በዐማራ ሕዝብ የተጠራ የሥራ ማቆም አድማ የለም!

በዐማራ ሕዝብ የተጠራ የሥራ ማቆም አድማ የለም!

ከመስከረም 9 እስከ 14 ቀን 2009 ዓ.ም በሕዝባዊ እምቢተኛነት ኮሚቴ የቤት ውስጥ የሥራ ማቆም አድማ በባሕር ዳር እና በጎንደር ተጠርቷል እየተባለ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው ወሬ ከዕውነት የራቀ ምናልባትም ወያኔዎች ወጣቱን በየቤቱ ለማፈስ የዘየዱት ሊሆን እንደሚችል በባሕር ዳርና በጎንደር ዛሬ ያነጋገርናቸው ሰዎች ገልጸዋል።
በዚህ ሰዐት የቤት ውስጥ አድማ መጥራት ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል። ትግሉ ከፍተኛ ደረጃ በደረሰበት በዚህ ሰዐት የቤት ውስጥ አድማ መጥራት ትግሉን ወደ ኋላ የሚጎትት ይሆናል።
ይህ ጥሪ የዐማራ ሕዝብ የማያውቀው ሲሆን ወያኔዎች በመከላከያ ሠራዊት፣ በብሔራዊ ደኅንነትና በፌደራ ፖሊስ የሚመራ ወጣቶን ማደን በጀመረበት በዚህ ጊዜ የቤት ውስጥ አድማ ተጠርቷል መባሉ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ተንኮል ወይም የኦፕሬሽኑ አካል ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል።

6 Comments on “በዐማራ ሕዝብ የተጠራ የሥራ ማቆም አድማ የለም!”

  1. እንኳን ሳምንት ቀርቶ ለምን ኣመት ሙሉ ቤትህን ዘግተህ ቁጭ ኣትልም? ረሃብ ሲሞሸልቅህ ሆድህን እያከክ ትወጣለህ።

  2. “ትግሉን እንዳይጎዳው” አልክ? ድንቄም ትግል። እስርቤት ገብቶ ተቃጥሎ መሞት የሚፈልግ ሰው የለም። “ፈሪ ለናቱ” ወይም “ጎመን በጤና” ብለናል።

  3. ጀግናው ጎንደሬ ለኣንድ ሳምንት የስራ ማቆም ኣድማ ማድረግ ኣቃተው!ድርብ ድርብርብ ውርደት ነው። የትግራይ ህዝብ ሥስት ኣመት ሙሉ በደርግ ተከቦ መውጫ እና መግብያ ኣጥቶ፣ ገበያ እንዳይወጣ ቀን ቀን ከላይ በኣይሮፕላን እየተደበደብ ጥርሱን ነክሶ ተወጥቶታል። እንደ ጎንደሬ ኣካኪ ዘራፍ ኣላለም፣ ሌሎችን ኤትዮጵያውን ወንድሞቹን ኣልተሳደበም፣ ኣልተመጻደቀም፣ ዘር ለይቶ ኣልገደለም ዘር ለይቶ ኣልዘረፈም። ለነገሩ በጎንደር ያጋጠመው ኣባቶች እንደሚሉት “ ልጅ ያቦካው ለእራት ኣይበቃም“ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*