ስፖርታችን አደጋ ላይ ነው ጥያቄያችን ምላሽ እስካላገኘ ድረስ ጉዳዮን እስከ አለምአቀፍ የአትሌቲክስ ፊዴሬሽን(IAAF) ድረስ ለመውሰድ እንገደዳለን

“ይሁንታ አግኝተን ከተመረጥን ለመምራት ዝግጁ ነን፡፡”- አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ

by

image

በዳዊት ፀሀዬ|ነሀሴ 19፣2008

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ጋዜጣዊ መግለጫ ዛሬ ከሰአት በብሔራዊ ሆቴል ተካሄደ፡፡

ጋዜጣዊ መግለጫውን ላይ የተገኙት ጋዜጣዊ መግለጫውን የጠራውን የኢትዮጵያ አትሌቶች ጊዜያዊ ኮሜቴን በመወከል አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ ፣አትሌት ገብረግዜአብሔር ገብረማርያም ፣አትሌት ገዛኸኝ አበራ ሲሆኑ ከነሱ በተጨማሪ እንዲሁ አሰልጣኞችን በመወከል ደግሞ ሻምበል ቶሎሳ ቆቱ እና የኦሜድላው አሰልጣኝ ኮማንደር አበበ በስፍራው በመገኘት ጋዜጣዊ መግለጫውን ሰጥተዋል፡፡

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ በርካታ ጉዳዮች ተነስተዋል ከነዚህም መካከል ስለ ኢትዮጲያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አሰራር ፣ዶፒንግ፣ከአትሌቶች አሰለጣጠን ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በዋናነት አፅንኦት ተሰጥቶባቸው በስፋት ሀሳብ ተንሸራሽሮባቸዋል፡፡

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ከተሰነዘሩት ሀሳቦች ውስጥ

ስለ ጋዜጣዊው መግለጫ አላማ አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ ሲናገር
“በዛሬው እለት እዚህ የተገናኘነው ስለሀገራችን ኢትዮጵያ ወቅታዊ የአትሌቲክስ ሁኔታና እና ስለወደፊቱ የአትሌቲክሳችን እጣ ፈንታ ለማውራት እንጂ እከሌን ከስልጣኑ ለማውረድ ወይም ለመፈጥፈጥ አይደለም ፤ ስፖርቱ በሽፍንፍኖሽ የሚታለፍ አይደለም እንዳለፈው የሪዮ 2016 ኦሎምፒክ እንጋለጣለን ምክንያቱም አትሌቲክስ በሚሊዮኖች ፊት የምኖረጠው  ከሀይማኖት እና ፓለቲካ የፀዳ ስፖርት ስለሆነ፤ ስለዚህ እንደኔ ሀሳብ የዛሬው ውይይታችን ሁሉንም ስፖርት ሊታደግ ይችላል በሚል እምነት የተጠራ ነው፡፡” ሲል ገልጿል፡፡

አትሌት ሀይሌ ይቀጥላል
“የዶፒንግ ጉዳይ በአፋጣኝ ምላሽ ባለማግኘቱ የተነሳ ብዙ ዋጋ እያስከፈለን ይገኛል፤ ጉዳዩ ሊያስቀጣን ይችል ነበር እዚህ ጋር አለመቀጣታችንን አትዩ ለምሳሌ ከዚህ ቀደም የአለም አቀፍ ፀረ አበረታች መድሀኒት ኤጀንሲ(ዋዳ) በራሱ ከአትሌቶቻችን ናሙና እየወሰደ ይመረምር ነበር አሁን ግን ራሳችንን በአንድ ናሙና እስከ 500የአሜሪካን ዶላር እየከፈልን ናሙናዎችን ወደ ኳታር እየላክን እናስመረምራለን፡፡ የዚህ የዶፒንግ ጉዳይ መዘዝ እስከ ሪዮ ኦሎምፒክ ድረስ ተከትሎን ሄዷል ፤አትሌት አልማዝ በ10ሺህ ሜትር በጥረቷ እና በላቧ ያመጣችውን ውጤት ጥርጣሬ ውስጥ እስከመክተት ድረስ ደርሷል፡፡” በማለት ተናግሯል፡፡

ስለ ሪዮ ኦሎምፒክ አትሌቶች የምልመላ ሂደት አትሌቱ ሲናገር
“ስለ አትሌቶቹ ምልመላ ከዚህ ቀደም እጅግ በርካታ ጊዜ አውርተናል፤ መስፈርቱ የወጣው በርካታ አትሌቶች ውድድሮቻቸውን ሮጠው ከጨረሱ በኃላ ስለነበር ነው ከዚህ ቀደም ከኦሎምፒኩ በፊት እንደዚያ ስንቧቀስ የነበረው፡፡” በማለት ተናግሯል፡፡

