አሁን ምን እናድርግ? (ይሄይስ አዕምሮ)
ይሄይስ አዕምሮ
ይድረስ ለኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን ጣቢያ፦
በቅድሚያ እንኳን ለ”ምርጫ 2002 በሠላም አደረሳችሁ!” ብዬ እንዳልጀምር ራሴን አከላከልኩትና፤ እንግዲያውስ ” እንኳን የኢትዮጵያ ህዝብ በጉጉት ለተቀበለውና እንዳይኑ ብሌን በስስት ለሚያየው የኢሳት ወይም የእሳት ቴሌቭዥን ሥርጭት መጀመር በሠላም አደረሳችሁ!” ማለትን ወደድኩ። የሚያግባባን ይመስለኛል። በዚያውም እናንተን ጨምሮ ብዙ ሰው ከማስቀየም እድናለሁ።