ኢትዮጵያ አሁን የሚያስፈልጋት ሰላም ነው ወይስ ፍትህ ? – ፓስተር ዳንኤል ጣሰው

ኢትዮጵያ አሁን የሚያስፈልጋት ሰላም ነው ወይስ ፍትህ ? – ፓስተር ዳንኤል ጣሰው

ሀገራችን ከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ ገብታለች።ምንም እንኳ በታሪካችን ብዙ መከራዎችንና የርስ በርስ ግጭቶችን ያሳለፍን ብንሆን እነዚያ አሁን መደገም አለባቸው ማለት አይደለም። እንዲያውም ካለፈው ተምረን በ21ኛው ክፍለ ዘመን ወደ ኋላ መመለስ አይገባንም። በተለይም ሀገራችን የአፍሪካ መኩሪያ እንደመሆኗ ባሁን ሰአት እየሆነ ያለው ከኛ የሚጠበቅ አይደለም።

ኢትዮጵያ ታማለች፤ፈውስ ያስፈልጋታል። ከዚህ አንፃር የሃይማኖት መሪዎች የበሽታው ሳይሆን የፈውሱ አካል መሆን ይጠበቅባቸዋል። በጥበብ የተሞሉት ዮሴፍና ዳንኤል የዓለም መንግስታትን አማክረዋል፤በጎውንም መንገድ አሳይተዋል።

ምነው በኛ ጊዜ ጠፉ? ያን ጊዜ የረዳቸው በነርሱ ያደረ የአምላክ መንፈስ ዛሬም ህያው ነው።

“የምድር ጨው የዓለም ብርሃን ሁኑ” ምን ማለት ነው? ጨውነታችን እኮ ለምድር ነው፤ለሰማይ አይደለም።

ብዙዎች “ሀገሬ በሰማይ ነው፤ይሄ ምድር ያልፋል ዋጋ የለውም” በሚል ድሆችን ከመርዳት፤ለፍትህና ለሰላም ድምጽ ከመሆን ሲሸሹ ይታያል። ቃሉ “ፍርድ ለተጓደለበት ተምዋገት” ይላል፤”ተርቤ አላበላችሁኝም፤ታስሬ አልጠየቃችሁኝም” ይላል። እኛ እስረኞች የምንጠይቀው ወይም የፍርድና የፍትህ መጓደል የሚታወቀን የኛ ዘመዶች ሲታሰሩ ብቻ ነው መሰል። እነዚያን እኮ “ከእኔ ሂዱ” ነው ያላቸው። ይሄንን ሁሉ ዘምረን፤ሰብከን፤ተሯሩጠን አገልግለን “ከእኔ ሂዱ” ከመባል ይጠብቀን። አንድ የሃይማኖት ድርጅት ለማስፋፋት እኮ አይደለም ጥሪያችን፤ይልቁንም ለሰው ልጆች ፍቅር እንድናሳይ እንጂ። የወንጌሉ ምርጥ ጥቅስ “ዓለሙን ወዷልና” አይደል የሚለው? ስብከቱ ይደርሳል መጀመርያ ፍቅር ለህዝባችን እናሳይ። አለበለዚያ “እኔ የምወደው የኔን ድርጅት አባሎች ብቻ ነው” ይመስላል።

አሜሪካዊው የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ማርቲን ሉተር ኪንግ ፤በበጎ ስራቸው የዓለም ኖቤል ተሸላሚና የክፍለ ዘመኑ ምርጥ ሰው የተባሉት ማዘር ቴሬዛ፤ባርነትን ለመጀመርያ ጊዜ ህገወጥ እንዲሆን ያስደረገው እንግሊዛዊው ዊሊያም ዊልበርፎርስ፤ደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ እንዲገረሰስ ታላቅ ሚና የተጫወቱት አርክቢሾፕ ዴዝሞንድ ቱቱ በሙሉ የ ቤ/ክ አገልጋዮች ናቸው። የዘመኑ ዮሴፎችና ዳንኤሎች። ዛሬስ ሰላምን፤ፍትህን፤እርቅን ለሀገር ለህዝብ እያመጣን ነው ወይስ ወንጀል ተፈጽሞበት በግፍ ደሙ የሚፈሰውን ምስኪን አልፈን ፍቅርና ህይወት ወደሌለው አገልግሎታችን እየተሯሯጥን ነው? አረጋግጥላችኋለሁ ጌታ “ከእኔ ሂዱ” ነው የሚለው። ለተደበደቡና ለሞቱት የሚቆሙ ደጋግ ሳምራውያን የት አሉ?

