ተ – ውሽ ሠለሞን ተካልኝ (ግርማዊ ተፈሪ)

Solomon Tekalegne ሠለሞን ተካልኝ ግርማዊ ተፈሪ

ዱሮ ገና ሠለሞን ተካልኝ ያቀነቅናቸውን የነበሩ የነፃነት ዜማዎች ደጋግሜ ስስማ፤ ይህ ሰው ቢያንስ በርታ ሊባል ይገባል በሚል የህዝብ ልጅ ነው ብዬ በግጥም አሞግሼው ነበር። ከዚያ ገልበጥ ብሎ ወደ አዲስ አበባ በመብረር የቆጥ የባጡን ሲዘላብድ ስሰማው፤ አይ ሰው መሆን ምነው ሰውየው እንዲህ ተጃጃለ ድሮስ ከሞኝ ምን ይጠበቃል እያልኩ አላግጨ ዝም አልኩ። ሰሞኑን ደግሞ ‘አወጣሁ’ ያለው ዘፈን አይሉት ምን ስሰማው፤ አይ ይህ ሰው ጃዝ ብለውታልና ዋ ካልተባለ የበለጠ ሊሸናብን ነው አልኩና እነሆ ይችን ወረቀት ጫርኩ። ዘፋኝ ነውና በግጥም ብፅፍለት ዘፈን እንዳይመስለው እነሆ ተ – ውሽ ሠለሞን ብየ በስድ ንባብ ልሰደድበት ጀመርኩ።