የሌ/ኰ መንግሥቱ ኃይለማሪያም መጽሐፍ በኦፊሴል ነገ ገበያ ላይ ይውላል
በዛሬው ዕለት ገበያ ላይ የዋለው ሁለት ሺህ ቅጂ በአንድ ሰዓት ውስጥ አለቀ
Ethiopia Zare (ዓርብ ሐምሌ 16 ቀን 2002 ዓ.ም. July 23, 2010)፦ በጋዜጠኛና ፀሐፊ ገነት አየለ የተዘጋጀው ”የሌተና ኰሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ትዝታዎች (ቁጥር 2)” መጽሐፍ ነገ ቅዳሜ ሐምሌ 17 ቀን 2002 ዓ.ም. (ጁላይ 24 ቀን 2010 እ.ኤ.አ.) በኦፊሴል ገበያ ላይ ይውላል። ዛሬ ማምሻውን በጥቂቱ ለሽያጭ የቀረበው ሁለት ሺህ ቅጂ በአንድ ሰዓት ውስጥ ተሸጦ ማለቁን ከአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ ሪፖርተር ዘግቧል።