በኢህአዴግ ውስጥ ድንገተኛ ጊዜ አዋጅ ታውጇል ። አዲስ አበባ ጭር ብላለች።

በኢህአዴግ ውስጥ ድንገተኛ ጊዜ አዋጅ ታውጇል ። አዲስ አበባ ጭር ብላለች።
#EthiopiaProtests#AddisAbeba#MinilikSalsawi#DownTPLF

Minilik Salsawi – mereja.com – በአሁኑ ሰዓት ሙሉ በሙሉ ኢህአዴግን የሚያስተዳድረው የህዋሃት የደህንነት ተቋሙና ወታደራዊው አመራር ነው።የደህንነት ተቋሙና ወታደራዊ ሃይሉ በሙሉ ስልጣን እየተንቀሳቀስ ነው።ድርጅት ውስጥ በድንገተኛ ጊዜ አዋጅ እየተሰራ ነው።

መቀሌ ዩንቨርስቲ የትግራይ ተዌላጅ ያልሆኑ ተማሪዎች ሕወሓት በጠራው ስብሰባ ላይ ኣንሳተፍም በማለት ተቃውሞ ኣሰምተዋል:: በኣዲስ ኣበባ ዙሪያ ያሉ ተቃውሞዎች የቀጠሉ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ከተሞች ተቃውሞ አና የሕወሓት ንብረቶችን ማቃጠል ቀጥሏል መሃል ኣዲስ ኣበባ ያለወትሮዋ ጭር ያለች ሲሆን የሰራ እንቅስቃሴ ሲቀዘቅዝ የትራንስፖርት እጥረት መከሰቱ ሲታወቅ ኣብዛኛው ሕዝብ ከቤቱ ኣልተንቀሳቀሰም።ወደ ደጅ የወጡትም የታክሲ ያለህ ሲሉ ተስተውለዋል።