መንግስት የቅሊንጦውን እሳት አደጋ በታሳሪዎች ላይ ለመደፍደፍ የሚያደርገውን ጥረት ያቁም! ድምፃችን ይሰማ
ድምፃችን ይሰማ
#EthioMuslims #EthioMuslimPeacefulStruggle
#EthioMuslimPrisoners
መንግስት የቅሊንጦውን እሳት አደጋ በታሳሪዎች ላይ ለመደፍደፍ የሚያደርገውን
ጥረት ያቁም!
ንጹሃን ታሳሪዎችን ማንገላታት ይብቃ!
ቅዳሜ መስከረም 21/2009
መንግስት የአገርን ህልውና የማስጠበቅ ኃላፊነት የተጣለበት አካል እንደመሆኑ
መጠን የአገር ህልውና ምሰሶ የሆነውን ሰላም የማስጠበቅ ኃላፊነት አለበት።
ይህንን ማድረግ ሲችል የአገር እና የህዝብ አለኝታ መሆኑን ያስመሰክራል፡፡
መንግስት አሁን እየሄደበት ያለው የዚህ ተቃራኒ ጉዞ በህዝብ ልቦና ውስጥ
የሚታነፅ ጥቁር ታሪክ ገንብቶና ከገዛ ህዝቦቹ ጋር ደም ተቃብቶ የታሪክ ባለ እዳ
እንደሆነ ወንበሩን ለተረኞች የሚያስረክበትን አይቀሬ ሂደት አመላካች ነው።
ሃያ አምስት ዓመት ያለፈው የገዢው መንግሰት የአገር አስተዳዳሪነት ታሪክ
ለህዝብ ሰላማዊ ጥያቄዎች ከአፈና የተለየ መልስ እንደሌለው እና ለአገር
ዲሞክራሲያዊ እድገት የሚጠቅሙትን የመብት ጥያቄ ያነሱ ዜጎች ላይ
በየትኛውም አጋጣሚ የበቀል እርምጃ እንደሚወስድ በተደጋጋሚ ታይቷል፡፡
የመብት ጥያቄ ያነገቡ ዜጎች ከመነሻው በማስፈራሪያና በዛቻ የፍርሀት ድባብ
ውስጥ እንዲኖሩ የመንግስት ፀጥታ ሃይሎች ሌት ተቀን የሚለፉ ሲሆን ብዙሃኑን
ህዝብ በድብደባና በግድያ፣ ከዚህ የመብት ጥያቄ ጀርባ ንቁ ተሳታፊ ናቸው
የሚሏቸውን ደግሞ በእስር በማንገላታት ይበቀላሉ፡፡ እነዚህ ታሳሪዎች ተገቢ
ባልሆነ የህግ ሂደት በማዕከላዊ ያልሰሩትን ወንጀል እንዲናዘዙ ከአራት ወር
ለሚበልጥ ጊዜ በተለያዩ መንገዶች የሚሰቃዩ ሲሆን የግፍ ክሱ ተመስርቶባቸው
ወደ ቂሊንጦ ሲሄዱም ይኸው ስቃይ መልኩን ቀይሮ ይጠብቃቸዋል፡፡ በካንጋሮው
ፍርድ ቤት የሚከናወነው ተውኔታዊው የክስ ሂደት ሳይቀር እነዚህን ንፁሃንን እና
ቤተሰቦቻቸውን በሚያሰቃይና ተስፋ በሚያስቆርጥ መልኩ የሚካሄድ ነው፡፡
ንፁሀን ታሳሪዎችን የማሰቃየቱ ሂደት ቀጥሎ በወርሃ ነሐሴ በቂልንጦ ማረሚያ
ቤተ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ንፁሀን ታሳሪዎች
ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን በርካቶችም ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ይህንን አደጋ
ተከትሎ ንፁሀን ታሳሪዎች ወደ ሸዋሮቢትና ዝዋይ ማረሚያ ቤት የተዘዋወሩ ሲሆን
በእነዚህ ማረሚያ ቤቶች ውስጥ ምግብና መጠጥ መከልከልን ጨምሮ በርካታ
ስቃዮች እየተደረገባቸው ይገኛል፡፡ የማዕከላዊ መርማሪዎች ወደእነዚህ ማረሚያ
ቤቶች በመሄድ ታሳሪዎቹን ‹‹እኛ ነን እሳቱን ያቃጠልን ብላችሁ እመኑ›› በሚል
ከባድ እንግልትና ስቃይ እያደረሱባቸው እንዳለ ከውስጥ የሚመጡ መረጃዎች
እያሳዩ ነው፡፡ ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ከተመለሱም በኋላ ስቃይና እንግልቱ
ከቀን ወደ ቀን እየጨመረባቸው ይገኛል፡፡ ንፁሃን ታሳሪዎች ላይ በማረሚያ ቤቱ
በተነሳው የእሳት ቃጠሎ የጥፋተኝነት ብይን ለመስጠት ክስና ለክስ ሂደቱ
