የኦህዴድ ምክትል የሆነው ወርቅነህ ገበየሁ ማንነት ሲገለጥ

የኦህዴድ ምክትል የሆነው ወርቅነህ ገበየሁ ማንነት ሲገለጥ
For Election purpose,his LName is “Negawo” &for schooling his LName is “Woldekidan”

fb_img_1474533819240ክንፉ አሰፋ – ከምርጫው ጥቂት አስቀድሞ የወርቅነህ ገበየሁ አያት ስም ገብረኪዳን ነበር። የቀድሞ ወዳጄ ወርቅነህ የአያቱን ስም ከገብረ-ኪዳን ወደ ኩምሳ ለመቀየር የወሰደበት ግዜ እና ምክንያቱ አላስደነቀኝም። ይህንን የዘር ፖለቲካ ጨዋታ ጠንቅቆ የሚያውቀው ዶ/ር መረራ ጉዲናም የተቃዋሚ እጩ ተመራጭ ነበር። ጉዳዩን ጠንቅቆ ያውቀዋል። በአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ ፖለቲካ ሳይንስ ፋካልቲ ስንማር ሁለታችንንም በአንድ ክፍል አስተምሮናል። የወርቅነህ ትክክለኛ አያት ስም ያለበት ሰነድም በእጁ አለ። ግን ጉዳዩን አላጋለጠውም። ምናልባት የሙያው ስነ-ምግባር ይህንን ለማድረግ አይፈቅድ ይሆናል።

ወርቅነህ ገበየሁ ሻሸመኔ ነው ተወልዶ ያደገው። እዚያ መኖሩ ደግሞ ኦሮምኛን አቀላጥፎ እንዲናገር ረድቶታል። ዘር መቁጠር ጸያፍ ቢሆንም ይህ ግን መታወቅ ያለበት ጉዳይ ነውና ርቅነህ ገበየሁ ወላጆች ኦሮሞዎች አይደሉም። ከትግራዩ አቶ ገበየሁ ገብራኪዳን ይወለዳል።

 

ወርቅነህ ገበየሁ ውሎውም ቢሆን ከጆሌ ኦሮሞ ጋር አይደለም። ከነ ጌታቸው ረዳ፣ ከትግራይ  ተወላጆች ጋር በብዛት ያዘወትራል። ለዚህም ምክንያት አለው።  ይህ ሰው አሁን የኦሮሞውን ድርጀት እንዲመራ መመረጡ አንደኛው ምክንያት ነው። በህወሃት የፖለቲካ ጨዋታ  ምክትል ሆነው የሚቀመጡት በዘር መስፈርት ተለክተው አልያም ታማኝ አገልጋይ  ሲሆኑ ብቻ ነው። ዋናውን ስራ የሚሰሩትም በምክትል ስም ያሉት ናቸው። ከስር ሆነው ዋናዎቹን እንደ ሮቦት ያንቀሳቅሷቸዋል። ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ እና ምክትሉ ደብረጽዮንን ያስተውሏል!

 

ለመሆኑ ወርቅነህ ገበየሁ ማን ነው? ለምንስ ታስሮ ተፈታ?  የወንጀል እስረኛ የነበረ ይህ ሰው እንዴትስ በጥቂት ጊዜ እዚህ ደረጃ ላይ ሊደርስ ቻለ? ከዚህ ቀደም በማስታወሻዬ ላይ ያሰፈርኩዋትን ቁም ነገር ላካፍላችሁ። መልካም ንባብ።

 

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጭር ብሏል። ኢህአዴግ ወደ አዲስ አበባ ሲጠጋ፤ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ደግሞ ለወታደራዊ ስልጠና ወደ ብላቴ ማሰልጠኛ ካምፕ ገብተው የተኩስ ልምምድ በማድረግ ላይ ነበሩ። በግንቦት ወር ኢህአዴግ ከተማውን ከተቆጣጠረ በኋላ፤ ተማሪዎች እንደወትሮው ጥቁር ጋዋናቸውን ለብሰው፤ የአበባ እቅፍ አልተበረከተላቸውም – 1983 ዓ.ም.።

 

ከወራት በኋላ በዩኒቨርስቲው አካባቢ ይመላለሱ የነበሩ ተማሪዎች ተስፋ የሚያስቆርጥ ዜና ሰሙ። አዲሱ የሽግግር መንግስት እንደከዚህ ቀደሙ ተማሪዎችን በየመስሪያ ቤቱ የማይመድብ መሆኑ ተገለጸ። ከዜናው ጋር የብዙ ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው ተስፋ አብሮ ጨለመ። በተለይ በወቅቱ በፖለቲካ ሳይንስ ለተመረቅነው ተማሪዎች፤ ምንም ክፍት የስራ ቦታ እንደሌለ በግልፅ ተነገረን።

