በአሁኑ ሰዓት ደብረማርቆስ ከተማ በአጋዚ ወታደር መወረሯ ታወቀ

በአሁኑ ሰዓት ደብረማርቆስ ከተማ በአጋዚ ወታደር መወረሯን መረጃ ደርሶናል፡፡ ከፍተኛ ውጥረት ላይ ትገኛለች፡፡ ማርቆስን ጥቁር ደመና ተጭኗታል፡፡ ህዝቡ በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ ለአጋዚ ወታደር የምግብና የመጠጥ አቅርቦት የሚሰጥ ሆቴል ካለ ህዝቡ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ አስጠንቅቋል፡፡ ባለፈው በተደረገው ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ የትልቅ ሆቴል ህዝባዊ ወገንተኝነቱን ወደ ጎን በማለት የሰረታው ስህተት ዋጋ እያስከፈለው ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ዋናው […]

3 Comments on “በአሁኑ ሰዓት ደብረማርቆስ ከተማ በአጋዚ ወታደር መወረሯ ታወቀ”

  1. እናንተ ቂሎች፣
    ይህ እኮ የመከላከያ ሰራዊት ነው። ሚሊሽያ ወይም እንደ ድሮው ታጋዮች ከህብረተሰቡ እየለመኑ ምግባቸውን የሚያገኙ ይመስላችኋል?
    የራሱ የሆነ ስንቅና ትጥቅ ያለው፣ አቅራቢውም ማዕከላዊ የሰራዊቱ የሎጅስቲክስ ክፍል አለ።
    ስለዚህ ሌላ የሚሰራ ስራ ነው መስራት ያለብን እንጅ፣ ለሰራዊቱ ምግብ እና ውሃ የሚሰጥ እናሳያችኋለን ፉከራ ትርጉም የለሽ ብቻ ሳይሆን የበለጠ ሰራዊቱን ወገንተኝነቱ ወደ አገዛዙ እንዲሆን እያደረግነው መስሎ ይሰማኛል።
    የባላንጣን አቅም አሳንሶ ማዬት ደግሞ ጥሩ አይደለም እና ባለን ጠንካራ ነገር እየገነባን የጎደለንን ለመሙላት ጥረት ማድረግ ተገቢ ነው።
    የሌለውንና ያልተደረገውን መስጠት ደግሞ ዉሎ አድሮ ትዝብት ላይ ከመጣል ባሻገር ተኣማኒነትን ጥያቄ ውስጥ ያስገባልና ይታሰብበት።
    ትግሉ አመራር ቢኖረው እየተረዳዱ ስራዎችን ባግባቡ መፈጸም ያስችላልና አገር ውስጥ ያላችሁ የተቃዋሚ አመራሮች ወጥ የሆነ አካሄድ እስከሚደራጅ፣ ቅድሚያዉን በመውሰድ ትግሉን በማፋጠንና መልክ በማስያዙ ዕገዛ ብታደርጉ ጥሩ መስሎ ይታየኛል። ምክንያቱም ወጣቱ በስሜት እና እልህ ብቻ ሲጓዝ ጉዳቶች እንዳይበዛበት አዛውንቶቹ መስመሩን ቢያስይዟቸው መልካም ነው።
    ወያኔም ጊዜው ሳያልፍባችሁ ከህዝባችሁ ጋር ዕርቅ አድርጉ።

    እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ።

  2. የአሜሪካ ወታደር ሁኘ ሰርቻለሁ ። ትጥቅ፣ ጥይት፣ዉሃና ምግብ ይዘን ስንሄድ የነበረው ለ ሶስት ቀን የሚሆን እንጂ ለሳምንት እንኩአን የሚሆን አይደለም። ዋናው ነገር ሌላ አቅራቢ የ “support battalion, for fuel, MRE (Meals Ready to Eat), water, ammunition” ካለ ችግር አይኖርም። መፍትሄው የነሱን መንገድ መዝጋት ነው። እኛም መገናኛ ድልድይ አና መንገድ ማፍረስ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*