ጠያቂ የተከለከለችው አስቴር ስዩም

አርማጭሆ ተወልዳ ያደገችው አስቴር ስዩም ከጎንደር ዩኒቨርስቲ ከዓመት በፊት ማስተርሷን በማዕረግ አግኝታለች፡፡ብአዴን/ኢህአዴግ ካልሆነች በተመረቀችበት ሞያ ስራ ማግኘት የማይታሰብ መሆኑ ቢነገራትም ሰዎች ባላቸው ብቃት ተወዳድረው ስራ የሚያገኙበት ዕድልን የሚፈጥር ስርዓት እንዲገነባ ለማገዝ የቀድሞውን አንድነት ፓርቲ በመቀላቀል በአርማጭሆ ወገኖቿን ስታደራጅ መቆየቷ በስርዓቱ ሰዎች ጥርስ ውስጥ አስገብቷታል፡፡
አስቴር በሚደርስባት ጫና የተነሳእና አዛውንት እናቷን ለመደገፍ በማሰብ ከአንድ ዓመት ሶስት ወራት በፊት ወደአዲስ አበባ ትመጣለች፡፡ነገር ግን በአዲስ አበባ የተቀበሏት የማዕከላዊ ቅጥረኞች ነበሩ፡፡በማዕከላዊ ቆይታዋ በቤተሰብ እንዳትጎበኝ በማድረግ ጠንካራ መንፈሷን ለመስበር ብዙ ግፍ ፈጽመውባታል፡፡


አሁን አስቴር ለእስር ከተዳረገች አንድ ዓመት ከሶስት ወራት ያህል ተቆጥሯል፡፡ከማዕከላዊ ወደ ቃሊቲ ቢያሸጋግሯትም የቃሊቲው መንግስት ከጠያቂዎች ጋር እንዳትገናኝ አድርጓታል፡፡


የአንዲት ህጻን እናት የሆነችው አስቴር ልጇን ይንከባከቡላት የነበሩት ወላጅ እናትዋ በዕድሜ መግፋትና ጤና ማጣት ጋር ተያይዞ ህመምተኛ መሆናቸው ስጋት ፈጥሯል፡፡አስቴር ብቻዋን እንዳልሆነችና ጀግኖቹን የማይዘነጋ ህዝብ(ወገን)አጠገቧ እንደሚገኝ ለማሳየት ይህ የጎ ፈንድ የትብብር ማሳያ አካውንት ተከፍቷል፡፡ እናም ለአስቴር አለን እንበላት፡፡

8 Comments on “ጠያቂ የተከለከለችው አስቴር ስዩም”

  1. የህዝብ ጥያቄ ስልጣን በአንድ አንስተኛ ጠባብ እጅ ስለወደቀ እኩል ተካፍለን አገራችን በጋራ እናስተዳድር ነው። የ 100 ሚሊዮን ህዝብ አገር በጥቂቶች መተዳደር ይብቃ። የአደራ መንግስት ሁሉንም ያካተተ ይቋቋም ነው ያለው ህዝቡ። ጥገና ሳይሆን ለውጥ። ሰው መቀያየር ሳይሆን የስርዐት ለውጥ። አባ ድላን አንስቶ ተሾመ ቶጋን መተካት ሳይሆን ምሁራንን የአገር ሽማግሌዎችን ተቃዋሚዎችን ያካተተ የአደራ መንግስት በአስቸኳይ ይቋቋም ነው ጥያቄው መልሱም እሱ ብቻ ነው።

  2. Ya eritrea yalew d.m.h.t (yetgrai nqnaqie) mibal mole segdom yekedaw ketewaga tgrai hido woyanien yiwaga wede gonder tekezen teshagro megbat yelebetm. Kegeba yimeta.

  3. እንደናስቴር ያሉትን ወጣት ዜጎች እጅ እና እግራቸው እየተነፈሰ ለሃገራቸው ለሕዝባቸው ብሎም ለራሳቸው ሰርተው የሚለወጡበትን ጊዜ ወያኔ በመንግስት ደረጃ ተቀምጦ እንደዚህ እያደረገ ያገሪቱን ንፁህ ዜጎች ለግል ፍጆታው መጠቀሚያ እያደረጋቸው ይገኛል፤ ይህ በመሆኑ ማንኛውንም ነፃነት ፈላጊ ዜጋ ሁሉ ሊአንገበግበው ይገባል፤ የሚአሳዝነው ነገር ደግሞ ለጥሩ ነገር ያልታደልን በመሆናችን፤ ሁልጊዜ መጥፎ ነገር አስታዋሽ እና ለበቀል ተዘጋቾች ሁነን መቅረታችን ነው፤ እንደዚህ አይነቱ ችግር አንዳንዴም በታድሎ ጭምር ካልሆነ በስተቀር ብቻውን በትግልና በፍላጎት አይገኝም።

  4. Where is the account number aster ayezosh nesanet kerb Nat sefew ye Ethiopia hezbe yashenfal GOD BLESSE ETHIOPIA!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*