 

በዚህ አይነት ያለ ስራ ብዙ ቆየን። በወቅቱ በፖለቲካ ሳይንስ ከተመረቅነው መካከል በከፍተኛ ነጥብ የተመረቀው ወርቅነህ ገበየሁ ጭምር ምንም አይነት የስራ እድል ለማግኘት አልቻለም።

 

ህወሃት ካመጣብን የዘር ፖለቲካ በፊት በትምህርት ቤትም ሆነ በዩኒቨርሲቲ ከቶውንም የትውልድ ዘራችንን ተጠያይቀን አናውቅም። ማን ምን እንደሆነ፣ ለማወቅ ፍላጎቱም አልነበረንም። የኋላ ኋላ ግን ነገሮች እየተቀየሩ መጡ። በጓደኛሞች መካከል የሚፈጠር ጥርጣሬና፣ የዘር ግንድ ማጥናቱ ኢህአዴግ በኢትዮጵያ እንደተስቦ ያመጣብን በሽታ ነበር እና የቅርብ ወዳጅን ማወቁ የግድ ሆነብን። ወርቅነህ ገበየሁም የሻሸመኔ ልጅ ከመሆኑ ባሻገር፤ ከትግራይ ሰው መሆኑን ያወቅነው ከዩኒቨርስቲ ከወጣን በኋላ ነበር። በወቅቱ ነበረው የሽግግር መንግስት ባወጣው የዘር መስፈርት መሰረት፤ ወርቅነህ በትግራይነትና በደቡብ ህዝብነት መካከል የቆመ፤ ምርጥ የትግራይ ልጅ አለመሆኑ፤ በዚህም ምክንያት ሊያገኝ ይችል የነበረው ጥቅማ ጥቅም በመቅረቱ የጓደኛችን ጉዳይ ያሳዝን ነበር።

 

ከብዙ ጊዜ አንዴ ስንገናኝ፤ አንዳንድ ጓደኞቻችን ፀጉራቸው አድጎ፤ ንፅህናቸው ተጓድሎ፤ ከስተውና ተኮሳምነው ይታዩ ነበር። ከነዚያ ከሰውነት ውጪ ከሆኑት ተማሪዎች መካከል አንዱ ወርቅነህ ገበየሁ ይጠቀሳል።

 

የ1980ዎች አጋማሽ የፕሬስ ነጻነት የታወጀበት ወቅት በመሆኑ በርካታ መጽሄቶችና ጋዜጦች በገበያ ላይ ይውሉ ነበር። ሞገድ ጋዜጣም በወቅቱ ከነበሩት ከመጀመሪያዎቹ የነጻ ፕሬስ ጋዜጦች ረድፍ ላይ ይሰለፋል። ወርቅነህ ገበየሁም በነበረው አቋም ምክንያት የሞገድ ጋዜጣ ተባባሪ አዘጋጅ ሆኖ የመስራት እድሉን አገኘ። ወርቅነህ የጋዜጣው አዘጋጅ እንደመሆኑ መጠን በእለት ተለት የጋዜጣው ህትመት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም። ሆኖም ሳምንታዊ ደሞዙን ለመቀበል ወደ ቢሮ ሲመጣ በወጡት ዜናዎችና ጽሁፎች ላይ አልፎ አልፎ እንነጋገራለን። አንዳንዴም በጣም ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን ስናገኝ፤ ከማንም በፊት ከወርቅነህ ጋር በመመካከር መስራታችንን ቀጠልን።

 

አንድ ቀን የሃሙስ እትማችንን የውስጥ ገጽ ስራዎች አጠናቀን በፊት ለፊት ሊቀርቡ የሚገቡ ዜናዎችን እየመረጥን ሳለ፤ ስልክ ተደወለ። ግርማቸው ነበር።

 

“ሰላም ግርማቸው? ምን ዜና አለ?”

 

“ብቻህን ነህ?”

 

“አዎ”

 

“ጥብቅ የሆነ ሚስጥር ነው። ተጠንቀቅ።”

 

“ምንም ችግር የለም፤ ንገረኝ።” አልኩና እስክሪብቶና ወረቀት አዘጋጀሁ።

 

ግርማቸው ጉዳዩን ሙሉ ለሙሉ በስልክ ሊነግረኝ የፈራ ይመስላል። ፈራ ተባ እያለ፤ “ከውጭ አገር ወደ ኢትዮጵያ የገቡ የኢህአፓ አባላት ናቸው…”

 

“እና ምን ሆኑ?”

