች ላይ ማተኮር፣ ስሜቴን ወጥሮ በያዘው በይዘቱ ላይ የምናውለውን ጊዜ ይሻማብናልና ወደ ይዘቱ።
ከገባንበት የታሪክ አጣብቂኝ አኳያ ድርጅቱ በ210 ገጾች ብቻ በተካተቱት ምእራፎች ውስጥ ሊያነሳቸው የሚገባቸውን ጉዳዮች ሁሉ ዳሷቸዋል። አብዛኛው የጽሁፉ ክፍል በመፍትሄ ላይ ያተኮረ መሆኑና መፍትሄውንም ያየበት ማእዘን፣ ባለፉት ሃያ ምንትስ አመታት ውስጥ በሃገር ጉዳይ ላይ ከተጻፉት መጽሃፍት ሀሉ የተለየ ያደርገውም ይመስለኛል። በግልጽና በድፍረት ያነሳውና፣ በህልውናችን አደጋ ላይ የሚያጠነጥነው ጽሁፍ ደግሞ በመጠን ጥቂት ቢሆንም ከስጋትም አልፎ ብርክ ያስይዛል። በመሆኑም መጽሃፉ ያተኮረባቸውንና እኔንም ስሜቴን ወጥረው የያዙኝን ሁለት ዋና ዋና ጉዳዮች አነሳለሁ። (ሙሉ ጽሁፉን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ።)