ምርጫ 2002 እና ቀጣዩ የትግል አቅጣጫ (ክርስቲያን)
ክርስቲያን ( [email protected] )
የምርጫ 2002 ዕቃ ዕቃ ጨዋታ ተጠናቀቀ። ከእባብ ዕንቁላል የእርግብ ጫጩት የጠበቁ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ተደናግጠው የሚሉትን አጥተው ዝምታን መርጠዋል። አቶ መለስ ዜናዊ በሠላማዊ መንገድ ሥልጣን ለመልቀቅ ፈቃደኛ አለመሆኑን ለማወቅ ምርጫ 1997 ወይም ምርጫ 2002 አስፈላጊዎች አልነበሩም (ይህ የኔ የግል አስተሳሰብ ነው)። የአቶ መለስ ዜናዊን አምባገነንነት እስከ አሁን ያልገባው ካለ አውቆ የተኛ መሆን አለበት።