የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን በኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜዎቹ ግጭቶች ስለጠፋው የሰው ህይወትና የንብረት ውድመት እንዲሁም ዜጎች ለእስር የተዳረጉበትን ሁኔታ በልዩ ትኩረት እከታተላለሁ አለ

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን በኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜዎቹ ግጭቶች ስለጠፋው የሰው ህይወትና የንብረት ውድመት እንዲሁም ዜጎች ለእስር የተዳረጉበትን ሁኔታ በልዩ ትኩረት እከታተላለሁ አለ

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን በኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜዎቹ ግጭቶች ስለጠፋው የሰው ህይወትና የንብረት ውድመት እንዲሁም ዜጎች ለእስር ለተዳረጉበት ሁኔታ በልዩ ትኩረት እከታተላለሁ አለ…ለጠፋው የሰዎች ሕይወትም ከልብ ማዘኑን በኢትዮጵያ የህብረቱ አምባሳደር ተናግረዋል፡፡

በአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ አምባሳደሯ ቻንታን ሀብርቻት የኢትዮጵያ ህገ መንግስት ሙሉ ለሙሉ ስራ ላይ ቢውል ምርጥ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡በመሆኑም አለመግባባቶች ሲፈጠሩ መንግስት ራሱን ከዜጎች ጋር ለመነጋገር ማዘጋጀት ነበረበት መፍትሄውም ኃይልን ከመጠቀም ይልቅ ጥያቄዎቻችሁ ምንድን ናቸው፣ ምን ላድርግ ማለት ነበረበት ብለዋል፡፡ የፖለቲካ ልዩነቶች ቢኖሩም እንኳን መንግስት ጥያቄዎችን ለማዳመጥ ጆሮውን ክፍት ማድረግ እንደነበረበት አክለው ጠቁመዋል፡፡መንግስት በቅርብ ጊዜ አደርገዋለሁ ብሎ ቃል የገባው ምን ላይ እንዳደረሰው እና የሚያደርገውን ለውጥ እንጠብቃለን ብለዋል፡፡

በስደተኞች ጉዳይም ሁለት አይነት እቅዶችን ማስቀመጣቸው ጠቅሰዋል፡፡በአምባሳደሯ የቅርብ ጊዜ እና የረጅም ጊዜ እቅድ ተብለው ከተቀመጡት መካከል ወደ አውሮፓ መዳረሻቸውን አድርገው በስደት የሚሞቱ አፍሪካውያንም በሜዲትራንያን ባህር ከመስጠም መታደግ የአጭር ጊዜ ዕቅድ ሲሆን የረጅም ጊዜ እቅዳቸው ደግሞ እስከ መንደር ድረስ በመዝለቅ የስራ ዕድል በመፍጠር ወደ ስደት እንዳያማትሩ ማድረግ ነው ብለዋል፡፡

ለዚህም ከአፍሪካ 5 አገሮች የተመረጡ ሲሆን ኒጀር፣ ሴኔጋል፣ ናይጄሪያና ማሊን ተከትላ ኢትዮጵያም ተቀምጣለች፡፡ ህብረቱ ጋዜጠኞችን ዛሬ በደሳለኝ ሆቴል ጠርቶ ስለ ሰላምና ፀጥታና ስደትን ስለመቆጣጠር ሽብርተኝነትን ስለመከላከል፣ ስለኢንቨስትመንትና የአየር ንብረት ለውጥ እየሰራ ስላለው ስራ እና ስለወደፊት እቁዱም መግለጫ ሰጥቷል፡፡

3 Comments on “የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን በኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜዎቹ ግጭቶች ስለጠፋው የሰው ህይወትና የንብረት ውድመት እንዲሁም ዜጎች ለእስር የተዳረጉበትን ሁኔታ በልዩ ትኩረት እከታተላለሁ አለ”

  1. Rasun yechal ager biet tegadlo ale

    keshabiya yemeshigew tagay arbe-gnbot 7 shiba hunoal.
    Be etiopiya behzbu yetejemerew tegadlo kerasu keanqesaqashoch miriwechn melmlo wede dlu meguaz alebet.
    Meri rasu tagayu mehon alebet. Ahun yetglu ajemamerna guzo amerqi new.
    Alamachn gedayun tgrie woyanie gelen maswegedna yekulnet ager memesret new.
    Gedayochachn tgrie woyaniewochn sngel, ” tgrie yezer fjit deresebet”, blo neger yelem.
    Jilnet weis majajal.
    Teqebaynet yelielew yetgrie woyaniena yajajalachew jiloch adenquari hasab new. Kejilochm mekakel arbe-gnbot 7 new.
    Kahun behuala rdata wugiya wedemideregbet wede gonderna gojam betolona bakal melak alebet.
    Aqumu erdata wede arbe-gnbot 7 melak.
    Yefelege agerbiet hido tglun yiqelaqel.

  2. የህዝብ ጥያቄ ስልጣን በአንድ አንስተኛ ጠባብ እጅ ስለወደቀ እኩል ተካፍለን አገራችን በጋራ እናስተዳድር ነው። የ 100 ሚሊዮን ህዝብ አገር በጥቂቶች መተዳደር ይብቃ። የአደራ መንግስት ሁሉንም ያካተተ ይቋቋም ነው ያለው ህዝቡ። ጥገና ሳይሆን ለውጥ። ሰው መቀያየር ሳይሆን የስርዐት ለውጥ። አባ ድላን አንስቶ ተሾመ ቶጋን መተካት ሳይሆን ምሁራንን የአገር ሽማግሌዎችን ተቃዋሚዎችን ያካተተ የአደራ መንግስት በአስቸኳይ ይቋቋም ነው ጥያቄው መልሱም እሱ ብቻ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*