በሪዮ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን ወክሎ ሰንደቅ አላማውን ስለ ያዘው ግለሰብ ሀይሌ ሲናገር
“ባንዲራ ስለያዘው ሰው ጥቂት ሰው ነው የሚያውቀው ፤ቀነኒሳ በቀለ እና ደራርቱ ቱሉ ሲይዙ እና አንድ ሌላ ሰው ሲይዝ በጣም ልዮነት አለው፤ለምሳሌ ስለ ቀነኒሳ ገድሎች ኮሜንታተሩ ሲያወራ የአለም ህዝብ ሰፍ ብሎ ያያል ይህም በተዘዋዋሪ ሀገሪቷን በደንብ ያስተዋውቃል፡፡”በማለት መልሷል፡፡

በመጨረሻም ሀይሌ እንዲህ ሲል ተደምጧል

“በአትሌቲክሳችን ውጤት ማጣት እናንተ ከሚሰማችሁ ስሜት በብዙ እጥፍ ተባዝቶ እኛን ይሰማናል፤ ስፖርታችን አደጋ ላይ ነው ሙያተኛው ከሌለ ሙያው አይመራም ፤በኛ በኩል ያለው አቋም እስከመጨረሻው ገፍተን እንሄዳለን የሚል ነው ፤ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ተጠርቶ ክልሎች የሚልኩት በስፖርቱ ያለፈ እና ለቀጣይ የሀገሪቱ አትሌቲክስ ተገቢ የሆነ ሰው እስኪሆን ድረስ ትግላችን ይቀጥላል ፤ ይህንን ስንል ግን እኛ ሙያተኞች ሆነን አይደለም፤ ነገርግን ጥያቄያችን ምላሽ እስካላገኘ ድረስ ጉዳዮን እስከ አለምአቀፍ የአትሌቲክስ ፊዴሬሽን(IAAF) ድረስ ለመውሰድ እንገደዳለን ነገርግን ጉዳዮን ወደዛ መውሰዱ ብዙ መዘዞች ስላሉት እኛ እዛ ደረጃ ድረስ እንደርሳለን ብዬ እንኳ አላስብም ከዛ በፊት በመግባባት ሊፈታ ይችላል ብለን እንጠብቃለን ፡፡የኛ ሀሳብ አሁንም ችግሩ ያለው አሠራሩ ላይ ሳይሆን ሂደቱ ላይ ነው፡፡” ሲል ተናግሯል፡፡

በመጨረሻም ሀይሌ ገብረስላሴ ከተለያዩ ጋዜጠኞች የተነሱለትን ጥያቄዎች መልሷል፡፡

ከነዚህም መካከል ከአንድ ጋዜጠኛ የአሁኑ ፌዴሬሽን እንዳላችሁት ስልጣኑን ቢለቅ አትሌቶች ለመምራት ዝግጁ ናችሁ ወይ ተብሎ ለቀረበለትን ጥያቄ ሲመልስ

“ይሁንታ አግኝተን ከተመረጥን ለመምራት ዝግጁ ነን፤ በኛ በኩል እንደነ አትሌት ሚሊዮን ወልዴ እና አሰፋ መዝገቡ የመሳሰሉ ባለሙያዎችን ለቦታው ብቁ ናቸው ብለን እናስባለን፡፡ “ሲል ተደምጧል፡፡

14 Comments on “ስፖርታችን አደጋ ላይ ነው ጥያቄያችን ምላሽ እስካላገኘ ድረስ ጉዳዮን እስከ አለምአቀፍ የአትሌቲክስ ፊዴሬሽን(IAAF) ድረስ ለመውሰድ እንገደዳለን”

  1. ሀይሌ አፍህን አትክፈት ኢትዮጵያ ባሁኑ ጊዜ ስለስፖርት የምታወራብት ሁኔታ ላይ አይደለችም።ዝንጀሮ እንኩአን መጀመሪያ የመቀመጫየን አለች አሉ ሰለዚህ አገር ከስፓርት የቅደም። አትንበላጠጥ

  2. In history of Ethhiopia olympic the worst rank, the rio olympic 2016 , rank 44th this was due to all sport federations in Ethiopia like politics controlled by woyane.