 

ግርማቸው አሁንም በስጋት ስሜት፤ “ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው። ለማንኛውም ለምን አንገናኝም?” አለኝ።

 

“ፖስት ራንዴቩ እንገናኝ?” ስለው ከጭንቀቱ የገላገልኩት ያህል፤ “አዎ እዚያ እንገናኝ።”

 

ረቡዕ ቀን ረፋዱ ላይ ፖስት ራንዴቩ ወደ ግርማቸው ጋ ስሄድ ብቻዬን አልነበርኩም። ወርቅነህ ገበየሁ አብሮኝ ነበር። በቀጠሮው ቦታ በሰዓቱ ተገናኘን።

 

ግርማቸውን ፖስት ራንዴቩ ስናገኘው ዘና ብሎ ያጫውተን ጀመር። “እንግዲህ ሰዎቹ የኢህአፓ አባላት ናቸው። ጉዳያቸው በሚስጥር መያዝ አለበት። ወደ አገር ቤት የመጡት ልዩ ሚሽን ተሰጥቷቸው ነው። ጉዳዩን ስትገናኙ በዝርዝር ትነጋገራላችሁ።” አለንና ስለሰዎቹ ማንነት አንዳንድ ተጨማሪ ነገሮችን ሲገልጽልን እስክሪብቶና ወረቀት አውጥቼ መጻፍ ጀመርኩ።

 

“በምታገኛቸው ጊዜ ይህንን የሚስጥር ኮድ መናገር አለብህ” አለና የድብቅ ስማቸውን ነገረኝ።

 

“የድብቅ መጠሪያ ስማቸው ‘ቤሬክ’ ይባላል” ሲለኝ ወረቀት ላይ ይህንኑ አሰፈርኩት። ወርቅነህም እስክሪብቶውን ከኪሱ አውጣ።

 

“በዚህ ስልክ ደውሉና የእኔን ስም ጥሩላቸው። ለጋዜጣችሁ በርካታ መረጀዎችን ሊሰጡዋችሁ ይችላሉ።’ አለን ግርማቸው።

 

ስልክ ቁጥራቸውን እየነገረን ወረቀት ላይ መጻፍ ስጀምር፤ ወርቅነህም ስልክ ቁጥሩን በእጁ መዳፍ ላይ ሲጽፍ አይቼ ሁኔታው አስገርመኝ። ነገር ግን በይሉኝታ ዝም አልኩት።

 

በወቅቱ በርካታ ጋዜጦች የፈሉበት ጊዜ በመሆኑ፤ ወርቅነህ ይህንን ዜና ከሞገድ ጋዜጣ ውጪ ለሚታተሙ ፕሬሶች አሳልፎ ሊሰጥ ነው በሚል ጥርጣሬ ብቻ ድርጊቱ አስገረመኝ። ከአንድ የትምህርት ቤት ጓደኛ፣ ከዛ በላይ ላስብ አልችልም። ልጠይቀውም አሰብኩና ጠይቆ ከመቀያየም ዝም ማለቱን መረጥኩ። በወቅቱ በውስጤ ቅሬታ አሳደረብኝ።

 

በሚቀጥለው ቀን… ግርማቸው በሰጠኝ ስልክ በተደጋጋሚ ብደውል እነ ቤሬክን ላገኛቸው አልቻልኩም። ቀን ላይ፣ በምሽት እና በሌሊት፣ ስልኩን መቀጥቀት ያዝኩ። ስልኩ ይጠራል። የሚመልስ ግን አልነበረም።

 

ከቀናት በኋላ ግርማቸውን ለመፈለግ ዘወትር ወደምንገናኝበት ወደ ፖስት ራንዴቩ ለብቻዬ አመራሁ። ሌሎች ጓደኞቼ እንደወትሮው ክብ ሰርተው ይጫወታሉ። ግርማቸው ግን አልነበረም።

 

“ግርማቸውስ?” አልኳቸው ወድያው እንደተቀላቀልኩ። ሞቅ ያለ ጨዋታቸውን እንዳቋረጥኳው ይሰማኛል።

 

“ሰላምታ አይቀድምም?” አለ አንዱ፣ ከፊቴ የሚነበበውን የደንጋጤ ስሜት በማስተዋል።

 