ሁላችንም እንደምናውቀው በሀገራችን ባለፉት ሳምንታት ከፍተኛ ተቃውሞ ተነስቶ ብዙዎች ሞተዋል፤ቆስለዋል፤ ታስረዋል፤ንብረትም ወድሟል። እንደዚህ አይነት ነገር ሲሆን የመጀመርያ አይደለም፤ከዓመት በፊትም በተመሳሳይ ብዙዎች ሞተዋል(በወቅቱ ተመሳሳይ ማሳሰቢያ በተደጋጋሚ አውጥተን ነበር ethiopiariseandshine.com)። በዚህ ከቀጠለ ጠ/ሚኒስትሩ እንዳሉት ሀገሪቱ ወደማያባራ ጥላቻና መተላለቅ ውስጥ ልትገባ ትችላለች።

ሰሞኑን የጉዳዩ አደገኝነት አሳስቧቸው የኢትዮጵያ ሃይማኖት መሪዎች ስለሰላም እንጸልያለን ብለው ጾም ጸሎት አውጅዋል፤መልካም ነው።እዚያ ጋ ግን መቆም የለበትም። አድልዎ የሌለበት የማስታረቅ፤የማግባባት፤የማቀራረብ ስራ መሰራት አለበት። ፍትህ ላጡ መምዋገት መጽሃፉ ያዛል። የኦርቶዶክስ፥ካቶሊክና ፕሮቴስታንት ህብረት የሆነው ጂኒቫ የሚገኘው የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ግድያው ቆሞ ውይይት ባስቸኳይ እንዲጀመር አሳስቧል።

የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽን ሰለሞቱት ሰዎች አስቸኳይ ምርመራ እንዲደረግ ጠይቋል።

በዚህ አጋጣሚ ከተቃዋሚዎችም ከፖሊሶችም ለሞቱት ቤተሰቦች መጽናናትንና ብርታትን እንመኛለን። ልናስተላልፍ የምንወደው 7 ነጥብ ያለው መልእክት እንደሚከተለው እናቀርባለን፤

1-ሰላማዊ ሰልፍ ስለወጡ ብቻ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ግድያ እንዳይፈጸም እንጠይቃለን።

2-ያልተመጣጠነ ሃይል በመጠቀም በሰልፈኞች ላይ ግድያ የፈጸሙ ወገኖች በአስቸኳይ በህግ ይጠየቁ፤ይሄንንም የሚያጣራ ገለልተኛና በሁሉም ወገኖች ተኣማኒነት ያለው አጣሪ አካል ምርመራውን ያድርግ፤

3-ከሰልፉ ጋር በተያያዘ ያላግባብ የታሰሩ እንዲሁም በተለያየ ምክንያት በወህኒ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና ጋዜጠኞች መንግስት ለሰላምና ለመግባባት ሲባል ይፍታ። የእስረኞች ሰብዓዊና ህገመንግስታዊ መብቶቻቸው ተጠብቀው ከቤተሰብና ከጠበቆቻቸው ጋር ያለምንም ተጽዕኖ ይገናኙ፤ፍርድ ቤት የመቅረብ መብታቸው ይጠበቅ፤

ፍርድ ቤቶች ከማንኛውም የፖለቲካ ተጽዕኖ ነፃ ሆነው ፍትህን ይስጡ።

4-ህዝቡ ያቀረበው የፍትህ ጥያቄ በአስቸኳይ ተገቢው ትኩረት ይሰጠው፤ጥያቄዎቹም ይመለሱ።

5-በተለያዩ ወገኖች ያለውን ቁጣ የምንረዳ ቢሆንም ከጥላቻ ንግግሮችና ከዘር ተኮር ስድቦች ከጥቃትና ከሀይል ተግባሮች ሁሉም አካል እንዲቆጠብ እናሳስባለን።እንዲህ አይነት ነገር ሀገር የሚገነባ ሳይሆን የሚያፈርስ ነው። ስሜታችንን ተቆጣጥረን የወደፊት ሀገርን አንድነትና ህልውና ማስጠበቅ መቻል አለብን። እድሉ ያለን ዛሬ ነው። አንዴ ጥላቻው ከቁጥጥር ውጭ ከሆነ መመለሻ አይኖረውም።

