የዞን ዘጠኝ ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ ፣ ፀደቀ ድጋፌ እና አዲስአለም ደስታ በሁከት ማነሳሳት ወንጀል ተጠርጥረው በትላንትናው እለት ታስረዋል፡፡

የዞን ዘጠኝ ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ ፣ ፀደቀ ድጋፌ እና አዲስአለም ደስታ በሁከት ማነሳሳት ወንጀል ተጠርጥረው በትላንትናው እለት ታስረዋል፡፡ ትላንት ከስራ ሰዓት በኋላ በላሊበላ ሬስቶራንት ተገናኝተው ሻይ ቡና እያሉ በሚጨዋወቱበት ወቅት ነው ከምሽቱ 1፡30 ላይ እዛው ሬስቶራንት በነበሩ ሲቪል የለበሱ የፓሊስ አባላት ተይዘው 6ኛ ፓሊስ ጣቢያ የታሰሩት፡፡

ዛሬ ጠዋት ላይ ሶስቱም ቄራ ፍርድ ቤት ቀርበው የነበረ ሲሆን የቀረበባቸው ክስ “ላሊበላ ሬስቶራንት ሆነው መንግስት በቢሾፍቱ የኢሬቻ አክባሪዎች ላይ የወሰደው እርምጃ ትክክል እንዳልሆነ በዙሪያቸው ያሉትን ሰዎች ለተቃውሞ እንዲነሳሱ በሚያደርግ መልኩ ሲያወሩ ነበር “ የሚል ነው፡፡ በዋስትና እና ምስክሮች ጉዳይ ላይ ምላሽ ለመስማት ነገ ጠዋት 3 ሰዓት ላይ ቄራ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፡፡

3 Comments on “የዞን ዘጠኝ ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ ፣ ፀደቀ ድጋፌ እና አዲስአለም ደስታ በሁከት ማነሳሳት ወንጀል ተጠርጥረው በትላንትናው እለት ታስረዋል፡፡”

  1. ዛሬ አ.አ ሙሉ ኢንተርኔት ተቋርጧል ህዝቡ ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል ይፋ እናድርግላቸው እባካችሁ።

  2. Kezihe behala woyane deberale yemiserawe ketu tefetotale tesefa koretale .mereja teru newo ketelubet .dile le ethiopia hezeb. Wolo kombolecha hezbune nekewotale ye woyane tekamatene mawodem newo

  3. እንግዲህ ይህን ያነበበ ሁሉ ወያኔ ራሱ ይመክራል ። ሙያ በልብ ነዉ አታዉራ ማለቱ ነው ። ምክር እንቀበላለን ። ከማንም ።
    ሙያ በልብ ነው ። አታዉሩ።ነዉ ምክሩ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*