“ቀን ላይ ተደዋውለን ነበር። በሆነ ጉዳይ ትንሽ ተረብሿል። ለማንኛውም ዛሬ እንደምንገናኝ ነግሮኝ ነበር።”  ሲል ሌላኛው መለሰ።

 

ግርማቸው አረፋፍዶ ብቅ አለ። ፊቱ ላይ አንዳች የብስጭት ስሜት ይነበባል።  በውስጡ የታመቀውን ንዴት ያወጣው ገና ወንበሩ ላይ ሳይቀመጥ ነበር።

 

“ሰዎቹን አሳሰራችኋቸው አይደል?” ሲል ፍጹም ሃዘን በተሞላበት አንደበት ጠየቀ፣ ወደ እኔ እየተመለከተ።

 

“ወርቅነህ!” አልኩ ሳላስበው በመጮህ።

 

በመካከላችን ለአፍታ ጸጥታ ሰፈነ። ለተልካሻ ነገር የጠረጠርኩት ሰው ከጀርባዬ ሆኖ ከባድ ወንጀል እየሰራ ኖሯል!

 

የነ ቤሬክ መሰወር በውስጤ ጥርጣሬ፣ ፍርሃት እና ቅያሜ ፈጥሮብኝ ኖሮ ወርቅነህን እርቀው ጀመር፣ ከዛ ስልክ ከተቀበልንበት እለት በኋላም አልተገናኘንም። ከሞገድ ጋዜጣም ቀስ በቀስ እየራቀ መጣ።

 

አንድ ቀን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ካምፓስ የሃይድሮ ፖለቲክስ ምሁር የሆኑትን ዶ/ር ያቆብ አርሳኖ ስለአባይ ጉዳይ ቃለመጠይቅ ለማድረግ ሄጄ ወርቅነህን ከሩቅ አየሁት። ከዚያ ደግሞ ተሰወረ።

 

ስራዬን ጨርሼም ከዩኒቨርሲቲው ግቢ ለመውጣት ስሯሯጥ ከኋላዬ አንድ ሰው ያዘኝ።

 

እኔን ያላየኝ መስሎኝ ነበር። ከእነማን ጋር እንደምንገናኝና ምን እንደምሰራ በአይነ ቁራኛው ይከታተለኝ ኖሯል ወርቅነህ።

 

“ለምንድነው የምትሸሸኝ?” አለኝ፣ እንደመቆጣት እያደረገው።

 

ትንሽ እንደመደንገጥ ብዬ ስለነበር ለሰኮንዶች ጸጥ ካልኩ በኋላ “አንተስ ለምንድ ነው የምትከታተለኝ?” አልኩት በቁጣ።

 

“እውነቱን እንድነግርህ ነው የምትፈልገው?… ተረጋጋ እና አድምጠኝ፣ ሁሉንም ጉዳይ እነግርሃለው።” አለኝ መልሶ ረጋ ባለ አንደበት። ቁጣዬን ለማብረድ ሲል ያደረገው ይመስላል። በድንጋጤ የተነሳ የምናገረውም ጠፋብኝ እና ጸጥ ብዬ ከአንደበቱ የሚወጡትን ቃለት መተባበቅ ጀመርኩ።

 

“በደህንነት መስሪያ ቤት ውስጥ ተቀጥሬ እየሰራሁ ነው።” ሲለኝ ያልጠበኩትን ሚስጥር ድንገት ስለነገረኝ ሁኔታው አስደነገጠኝ።

 

“በደህንነት ውስጥ በመስራቴ ደግሞ እናንተን ከስንት አደጋ ጠብቅያችኋለሁ። በአጭሩ ‘I am protecting you’ ስለዚህ አትሽሸኝ።” አለኝ። ከእግር ጥፍሬ እስከራስ ጸጉሬ አንዳች ነገር ወረረኝ። ልቤ በፍጥነት ሲመታ፣ ደምስሮቼ ሲገታተሩ ተሰማኝ።

 

“እና ሰዎቹን…” መናገር አልቻልኩም።

 

“የምን ሰዎች?”