6-ይህ ችግር እንዳይደገምና ሀገሪቷ ወደ ለየለት ሁከት እንዳትገባ በሀገር ውስጥም በውጭም ያሉ የሀገሬ ጉዳይ ያገባኛል የሚሉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በተወካዮቻቸው የሚሳተፉበት የውይይት መድረክ መንግስት ያዘጋጅ፤ይህን ውይይት የሚያመቻች ሁሉም ወገን የሚቀበለው ከሀገር ውስጥና አስፈላጊም ከሆነ ከዓለም አቀፉ ህብረተሰብ የተውጣጣ አካል ባስቸኳይ ይቋቋም። የወደፊቱም የሀገሪቱ አቅጣጫ መግባባትና በልዩነት አንድነት በሚፈጠርበት ሁኔታ ላይ ተመሳሳይ ብሄራዊ መረዳት ላይ ይደረስ።ለዚህም ያለ ማንም የፖለቲካ ተጽእኖ በተለይ የሃይማኖት መሪዎች፤የሀገር ሽማግሌዎች፤የሲቪክ ድርጅቶችና አስፈላጊ ከሆነ ዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ድጋፉን ያድርግ።

7-ከዚያ በመቀጠል የሚደረገው ሀገራዊ ምርጫ ሁሉን ያሳተፈና በተቃዋሚውም በዓለም አቀፍ ደረጃም ተኣማኒነት ያለው ይሁን።

ኢትዮጵያችን ሰላምም ፍትህም ያስፈልጋታል

ሁላችንም የድርሻችንን ዛሬውኑ መወጣት እንጀምር

“በሰዎች መካከል ዕርቅና ሰላምን የሚያደርጉ የእግዚአብሔር ልጆች ስለሚባሉ ደስ ይበላቸው”

ዳንኤል ጣሰው

ከኢትዮጵያ ተነሺ አብሪ

ethiopiariseandshine.com

18 Comments on “ኢትዮጵያ አሁን የሚያስፈልጋት ሰላም ነው ወይስ ፍትህ ? – ፓስተር ዳንኤል ጣሰው”

  1. ፓስተር ዳንኤል ጣሰው

    let us know you first>
    Are you the one from “Prison Fellowship” before we start commenting.

    Thanks

  2. No this one is not from the Prison Felloship. by the way Ethiopia needs both justice and peace as justice is the cause for peace.

  3. ምን ያለህ ድንዝ ያልክ ደነዝ ነህ እባክህ? በየትኛውም አገር ላይ ፍትህ ካል ሰላም አለ ፍትህ ከሌለ ግን ሰላም አይኖርም የኔ ግትቻ።

  4. 25 አመት የት ተኝተህ ነው ዛሬ ፍትህ ምናምን የምትለው ከውልደቱ ጀምሮ ወያኔ ጥላቻን ሲዘራ የኖረ ድርጅት መሆኑ ጠፍቶህ ነው? ማስመሰል በፍፁም ደስ አይልም ወንድሜ እኔም ፕሮቴስታንት ነኝ ሽንገላን አጥብቄ እጠየፋለሁ አሁን ከአንተ የሚጠበቀው ማስታረቅ ሳይሆን ንስሀ ገብተህ ከአምላክህ ጋር መታረቅ ነው በእውነት ነው የምልህ አብዛኛዎቻችሁ የእምነት አባቶች ቀላችሇል ከጥቂቶች በስተቀር ስለዚህ በህዝብ ቁስል ላይ ጨው አትነስንስ፡፡