የሚሆኑ የሀሰት ምስክሮችንም መንግስት እያዘጋጀ ይገኛል፡፡
እነዚህ ትንኮሳዎች እና በደሎች ህዝብን ለማሸማቀቅ፣ የመብት ትግልን ለማፈን
የሚደረጉ የተለመዱ ከንቱ ሙከራዎች ናቸው፡፡ መንግስት እንደዚህ ቀደሙ ሁሉ
በዚህ የግፍ ተግባሩ በህዝብ ዘንድ የተቀጣጠለውን የትግል ስሜት ከማጋጋልና
እየተከናነበ ያለውን የፖለቲካ ኪሳራ ከማባባስ ያለፈ አንዳች ጥቅም የማያገኝበት
በመሆኑ ንፁሃን ታሳሪዎችን ማንገላታት እንዲያቆም በጥብቅ እናሳስባለን! በዚህ
ሂደት በሚደርሱ ጉዳቶች ሁሉ ተጠያቂው መንግስት መሆኑን ህዝብ በሙሉ ልብ
የሚያውቀው እውነታ በመሆኑም ትርፍ የማያገኝበት የበቀል እርምጃ ከተጠያቂነት
እንደማያድነው መንግስት ሊያውቅ ይገባል!
በዚህ አጋጣሚ ህዝብ ከእነዚህ በግፍ እየተሰቃዩ ከሚገኙ ጀግኖችና
ቤተሰቦቻቸው ጎን በመቆም አጋርነቱን እንዲያሳይ ጥሪ እናቀርባለን!!!
መንግስት የቅሊንጦውን እሳት አደጋ በታሳሪዎች ላይ ለመደፍደፍ የሚያደርገውን
ጥረት ያቁም!
ንጹሃን ታሳሪዎችን ማንገላታት ይብቃ!
ትግላችን በአላህ ፍቃድ እስከድል ደጃፎች ይቀጥላል!
ድምፃችን ይሰማል!
አላሁ አክበር!
Like ☑ Comment ☑ Share ☑

እኛም እንደ ዜጋ አገር ስትጠፋ ዝም ብለን አናይም።
ኢህአዴግ እንደ መንግስት መቀጠል ስላልቻለ አገሪቱን ከጥፋት ለመታደግ በአደራ የሚያስተዳድር መንግስት በአስቸኳይ መቋቋም አለበት። ይህንንም የአደራ መንግስት ለመመስረት በህዝቡ ተዐማኒነት ያላቸውና ክሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የተውጣጡ ግልሰቦችን ስም ዝርዝር እናውጣና ኮሚቴ መስርተን ይህንን ለተለያዩ መገናኛ ብዙሃንና ተቋማት መንግስትን ጨምሮ እናስታውቅ። መመረጥ ያለባቸው ግለሰቦች በአገሪቱ ውስብስብ የፖለቲካ ጉዳይ ልምድና ዕውቅ ያላቸው ምሁራንና የፓለቲካ ጠበብት ፣ አድርባይነት የሌለባቸው፣ የማይፈሩትን፣ ቀናነት ያላችውንና በዚህ ውስጥ ምን እጠቀማለሁ የሚሉትን ሳይሆን ለአገራችን ሰላምና ለህዝቧ ደህንነት ክልብ የሚያስቡትን ይሁን።
ለጊዜው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግለሰቦች ስም አግኝተናል። ለዚህ ትብብር Abye A ን እናመሰግናለን። ከጎሰኝነት ስሜት ውጭ በሆነ ለአገር ይጠቅማሉ የምትሏቸውን የሰዎችን ስም አክሉበት። ቢያንስ የ 20 ሰዎች ስም ዝርዝር ቢኖረን ጥሩ ነው። እንፍጠን አገራችን ያለችበት ሁኔታ ጊዜ የሚሰጥ አይደለም።
1ኛ/ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ
2ኛ/ ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም
3ኛ/ ኮሎኔል ፍስኃ ደስታ
4ኛ/ አቶ ታምራት ላይኔ
5ኛ/ ዶ/ር ኃይሉ አርዐያ
6ኛ/ ፕ/ር ላፒሶ ገ ደለቦ
7ኛ/ አቶ አብዱ አሊ ሂይጅራ
8ኛ/ ዶ/ር ፈቃደ ሽዋቀና
9ኛ/ ዶ/ር አክሎግ ቢራራ
10ኛ/ አቶ አሰግድ ገ/ስላሴ
11ኛ/ ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም
Aklilu Seyum,
You forgot to include ,Abay Tshaye, Samora Yunus,..why not the whole tplf???
