የኢትዮጵያ ሕዝብ ስለ ልዩነትና በአንድ ዘር ስለተደራጀ ወታደራዊ ገዳይ ጦር ሊሰማ ሊያይ ኣይገባም። ቆንጂት ስጦታው

ቆንጂት ስጦታው — የኢትዮጵያ ሕዝብ ስለ ልዩነትና በአንድ ዘር ስለተደራጀ ወታደራዊ ገዳይ ጦር ሊሰማ ሊያይ ኣይገባም። ይህንን የሚመኙለት ካሉ ኣንድም እድገትና ኣንድነት ፍቅርና እኩልነት የማይፈልጉ ሕዝብን ለማናከስ የሚጥሩ ኣልያም ልክ ሕወሓት በኣንድ ዘር ወጥ ምልምል ኣድርጎ በሰራቸው የኣግዓዚ ኮማንዶዎች ኣይነት ሌላ ኣዲስ የዘር ጭፍጬፋና እልቂት የሚመኙ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰው ጭፍጨፋ ማቆም የለበትም ብለው የሚያልሙ ቅዥታም ዘረኞች ናቸው። ሕወሓት የትግራይ ተወላጆችን ሰብስቦ በመሰረተው የኣግዓዚ ጦር እየደረሰ ያለው እልቂት ትምህርት ሊሆነን ይገባል።

ኢትዮጵያንን ያቀፈ ጠንካራ የእኩልነት መንግስት እንዲመሰረት ዜጎች በየትኛውም የሃገሪቱ ክፍሎች ተዘዋውረው የመኖርና የመስራት ሕልውናቸው እንዲረጋገጥ የሃገሪቱ ጦር ለስልጣን ጥመኞች ሳይሆን ለሕዝቦች ጥቅም የሚውል እንዲሆን መንግስት ሕዝብን እንዲያዳምጥ ጨፍጫፊው የሕወሓት ኣገዛዝ እንዲወገድ ሁላችንም የጀመርነውን ትግል ልንቀጥል ይገባል። ባረጀና ባለፈበት የዘር ፖለቲካ መጠመድን ኣቁመን የጀመርነውን የኣንድነት ትግል በድል በማጠናቀቅ ሕዝቦች በእኩልነት ካለኣድልዎ የሚኖሩባትን ኢትዮጵያን ልንመሰርት ይገባል።

 

ቆንጂት ስጦታው

4 Comments on “የኢትዮጵያ ሕዝብ ስለ ልዩነትና በአንድ ዘር ስለተደራጀ ወታደራዊ ገዳይ ጦር ሊሰማ ሊያይ ኣይገባም። ቆንጂት ስጦታው”

  1. እህቴ ጥሩ ብለሻል እኔም በጎረምሳው የዘር ፖለቲከኛ በጃዋር የተባለውን ዘረኛ ዲስኩር ሰምቼ መቸም ልጅ ያቦካው ለራት አይበቃም ነውና ከበሰበሰው ዘረኝነት ወደ ተግማማው ዘረንነት ሊያሸጋግሩን እየሰሩ ያሉ መኖራቸው ስጋቴን ከፍ አደረገው።
    ወያኔ ሆይ መቸም መሞቻህ ላይ ነህና እባክህ ቢያንስ አሟሟጥን ኣሳምረህ ሙት አገር ይዘህ አትሙት በሉልኝ

  2. Dont allow the perfect to be the enemy of the good. What you said is a perfect idea but not pragmatic and time sensitive. Doing so may take longer due to the challenge of unity i.e. buerocracy so that much more lives will lost until oppositions unify

    Why not we use common sense and encourage everyone carry fire arm so that he would save himself and his family from brutual murderers

  3. የአ.አ ህዝብ ውጥረት ውስጥ ነው ኢንተርኔት ከትግራይ እና ባንኮች በስተቀር ባጠቃላይ ተቄርጧል የዚህም ተጠያቂ በደብረፅዬን እና በድብቅ ጄነራሎች የሚመራው በአፍሪካ ኢንሹራንስ ህንፃ ሽፋን ስር ያሉ የደህንነት ባለሞያ ተብዬዎች ይህን ፈፅመዋል ግን የህዝብን ድምፅ ማፈን አይችሉም።

    ሞት ለወያኔ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*