 

“እነቤሬክን ያሳፈንካቸው?” አልኩትና መልስ ሳልጠብቅ እዛው የቆመበት ጥዬው ሄድኩ።

 

***

 

ከወራት በኋላ ወርቅነህ የደህንነት ሃላፊ ሆኖ ሻሸመኔ ስራ መጀመሩን ሰማሁ። ይህንን ዜና ሰምተን ብዙ ሳንቆይ “ወርቅነህ በጦር መሳሪያ ሽያጭ ተያዘ” ተብሎ ወደ እስር ቤት ተወረወረ።

 

ከሰባት ወራት በኋላ ወርቅነህ ገበየሁ ከእስራት መፈታቱን ሰማሁ። ከእስራት ሲፈታ ግን የምናውቀው የወርቅነህ ገበየሁ የዘር ሃረግ ተቀይሮ፤ የ‘ኦሮሞ’ ብሄር ተወላጅ ተብሎ፤ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ከፍተኛ አመራር ሆኖ፤ ሹመት አግኝቶ የኢህአዴግን ካምፕ በግላጭ ተቀላቀለ… ወጣት ወርቅነህ ገበየሁ።

 

የእድሜ፣ የትምህርት ደረጃ፣ የስራ ልምድ፣ በተለይ በፖሊስ ሰራዊት ስራ የሚጠይቀው የስራው ስነ-ስርዓት እና በሙያው ስነምግባር ላልተካነ ግለሰብ ያንን ትልቅ ስፍራ እንዲመራ ነው፤ አቶ መለስ ዜናዊ ሹመት የሰጡት።

 

አንዳንዴ ወርቅነህ ገበየሁ በቴሌቭዥን ሲቀርብ የድሮውን መልካም ሆነ ክፉ ነገር እያሰብኩ፤ “ወይ ጊዜ” ማለቴ አልቀረም። ወርቅነህ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፖለቲካ ሳይንስ በባችለር ዲግሪ በጥሩ ውጤት የተመረቀ ወጣት ስለሆነ ከሌሎቹ ፊደል ካልቆጠሩ የህወሃት ባለስልጣናት የተሻለ ነው። ሆኖም በማናቸውም ጊዜ የግል ፋይላቸው ታይቶ ወደ እስር ቤት ሊወረወሩ ከሚችሉት፤ በ“ቀይ መስመር” ከቆሙት ባለስልጣኖች አንደኛው መሆኑ እርግጥ ነው። ግና ለጌቶቹ ታማኝ መሆኑን በዘሩ ብቻ ሳይሆን በስራውም አረጋግጦላቸዋል። ዛሬ ኦህዴድን የሚመራው የኦሮሞ ተወላጅ ሳይሆን የኦሮሞ ተናጋሪ ትግሬ እንዲሆን የተፈለገበት ዋነኛው ምክንያት ትክክለኝስዎቹ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ ህወሃት እምነት ስላጣ ይመስላል።

13 Comments on “የኦህዴድ ምክትል የሆነው ወርቅነህ ገበየሁ ማንነት ሲገለጥ”

  1. ወንድሜ እስካሁን ድረስ ኦረሞንም ሆነ አማራን ወይንም ሌሉቹን ጉሳዎች የጉሳዎቹ ተወላጆች አላስተዳደርዋቸውም አያውቁም አንዳንዶች በየጉሳወቹ ያሉ የሚመስሉህ ያው ለትግራይ ነፃ አውጪ ተቀጥረው አገራችንን አሁን አለችበት ደረጃ አድርስውናል በአጠቃላይ ወያኔ 25 አመት ኢትዮጵያን በማፍራረስ ትግራይን በመገንባት ላይ ይገኛል !!!

    • Enezihn teshuamiwoch ttgrie woyanie edmiewn lemarazem oromona amara adnet endaynorachew mokru bloachewal.

  2. መርዝ ለምን አትግተውም ነበር። አሁን ይሄን ወሬ ብለህ ታወራለህ እነዚያን የኢሃፓ ታጋዮች አሁን በህይወት ያሉ ይመስልሃል? የማትረባ ሰው ነህ ያውም ሰው ከሆንክ

  3. Why do Oromo Ethiopians tolerate these types of implants? This Gebeyehu guy is responsible for the crimes perpetrated against our Oromo brothers and sisters. He must and should be put out of his miserable life. Leaving these types of terrorists and treacherous is very dangerous. These types of “hoddams” and hood lumps should be eliminated if we want to protect our citizens and get respect, freedom, rule of laws, and democratic governance in our country.

  4. According to his friend narration, Ato Workneh looks untrustworthy,selfish and opportunistic person. Such individuals who exhibit such character are good for nothing. They always look loyal, as long as they get what they want. Betrayal is their trade mark. Loyality is not their strong position. Their strongest motive is to get what they want, even at the expense of their bosses.Individuals who possesses such personality are dangerously cruel, because, they want to prove themselves to the bosses.It is good to know.