  3. HAILE G. Stop your rubbish propaganda we know you very well what you have done with the criminal Meles Zenawi against KINIJIT IN 2005 as being a mediater member or part of reconcillation.

  4. This is obvious an arranged press release by TPLF to divert the attention of the Addis from the current burning issue to the faild athletics. I bet its Gebreigziabeher G/Mariam who initiated the press release! But,they had to appear a wolf in sheep’s clothing so that they used hodam and banda Haile as they always do.

  5. አሁንም በዚህ አንተ ሰዓት ስለ ስፖርት ታወራለህ ማፈሪያ፡ ጀግናው ፈይሳ ለሊሳ ሪዮ እንዳንተ ሩጫ ብቻ አይደለም ያሸነፈው የኢትዮጵያን 85 ሚሊዮን ህዝብ (ስለ ቁጥሩ ይቅርታ አንተንና መሰል ሆድ አደሮችን ቀንሸ ነው) ልብና የአለምን ትኩረት አግኝቷል አሸንፏል። ታሪክ ሰርቶአል። አንተ ግን መቸ ነው ወገንህን ዘወር ብለህ የምታየው። ከስርአቱ ጋር አብረህ መውደቂያህ ደርሰዋል እና ሩጫህ ወደ መቀሌ ወይስ ወደ አርሲ ቆም ብለህ አስብ እንደለመድከው በሆድህ ወይም በእግርህ ሳይሆን በጭንቅላትህ ብታስብ ይሻልሃል።

  6. Vagabond hooligans do not open your toilet stinky mouth at Ethiopia’s icon runner. You are good at fabrication of lies and we enjoy it. Do not mess in the areas of you donot have the skill. Now, tell us what is happening in Gonder and Gojam. Share us your credible information how many woyanes died and captured. Yesterday I read in this forum the opposition has fighter jets like SU 29 and tanks. Please confirm if this is true? if it is true our sacrifice will be minimized and victory will be very near.
    You have not told us about Dr. Berhanu? We heard he was kicked out from Arbenyoc Ginbot7. Please check with your reliable reporters in Eritrea to update us on his condition. The whole of Gonder, Gojam, wollo and north Shewa are liberated and Woyane will collapse in four weeks. Dr. Berhanu has to arrive Addis jubilantly after all these difficult years, fighting on behalf of us, to be Prime Minister. One reservation I have on the “revolution” is looting. Teach the people of Gonder to stop looting and stealing that do not belong to them. looting in 21st century is a reflection of backwardness.

