ከወሎ የአማራ ተጋድሎ የጎበዝ አለቆች ግብረኃይል የተሰጠ መግለጫ !!
ከዚህ በታች ስማቸሁ ለተጠቀሱ የአማራ ከተሞች፣ የገጠር ቀበሌዎችና ገበሬ ማህበራት ነዋሪዎች በሙሉ፡-
እንደሚታወቀው በጎንደር እና በጎጃም ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ የአማራ ተጋድሎ የጎበዝ አለቆች ትግሉን አሁን በደረሰበት ራስን ነጻ የማውጣት ደረጃ አድርሰውት ይገኛሉ። ይሁንና አፋኙና ገዳዪ የትግሬ ነጻ አውጪ ቡድን በተለይም በወልድያ፣ በደሴ፣ በኮምቦልቻ፣ በከሚሴ፣ በሸዋሮቢት፣ በደብረሲና ደብረብርሃን ከተሞች፡ከተማዎቹ መተናፈሻ ከተሞች ከመሆናቸው ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ነፍሰ በላ የአግአዚ ወታደሮችን በማስገባት ቀላል የማይባል ቁጥር ያለው ህዝባችንን በማፈን ወደ ማይታወቅ ቦታ እየወሰደ መሆኑን ኗሪው ራሱ ምስክር ነው። እስከ ዛሬው ዕለት ይኸው አፈና ቀጥሏል።
ስለዚህ አንድም ግፍና በደላችን ያበቃ ዘንድ፤ ሁለትም የጎንደርና የጎጃም ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት የእኛው ጉዳት ስለሆነ እኛ የወሎ የአማራ ተጋድሎ የጎበዝ አለቆች የሚከተለውን አስቸኳይ መግለጫ አውጥተናል፤
በወልድያ፣ በደሴ፣ በኮምቦልቻ፣ በከሚሴ፣ በሸዋሮቢት፣ በደብረሲናና በደብረብርሃን ከተሞችና አካባቢዎች ላይ ከእሁድ ነሐሴ 29/12/2008 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ጷግሜ 2/2008 ዓ.ም. ድረስ የሚቆይ ከቤት ያለመወጣት አድማ ታውጇል።
በተጠቀሱት ከተሞች ላይ ይህንን አድማ ተግባራዊ የማያደርግ ማንኛውም ግለሰብ በጎንደርና በጎጃም በወያኔ ጥይት የፈሰሰውን የወገኖቻችንን ደም እንደመርገጥ ስለሚቆጠር ከመድኃኒት ቤቶች በስተቀር በተጠቀሱት ቀናት ውስጥ ማንኛውም ዓይነት ንግድ ቤቶችም ሆነ አውቶቡስ፣ ሚኒባስ፣ ባጃጆችና ሌሎችም እንቅስቃሴዎች ቢኖሩ በሚከተለው እርምጃ ማንም ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን ከወዲሁ እንገልጻለን።
የአማራ ተጋድሎ የወሎ የጎበዝ አለቆች ግብረኃይል
( Achamyeleh Tamiru )