  5. ተናግረህ ባታናግረን ጥሩ ነው፡፡
    ስለዘገያችሁ ብዙም የምትቀይሩት ነገር አይኖርም፡፡
    እርግጥ ነው ህውሃት የሚባለውን ዘረኛ ድርጅት የፈጠርነው እኛው ነን፡፡ለአላማችንም በጥሩ ሁኔታ እየተጠቀምንበት ነው፡፡ለትግራይ ልሂቃን በአጠቃላዩ ተንኮልን ያሰተማርናቸውና ያሰለጠናቸው እኛው ነን፡፡ታሪካዊ ቅድስት ኢትዮጵያን በቁጥጥራችን ስር የማድረግ የረጅም ጊዜ ህልም ነበረን፡፡የእያንዳነዱን ኢትዮጵያዊ የህብረተሰብ ክፍል ስስ ብልትና አመለካከት በቂ ጊዜ ወስደን በቅጡ አጥንተን ነው የተንቀሳቀስነው፡፡በዘር በሃይማኖት በፆታ በእድሜ በሁሉም ዘርፍ ቀዳዳዎችን አጥንተናል፡፡ህልማችንን ለማሰካት ሀ-ብለን የጀመርነው ግን ንጉሳዊ አገዛዙን በመጣል ነበር፡፡ለምን ቢባል ንጉሳዊ አገዛዙ የእውነተኛይቱ ፅዬን ሀቀኛ የበላይ ጠባቂ ነበር፡፡ንጉሳዊ አገዛዙ እውነተኛ የፅዮን ልጅ እና ቀናኢ የኢትዮጵያ ሙሽራ ባልተቤት ነበር፡፡አሁን ግን ሙሽሪት ኢትዮጵያ በውሽሞች በደላሎች የቀን ጅቦች እና ተኩላዎች እንድትተዳደር ነው ያደረግነው፡፡ንጉሱን ስንገረስስ ቀጥሎ ቤተክርስቲያኒቱንም ቀስ በቀስ ለመገዝገዝ እንደምንችል እናውቅ ነበር፡፡ምክንያቱም ንጉሳዊ አገዛዙና ቤተ-ክርስቲያን እጅና ጓንት ነበሩ፡፡ሁለቱ እጅና ጓንት ሆነው ኢትዮጵያን ጠንክረው ከውጪ ጠላት ለመከላከልና ማንነቷን ለማስጠበቅ ችለዋል፡፡ንጉሱን ለመጣል ጥራዝ-ነጠቅ ምህሩን ተጠቅመንበታል፡፡ምክንያቱም ምሁሩ ሳያገናዝብ ዝም ብሎ በመጤ አዲኦሎጂ በጭፍን የሚነዳ ከብት ነበር፡፡ሶሻሊዝም ስንለው ሶሻሊዝም ኮሙኒዝም ስንለው ኮሙኒዝም ይላል፡፡ቀጥሎ ደግሞ ካፒታሊዝም ስንለው ካፒታሊዝም ዲሞክራሲ ስንለው ዲሞክራሲ ሊበራሊዝም ስንለው ሊበራሊዝም ብሎ ይጮሃል፡፡የነገርነውን ነገር በደንብ ሳይመረምር እንደ ገደል ማሚቶ መልሶ ያስተጋባልናል፡፡የሀገሩንና የአለም ታሪክ ማገናዘብ የሚባል ነገር የለም፡፡የሰውንም ውስብስብ ባህሪ ገና በቅጡ አልተረዳም፡፡ይህንን ግልብ ምሁር እና ደርግን ተጠቅመን ንጉሳዊ አገዛዙን ስንገረስስ በዙሪያው ያለውንም የልሂቃን ስብስብ ጨምረን ነው አብረን ያዳከምነው የገረሰስነውና ያጠፋነው፡፡ንጉሳዊ አገዛዙን ብቻም ሳይሆን በዙሪያው ያለውን እርዝራዥ ልሂቃንና ወጣት ምሁሩንም ጭምር በቀይ-ሽብር ነጭ-ሽብር ለማጥፋት ደርግ የተባለውን ሃይል እስከመጨረሻው ውድቀቱ ድረስ በዘዴ ተጠቅመንበታል፡፡እንደዚህ እያደረግን የአላማችን ታማኝ አገልጋይ የሆኑትን