  7. የጉድ ሀገር !!!!
    ቅዱሥ መዕሀፍ ” እንዳታሥተውሉ አዚም ያደረገባችሁ ማነው ” ይላል ። የቀድሞ ፕሬዝዳንት ” ወርቅ ለነጠፈ ፋንድያ ” የሚል ነገር አንብቤአለሁ ። እንዲት ነው የምናሥበው ? በምንሥ ነው የምንደሠተው ? የፈለገ ብንበደል በምን ( ሞራል ) ነው የሀገራችንን እንቁ የሆኑ ዜጎቻችንን ለመሣደብ ድፍረት ያገኘነው ? ምን በደሉ ? ምን አጠፉ ? የሀገራችን ሥም ጠፋ ! በአለም ተዋረድን ! ህዝቡ የሚጠብቀውን ውጤት አጣ ! ሥለዚህ ግዜአችንን ሠውተን ሀሣባችንን ለመንግሥት እናሣውቅ አሉ መንግሥትም ጆሮውን ሠጠ ውይይቱ ቀጠለ ።
    ዛሬ ሀገራችን በአለም እንድትታወቅ ያደረጉንን ክዋክብት መሣደብ አሣፋሪ ነው ። እርግጥ ነው ማንም ሠው ሀሣቡን የመግለጽ መብት አለው እኔም ትንሽ ልበል ።
    እነዚህን ተሣዳቢወች በ3 ከፍሎ ማየት ይቻላል
    ሀ ፦ ለኢትዮጽያ ምንም ፍቅር የሌላቸው ውርደቷን የሚወዱ
    ለ ፦ በጭፍን ጥላቻ
    ሐ ፦ ያለችሎታ በዘመድ አዝማድ ጥቅማ ጥቅም የተወታተፉ የተከበረውን ፌዴሬሽን ለሆዳቸው መሙያ ያደረጉ ናቸው ብዬ እገምታለሁ ። መብቴ ነዋ !!
    እንደውለመሆኑ ተሣዳቢዎች ሆይ የአምሥት ደቂቃ መንገድ 25 ደ.የምትቆሙ ሥንፍና እጅና እግራችሁን ሠንጎ ከጀግናው ሃይሌ ምጽዋት የምትጠብቁም ትኖራላችሁ መጻፉም የሚለው ” ያልሠራ አይብላ ” ነው ። እነሡ በዘረጉት ( ኢንቬሥት መንት ) ሥንት ዜጎቻችን እንጀራ እንደሚበሉ ዘነጋችሁ !! ይቆየኝ ወደማይመለከተኝ አሥገባችሁኝ ። ወደ አትሌቲክሡ ልግባና ለተሣዳቢውች ጥቂት ፍንጭ ልሥጥ ። አትሌቲክሣችንን የሚያተራምሡት እነማን ናቸው ??
    1ኛ.መቼም የኢትዮጵያን ማረሚያ ቤቶች ሥፓርት ክለብ እነ ደራርቱን ፣ ጡርየን ፣ ሥለሽን ሌሎችንም ብርቅየ አትሌቶች ያፈራ ከለብ ዛሬ የት አለ ! ማን ገደለው ! የዘመዳሞች ጥርቅም ሆኖ እንደውም ” ሁሤን ሽቦ እና ቤተሠቡ ሃላፊነቱ የተወሠነ የግል ማህበር ” እሥከ መባል የደረሠ ሥንቱን አትሌት አማሮ ከሀገር ያሠደደ ዛሬ አይኑን በጨው አጥቦ የብሄራው አሠልጣኝ ሆኖ አንገታችንን አሥደፋን !! እንዴት አንድ አሠልጣኝ ( ሞ ፋ ራ ንን ) አንችለውም ብሎ መግለጫ ይሠጣል ? አትሌቱ ተሸንፎ ነው የሄደው !! ሥነ ልቦናቸው በመጎዳቱ ። በርግጥ በግምገማ ከማረሚያ ቤት ባረርም በመተካካት À€á“ሊሢ ወንድሙን ተክቶ በነ ዱቤ ሠበብ ወደ ብሄራዊ ተጠጋ አንድ በሉ…
    2ኛ. ሙገር ሢሚንቶ ሥፓርት ክለብ ይህ ክለብ ተሥፋዬ ቶላን ፣ ተሥፋዬ ጅፋር ፣ ቀነኒሣ በቀለ ፣ ገዛኽኝ አበራ ፣ ዘነበች ቶላ ( ባህሬን ..መሪማ ጀማል ) ሌሎችንም ያፈራ ነበር ዛሬ የሚሠለጥነው በመላኩ የሚሠለጥን ነው ክለቡ ይኑር አይኑር አሁን መረጃ የለኝም ሙገርን ሥለገደሉ የብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ሆነው የዱቤ እና የዶ’ር እርግጠኛ ባልሆንም ይልማ ቡድን ሥለነበሩ ዶክ ከዱቤ ጋር ሢለቁ ማራቶንን ይዞልን ብራዚል አቀኑልን ። ሁለት …
