የሰማያዊ ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ እና የህግ ጉዳይ ኃላፊ ወጣት አዲሱ ጌታነህ ታሰረ።
ወጣት አዲሱ ጌታነህ ታሰረ።

የሰማያዊ ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ እና የህግ ጉዳይ ኃላፊ ሆኖ ሲሰራ የነበረው ወጣት አዲሱ ጌታነህ በፖሊስ ተይዞ ከአዲሱ ገበያ ወዳልታወቀ ቦታ ተወስዷል። የፓርቲውን አራት አባላት ከያዙ በኃላ አቶ አዲሱን አስቀርተው ሌሎችን ፈተዋል። ባለፉት ወራት መንግስት የሰማያዊ ፓርቲ አባላትን ያለ ምንም ምክንያት በማሰር ላይ ይገኛል። ይህንን ሌሎች ተመሳሳይ ጉዳዮችን አስመልክቶ ፓርቲው አስፈላጊውን ክትትልና ሪፖርት ያደርጋል።