የትግራይ ልሂቃኖችን ለስልጣን እስከምናበቃ ድረስ እውነተኛዎቹን የፅዮን ልጆችና ቀናኢ የኢትዮጵያን ባሎች ሁሉ ቀበቶ አስፈትተን ሱሪያቸውን በዘዴም በሃይልም ስናስወልቅ ቀጥሎ ኢትዮጵያንም የክብር ቀሚሷን እንደምናስወልቃት ሳይታለም የተፈታ ነበር፡፡ሀገር በሴት ትመሰላለች አይደል የሚባለው፡፡ታሪካዊት ድንግል ቅድስት ኢትዮጵያም የክብር ቀሚሷን አውልቃ በዘመኑ አባባል ሬፕ መደረግ ጀመረች፡፡በውሽሞች በደላሎች የቀን ጅቦች እና ተኩላዎች የምትተዳደረው ኢትዮጵያ የክብር ቀሚሷን አውልቃ እንደ ሴተኛ አዳሪ ክብሯን ሸጣ በምታገኘው የውጪ ዶላር ዩሮና ፓውንድ አርተፊሻል የኢኮኖሚ እድገት እንድታስመዘግብ እያደረግን ነው፡፡የሚገርመው ደግሞ 15 ሚሊዮን ልጆቼ ተራቡብኝ እርዱኝ እያለችን ነው፡፡እኛ ግን ተይ አትቀልጂ እስኪ ቀናብለሽ ተመልከቺ ፎቁን መንገዱን አድገሻል ተመንደገሻል እያልናት ነው፡፡የኢኮኖሚ ሴክተሩንም ሆነ ተመዘገበ የሚባለውን አሳሳችና አርተፊሻል የኢኮኖሚ እድገቱን ለራሳችን አላማ በሚጠቅመን አቅጣጫ አስበንበት ነው ያዋቀርነው፡፡ስለዚህ 15 ሚሊዮን ህዝብ ቢራብ እና የቀረውም በገፍ ቢሰደድ ብዙም የሚገርም አይደለም፡፡ከላይ እንደተገለፀው የእያንዳንዱን የህብረተሰብ ክፍል ስስ ብልትና አመለካከት በደንብ አድርገን ውስጣ ውስጡን መርምረን አጥንተናል፡፡ምሁሩ ምን ይፈልጋል? ፖለቲከኛው ምን ይፈልጋል? ወጣቱ ምን ይፈልጋል?ሴቱ ምን ይፈልጋል?ወንዱ ምን ይፈልጋል?እስላሙ ክርስቲያኑ ምን ይፈልጋል ? ትግሬው አማራው ኦሮሞው ወዘተ ምን ይፈልጋል? ገጠሬው ከተሜው ምን ይፈልጋል? የሁሉንም እንደበአቱ ለማጥናት ሞክረናል፡፡ማስመሰልና ምስጢራዊነት የጥንካሬያችን ዋና ምንጭ ናቸው፡፡እራሱን እውነትን ሳይሆን እውነት የሚመስልን ነገር ማቅረብ እንዳለብን እንረዳ ነበር፡፡እውነትንማ ማንም ተስማምቶት እንደማይወደው እናውቃለን፡፡ምሁሩና ፖለቲከኛው ነፃ-ፕሬስ ዲሞክራሲና ሌሎችንም አይዲኦሎጂ የሚባሉትን ቲዎሬቲካል ነገሮች በጭፍን ማራገብ እንደሚወድ ተረድተናል፡፡ብዙም ተግበራዊነት የሌላቸውን ቲዎሬቲካል ነገሮች በማቅረብ ደረጃ በማስመሰል ክህሎታችን ተጠቅመን ማህበረሰቡን ማደናገር ችለናል፡፡የኢትዮጵያ ምሁርና ፖለቲከኛ ቀስ በቀስ እግዚአብሄር የሚለውን ጉዳይ ከልቦናውና ከአእምሮው እንዲፍቅና በአለማዊ እውቀቱ ብቻ እንዲመፃደቅ ማድረግ ችለናል፡፡ዳርዊንዝምን ሴኩላር-ሁማኒዝምን ኮሙኒዝምን ካፒታሊዝምን ሊበራሊዝምን