ምህረቱ -ምህረት የሚሆነው ሁሉም የኅሊና አስረኞች ሲፈቱ ብቻ ነው [ግርማ በቀለ]
እንኳን ምህረት ለመባል ምህረት ለማድረግ ለሚከወን ጥናት ናሙና የማይበቁ ቀድሞውኑ ወንጀል ያልፈጸሙና ሊታሰሩ የማገይባቸውን ‹እስረኞች›ን በምህረት ስም በመፍታት ፕሮፖጋንዳ መስራት ፣ በ‹እሳት› ያለቁ ወገኖቻችንን ሃዘን በደስታ መለወጥ አይቻልም፡፡
እኛ ኢትዮጵያዊያን ‹ምህረት ተደረገ የምንለው› ሁሉም በነጻ አመለካከታቸው ፣ የህዝብ ወገኝተኛና ድምጽ በመሆናቸው፣ ሰብዐዊና ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀማቸው…. በአፋኝ ህጎችና በፈጠራ ተወንጅለው በህገወጥ መንገድ ለሥቃይ የተዳረጉ የኅሊና እስረኞች በሙሉ ያለአንች ቅድመ ሁኔታ ሲፈቱ ብቻና ብቻ ነው፡፡
ከዚህ ውጪ በተፈቱት ባንከፋም ሁሉም የኅሊና እስረኖች እስካልተፈቱ ምህረት ምህረት ተደረገ ብለን አንደሰትም፤ መንግስትን መሃሪ ለመምሰል በምህረት ሥም በሚነዛው ደረቅ ፕሮፖጋንዳ አንሳሳትም፣አንወናበድም፡፡
ከኅሊና እስረኞች አልፎ ሁላችንም ነጻነታችን እስከምንቀዳጅ ትግሉ በፈጣሪ ፈቃድ እስከድል ደጃፍ ይቀጥላል፡፡ ወደፊት//
በ2009 በድል እንገናኝ፡፡ የ2008 መጨረሻ ቀን፡፡ UNITE