YOU BANDA!!!!
Don’t forget Gecho reda our communicator. We need spy so I will pick Debre tseion, is that a women’s name? Debre and Tsion.himmmmm….
በኢትዮጵያ ከአጣብቂኙ መውጫ መንገዶችና ዘላቂ መፍትሔዎች:- የውይይቱን የመጀመሪያ ክፍል – VOA Amharic (Part1)
http://niletube.net/?a=vVid&vidId=469&vidCId=8
NileTube.net
woyane thugs and looters never stop creating lies and fabrications. Woyane is fraudulent, corrupt, thief, murderer.
Woyane is founded on LIES. ITS FOUNDATION IS BUILT ON A lie AND A BIG LIE. IT has never told a true story. its composition is LIE, DAMN LIE and LIE. THEY EXIST to make lies and to fabricate stories. without LYING they cannot talk, or survive. It is their main job sitting in Arat Kilo. 24 hours 365 days a week the lie factory of woyane thugs and looters is at full speed working on their trade. they fully understand what the master BIG LIAR , Adolf Hitler said and they are taking their trade to new heights.
Hitler said, “If you tell a big enough lie and tell it frequently enough, it will be believed.”
tHE woyane looters even create dramas using their fabricated stories to convince the Ethiopian people. who can forget what they did in a mosque in Addis abeba – hey planted bombs in the mosque and try to blame and smear the moslems as terrorists. it is the catch phrase of the woyane thugs and looters to call everyone a terrorist, when the real terrorists are thr woyane thugs themselves.
the woyane looters are now looking like the proverbial hyena, who suddenly realises that the night is over for scavenging and suddenly it starts to rush to get back to its den to get cover before it is chased out.
woyane lie and fabricated propaganda is a thing of the past , it has expired, woyane looters are exposed, it is a common knowledge that woman means thief and murderer and LIAR.
everybody knows woyane as a LIAR and a THIEF. whatever LIE the woyane fabricate no body is going to listen. woyane is buried under its own LIE.
Lemanbeb:
x ende xornet=war
Kebietachuh liyafnuachuh lemexu ye tgrie woyanie telalakiwoch eji atsxu.
Bexam xenkara xere-woyanie tegbar adragi gleseboch yemetafen sgat alebachew. Slezih shgux kelielach yesela bilawa weym mexrebiya mazegajetna liyafnu yemimexubachuhn biyans andun gelo memot weym mamlex yichlal.
Yihn snaderg be afena yetesemarutn slemiyasfera bezih sra lemegbat flagot aynorachewm weym melegemna/mkniyat fexero wede huala maletna mitafenew gleseb endiyamelx madreg weym axanew blew behiwet lememeles shaxr yiseralu.
Asqedmew shuk yilutal, aqxaca yetesasatu meslew endiyamelx edlun yifexruletal, yewoyanie teqawami yehonut yeafena abalat yewoyanien degafiwech lemegdel (mitafenew gedelachew bemalet), weym lemasgedel endimokru yadergachewal.