በጎንደር ዩንቨርስቲ መምህራን የወያኔ ስብሰባን ላለመሳተፍ ኣድማ መቱ።
በጎንደር ዩንቨርስቲ መምህራን የወያኔ ስብሰባን ላለመሳተፍ ኣድማ መቱ።
#Ethiopia #Gonder #GonderUniversty #AmharaProtests #EthiopiaTeachers

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በጎንደር ዩንቨርስቲ መምህራን ሰብስቦ ለማስፈራራት ለማዘናጋት ለማታለል እንዲሁም በተለመደው የሃሰት ፕሮፓጋንዳና ኣብዮታዊ ዲሞክራሲ ለመጥመቅ ኣስቦት ሕወሓት የጠራው ስብሰባ በመምህራን ኣድማ ምክንያት መደናቀፉ ታውቋል።ወያኔ ካድሬዎቹን ብቻ ሰብስቦ ሊመጻደቅ ነው።
በዚህም መሰረት የጎንደር ዩንቨርስቲ መምህራን በከተማዋ ወጣቶች እየተገደሉ ከየቤታቸው ተይዘው እየታሰሩ ታፍሰው በየማሰቃያ ማጎሪያ ካምፕ እየታጎሩ ነዋሪው እየተንገላታና እየተሳቀቀ ስብሰባ የሚቀመጡአበት ኣንዳችም ምክንያት ባለመኖሩ እንዲሁም ከፍተኛ የታጠቀ ጦርና የደህንነት ኣካላት በከተማዋ ሰፍረው ሕዝብን ለማሸማቀቅ እየሞከሩ ስብሰባ ማካሄድ ከሞራል ኣኳያ ኣስፈላጊ ስላልሆነ ስብሰባው ላይ ላለመሳተው ውሳኔ ማሳለፋቸው ታውቋል። #ምንሊክሳልሳዊ