    Ato Workmen was born in an Oromo region from Tegrian parents. Like anybody else he grew up in that locality enjoying everything what the social and physical environment offered. He speaks the language, adapted and exercise the culture. He is definitely an Oromo. Being a bad person, betraying the society he grew up with, I guess, totally different.
    In another argument, what is freedom, equality,justice,democracy and equal opportunity all mean. If we had freedom, equality and equal opportunity and,fair and democratic government,the questions of ethnicity:- from what parents, which region, what language we speak,what religion we follow, etc could have been irrelevant. We can not avoid such backward thinking,practices and political vices as long as the system that support. Let us not lose focus,aim on target, on our priorities.

  5. Woyane’s decision to appoint Workineh Gebeyehu over OPDO shows that Woyane has chosen to continue to disrespect Oromos. Workineh is not an Oromo and he has no business in the affairs of Oromo. Workineh is a member of Woyane and he is responsible for death and maiham of hundreds of thousands of Ethiopian Oromos and Amharas. Oromos should never trust this guy and his masters and handlers at TPLF. His assignment is to spie, report, control, kidnap, and murder each and every Oromo citizen that Woyanes think will oppose or challenge them. !Secondly, his assignment also include to spie, report, kidnap, and murder each and every member of OPDO. These types of manipulation of Woyane in OPDO and ANDM is not new. Woyane started these types of henious crimes from the beginning. Woyane selected and assigned people like Bereket Simon, Adissu Legesse, and others in ANDM and Abadula Gemeda, Kuma Demeksa, and others in OPDO. These slaves don’t have any type of self respec. They sold their souls to Woyane to do and die to do Woyane’s bidding of treasons and treachery and committing state sponsored terrorism against Ethiopian Oromos and Amharas. They are either half or full Tigreans and Ethiopians have to refuse Woyanes that they don’t want Woyane’s interference in their life and self administration.

  6. ከሱ የባስክ ወሬኛ አንተ ነህ አብርሀ በላይ እስከ ዛሬ ጠብቆ የክንፈ አማሙዋት ብሎ የጻፈው ተረት ነው የመሰለኝ። ሰዎቹን ያስገደልክ አንተ እንጅ ወርቅነህ አይደለም ከባድ ምስጢር መሆኑን አያወቅህ ምን እሱን ወሰደህ?ደግሞ መራራ ጉዲናን የሞራል ሰው አድርገህ ልታቀርብ ይዳዳሀል። እስከ ዛሬስ ምን አስጠበቀህ ወርቅነህ እስኪታሰር ነው?

  7. Dear Kinfe,
    I was shocked by the story of mr. Workineh. The oromo society doesn’t care about one’s ethnic identiy as far as the person is of moral standard. There is a saying in oromo “whoever take power as far as rule us in justice we dont go to palace” what is a pity is that opdo has a regulation that says any body who can speak afan oromo can be a member of the party and can participate in the oromo politics. so why Mr. workineh worried to change his grandfather’s name to oromo langauge? He was born and bred in Shashemene and he speaks oromo fluently and he has an oromo culture and world view. can’t he struggle for oromo being who he is with his tigre blood. Oromo is not racist we are accommodative . shame upon him for his deed.

  8. እኔን ኦሮሞ ያርገኝ ግን አሁን በርካታ የኦሮሞ ተወላጆችን በጅምላ ለመጨረስ በመስከረም 22 እሬቻ በአልን ኦህዴድ ላደራጀው ሰልፍ ለመበተን ሆን ተብሎ የተደረገ ቅድመ ምርጫ ነው ግን ይህ ሌባ ሰውዬ ይህን ማድረግ አይችልም ትግሉ የህዝብ ነው ህዝብ ያሸንፋል።

    ወያኔም ዛሬ ባወጣው መረጃ የቤት ችግር ያለባቸውን ህዝቦች በኔ አቅም ማስተናገድ አልችልም ብሏል እስካውን 11 አመት እጣው ያልደረሳቸው ባለእጣዎች 1ሚሊዬን በላይ ይገኛሉ ይህ ሲሆን የመሬት ወረራውን አቶ ወርቅነህ እኔ ፈታዋለሁ አይዞህ ህወሀት ነው የሚሉት?….በርካታ ሀሳቦችን እንዲጭር ይህን ካልኩ የማስተር ፕላን ሂደቱን ሆን ተብሎ በቤት ፈላጊ ፖለቲካ ሊያስታክኩት ይሆን?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*