    3ኛ . ኦሮሚያ ፓሊሥ ሥፓርት ክለብ እጅጋየሁ ዲባባን ፣ ማርቆሥ ገነቴን ሌሎችንም ያፈራ ዛሬ በ ቶሌራ እጅ ወደቀ ሥንቱን ለዝሙት ጠይቊል ሥንቱሥ ተማሮ ሀገር ጥሎ ኮብልሏል ዛሬ ብሄራዊ አሠልጣኝ ሆነው ብራዚል ሄደዋል
    4.ኛ አቶ አድማሡ የኮተቤ መምህር ሢሆኑ የት አሠልጥነው አትሌት እንዳወጡ ባላውቅም ዘመዳቸው አቶ ተሾመ ጉዋደኛቸው ብዙአየሁን ይዘው ብራዚል ሌሎችም ..
    5ኛ .ለአንድ አትሌት ሁለት አሠላጣኝ መሄዱንም ሠማን ሀገራችን አደገች!!” ነገሩ ወዲህ ነው አትሌቷ የኔ ነች የኔ ነች ተባብላው የሚጣሉበት የኛ ፌደረሽን አሣየን እሷም አቊረጠች አትሌቷ ትግሥት ቱፋ ሥትሆን አሠልጣኞቹ ሀጁ እና ይረፉ እንደሚባሉ ሠምተናል 2ቱም ብራዚል ሄደዋል
    6ኛ.ቢጫዎቹ እነ ፋጡማ ሮባ ፣ ሀይሌ ገ’ሥላሴ ፣ ሀይሉ መኮንን ፣ ጌጤ ዋሚ ፣ መሥታወት ቱፋ ሌሎችንም ያፈራ ኦሜድላ የት ገባ ማን ገደለው ዛሬ በሥፓርት ክለቡ ሥጋዊ ፍላጎታቸውን አርክተው በፌዴሬሽን ሥር የሚርመጠመጡትን አናውቅም ? ከርእሡ ጋር ሥለማይሄድ ልለፈው ..
    7.ኛ.ለዘመናት ከዶክተር አያሌው ጋር በወጌሻነት የማትለየውን ልምድ ያላትን ሥሟን ዘነጋሁ አሥቀርተው በመተካካት ፓሊሢ አቶ ዱቤ ልጃቸውን ተክተው ብራዚል ልከዋል !!
    8ኛ.. በአሁን ሠአት መብራት የነ መሢ ፣ሚልዮን ..ባንክ እየከሠመ ባለበት ሠዓት እየተውተረተረ ላለመውደቅ እየታገለ ያለው መከላከያ አትሌቲክሥ ክለብ ነው !! እሡም ቢሆን አመራሩ እሥከ ታች ወርዶ የአትሌቱ ችግር ማድመጥ አለበት ያለበለዝያ የአንድ ወገን ሪፓርት የሚሠማ ከሆነ የማረሚያ ቤቶች እጣ እንዳይገጥመው አልማዝ አያና
    ሌሎችም ለም ይለቃሉ ሊያሥብበት ይገባል እላለሁ ።
    8ኛ.. ፌዴሬሽኑ ን እነ ሃይሌ ተሠባሥበው ለመወያየ ያበቃቸው ሥር የሠደደ ብልሹ አሠራር ከንክኖአቸው ፣የሞያ ፍቅር አንገብግቧችው ፣ ዳቦየበሉበት ቤት ሥለሆነ፣ ለሃገራቸው የውጭ ምንዛሪ እንድታገኝ የኢትዮጽያ አምባሣደር በመሆናቸው ፣ መንግሥትም ቤተ መንግሥት ጠርቶ አደራ የሚላቸው ተቃዋሚ ወይም ደጋፊ ሥለሆኑ ሣይሆ ምያቸው ክብር እንዳለው በማወቁ እንጁ የሚበላ የሚጠጣ ፈልገው አይደለም ለሆዳቸውማ ተጠግተው ለመንግሥት ታማዝን ነኝ ባዮቹማ መንግሥትን ከህዝብ የሚያጋጩ ለ10 ሽህ ብር ህሊናቸው የሸጡ የውሃ ዋና ፌዴሬሽናችንን ወንድሞቻችንን አንዘንጋ ።
    ወደ ነገሬ ልመለሥ እናም እነ ሀይሌ የተነሡት በኔ እይታ በቅንነት ነው ። ፌዴሬሽኑ ደሞ የሚያላክከው አልተማሩም ባይ ነው እነሡም ኮተቤዎች በጠበጡ ነው ለመሆኑ ኮተቤዎች ማናቸው ?
    አትሌቲክሥ በተማረ ባለሞያ ይመራ ሢባል ብዙ የተማሩ ለሞያው ፍቅር ያላቸው ሥፓርቱን አበጥረዉ የሚያውቁ የሚይሥጠጋቸው አጥተው በዩንቨርሥቲ ፣ ክፍለከተማው ሌሌችም በውጭ ሀገር ተማረው የተሠደዱም አሉ መቸም ኢትዬጵያ የወላድ መሀን ሆና እንጅ እነ ፍቅሩ ኪዳኔ ፣ ኮማንደር አይናለም ፣ ዶክተር በዛብህ ፣ ሻምብል ቶሎሣ ቆቱ አቶ ካሡ ሌሎችም እያሉ ኮተቤ ለምን አሥፎከረ ዶክተር በዛብህ በሥፓርት ሣይንሥ ዘርፍ ፣ ዶክተር አሸብር ዶክተር ንጉሤ ፣ ረዳት ፕሮፌሠር አያሌው አትሌቲክሥ ፣ አቶ ተሾም ( ሜቶዶሎጁ) አቶ ሙሉነህ ቅርጫት ኲዋሥ አቶ መብራቱ ጅምናሥቲክ በነበሩበት ሠአት በኢትዮጵያ ውሥጥ የመጀመሪያው የጤ.