ነፍስ ይማር ዶ/ር ከፍያለው
ነፍስ ይማር
በኦባማ ሠፈር በነጻነት ማማ
በዋሽንግተን ዲሲ በሰፊው ከተማ፤
ከፍ ያለው ዶ/ሩ በቁም ሲከረፋ
ዝም ትላላችሁ ዕድር ሲያንቀላፋ?
ምነው የዕድር ዳኛ ንፋ እንጅ ጥሩምባ
ይሄ ዶ/ር ሞቷል በጧት አፈር ይግባ።
ፍታቱ ይፈታ ዕምባም ይለገሠው
መች ቀባሪ ያጣል በቁም የሞተ ሰው።
ለቅሶ ጠሪ ይላክ ለሰሌ ጠቢቡ
ለቁመና ዛላው ይቀኝ ለቅንድቡ።
የተማረ ሆዳም ፣ይህ የልጅ አመዳም
ከነፍሱ ቢቀበር እምብዛም አይጎዳም።
ዕድር ዳኛው ተነስ ሥራህ ነው ልፈፋ
ዶ/ር ከፌ ሞቷል ይነገር በይፋ።
ዕድሜ መስታዎት ነው ሁሉን አይቻለሁ
ሙት ወቃሽ አያርገኝ ነፍስ ይማር እላለሁ።
– ወርቁ