ሠ.ማ ኮሌጅ ነበር ዛሬ ሁሉም ለቀዋል ከአቶ ሙሉነህ በሥተቀር እነሡ በነበሩበት ዘመን ማንም ዘሎ የሥፓርት መምህር አይሆንም ለምሣሌ ዶር በዛብህ ተወዳዳሪ ነበሩ ዛሬም በጣም ጥሩ መምህራን አሉ እናም ወረቀት ሢባል በጣም ጎበዝ የጅምናሥቲክ መምህር አድማሡ የተለያዩ ኮርሥ ወሥደው ከነአቶ ዱቤ ተዋወቁ ልብ በሉ አቶ ዱቤ ዲፕሎማቸው የምን እንደሆነ ባይታወቅም ቀጥታ ድግሪ ተመረቁ ለዚህም በፌዴሬሽኑ ፈላጭ ቆራጭ ሁኑ ለዚህም ውለታቸው አለምን ዞሩ አቶ ቶሌራም ከሥፓቱ ጋር የማይገናኝ ዲፕሎም ይዘው ከተፍ አሉ ድግሪአቸውን ገዝተው ሁለቱም ከአዲሥ አበባ ዩንቭርሥቲ ዶክ ይልማ ነበሩ ልብ ይበሉ በወቅቱ ዶክተሩ የብሄራዊ ቡድን አሠልጣኝ እና የነ ዱቤ ወዳጅ ነበሩ ማሥተርሥ ተያዘ ፌዴሬሽኑን ተቀላቀሉ ። በመማራቸው በጣም አደንÀ€á‰ƒá‰¸á‹‹áˆˆáˆ ግን ፍሬው ምንድንው ትላንት የት ነበሩ ? አሥገራሚው ነገር ዳሞ አቶ ሁሤን ሽቦ ጒዳቸውን ተማምነው ይመሥላል ሣይሸምቱ አይቀሩም መሠለኝ ፌዴሬሽኑ በተማረ ሠው መመራት አለበት ብለው የዲፕሎማይሁን ድግሪ ፊርማቸው ሣይደርቅ ትችት ጀመሩ አሉ !”ለመሆኑ የኮተቤው ሚሥጢር ይህ ይመሥለኛል ለምን አዲሥ አበባ ዩን.አይማሩም ??
    በዚሁ አጋጣሚ ለአትሌት ንጉሴ ጌቻሞ ትልቅ ክብር አለኝ ምርጥ የብሄራዊ ቡድኑ እኗ የማረሚያ ቤት 100 ሜ.አትሌት ነበር አሁን ኮተቤ መምህር ናቸው አጭር ርቀትን መካከለኛ በእነ መሓመድ አማንን አሣይተዋል ምክንያቱ ሮጠዋ በሣይንሡ ተደግፈው አጭር ርቀትን ላይ ተሥፋ እንዴፈነጥቅ አድርገዋል
    ጽሁፌን ሣጠቃልል በየዋህነት በአትሌቱ ላብ ፎቅ የሠራችሁ ፣ ሀገሪቷን አንገት ያሥደፋችሁ ፣ እናቃለን ካላችሁ ታች ወርዳችሁ አሠልጥናችሁ እምጡልን አሁን አትሌቱ ተንግሽግሿል ፣ከፋፍላችሁታል ይብቃችሁ ቆይ ከአንድ እንጀራ በላይ አትበሉ የሠውሥ ፊት ለምን ይግረፋችሁ !!!
    የተከበራችሁ አትሌቶች ምንም አታችሁ እንዳልሆነ የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ ያምናል እናም ሁሉም ኮተቤ የተማረ አይችልም ብላችሁ አትደምድሙ ።
    የኢትዩጵያ መንግሥት ሃላፊነት አለበት እሡ በሚመራው ሃገር እንዲህ አይነት የተቡካካ አሠራር መፈተሽ አለበት የፓለቲካ ሃላፊነቱን በመምራት ሌላው በባለቤቶቹ ይመራ እላለሁ ነብሣቸውን ይማር በእነ አቶ አሠፋ ማሞ ግዜ መች እንዲህ አይኑን ያፈጠጠ ችግር ታዬ ።
    ሥለዚህ ከመሣደባችን ይልቅ የሀገራችንን ጀግኖች እናወድሥ !! ሥፓርት ኮምሽንም ዝም ብሎ ይቀመጣል ብዪ አላሥብም ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ ሢዘም ዝም ብሎ ማየቱ መልካም አይደልም እላለሁ ።

    እጅ ለእጅ ተያይዘን ሥፓርታችንን ከወደቀበት እናንሣት !! ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!!

    1

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*