ወዘተ ተመሳሳይ አስተሳሰቦችን በምሁሩና በፖለቲከኛው አስተሳሰብ ውስጥ አስርፀናል፡፡ሁሉም አይዲኦሎጂ እጃችን ያለበት የእኛው የፈጠራ ውጤት፡፡ነገር ግን የሁሉም ቲዎሬቲካል አይዲኦሎጂ ድብቅ አላማ መጨረሻ ላይ የሰውን ልጅ ከፈጣሪ አምልኮት ማስካድና የእኛ ተከታይ ማድረግ ነው፡፡በእርግጥ ሁሉንም የምናቀርባቸው በማር የተለወሱ መርዞች አድርገን ነው፡፡ለምሳሌ ሴኩላር-ሂዩማኒዝም ስንል ሰሙና ወርቁ የተለያየ ነው፡፡ውጪያዊ ሰሙ ለሰው ልጅ ከፍተኛ ሰብዓዊነትን ማላበስ ወይንም ለሰው ልጅ ሰብዓዊ ፍቅርና አክብሮት ማሳየት የሚል ሊመስል ይችላል፡፡ውስጣዊ ቅኔው ግን ሌላ ነው፡፡ ማለትም ሰው በራሱ ለራሱ አምላክ ነው ስለዚህም ሰው የአምላኩን መመርያ ሳይከተል የራሱን ውስጣዊ ፍላጎቱንና አመለካከቱን ብቻ በመከተል እውነተኛ ማንነቱን እና የመጨረሻውን የስውነት ደረጃውን እራሱ በራሱ ማግኘት ይችላል የሚል ነው፡፡በአጭሩ እግዚአብሄር የለም ማለት እራስህን አምልክ እራስህን ተከተል ማለት ነው፡፡እንደዚህ እያደረግን ብዙውን ምሁር አሳስተናል፡፡ወደ ወጣቱ ትውልድ ስንመጣ የአውሮፓ ኳስ ፊልም ጫትና አደንዛዥ እፅ ሌላውንም ብልጭልጭ ቁሳቁስ በገፍ አቅርበንለታል፡፡ለሴቶቹ ፋሽን ኮስሞቲክ እና በአጠቃላይ ብልጭልጭ የሆነውን ማቴሪያል ነገር ሁሉ በገፍ አቅርበንላቸዋል፡፡ይህ ብቻውን ስለማይበቃ ሴቶቹ በራሳቸው የቅዠት አለም ውስጥ እየተቅበዘበዙ እንዲኖሩ ማድረግ አለብን፡፡ለዚህም እንዲረዳን ስሜታዊና የተፈጥሮ ደካማ ጎናቸውን በመጠቀም የሴቶች ነፃነት የፆታ እኩልነት የሴቶች ጥቃት የሚለውን በመርዝ የተለወሰ ማር አቅርበንላቸዋል፡፡ሴቶች በተፈጥሯቸው አቅጣጫ መሪ ጠባቂና ሃይ ባይ ከሌላቸው በቀላሉ እንደሚበላሹ ጥንቱንም እናውቃለን፡፡ለዚህ እንዲረዳንም ፌሚንዝምን በማስፋፋት በወንዶችና በሴቶች መካከል ጥላቻንና ጥርጣሬን በማራገብ በመካከላቸው የፆታ ጦርነት ከፍተናል፡፡በመካከላቸው ድልድይ ሳይሆን ግንብ ገንበተናል፡፡ሴቱን ወንድ ወንዱን ሴት አድርገነዋል፡፡በፊልሙ በሚዲያው በመዝናኛው በአካዳሚው ወዘተ አማካኝነት ልቅ ወሲብን ሽርሙጥናን ግብረ-ሰዶምንና አስፋፍተናል፡፡እውነቱን ሃሰት ሀሰቱን እውነት ጥሩውን መጥፎ መጥፎውንም ጥሩ አስመስለን አቅርበነዋል፡፡በዚህም የማህበረሰቡን የቆየ ወግ ባህል ሞራል ሃይማኖት ታሪክ ፈሪሃ-እግዚአብሄር በርዘን እያፈራረስነው ነው፡፡ወሲብ ገንዘብና ስልጣን የሰው ልጅ ደካማ ስስ ብልቶች እንደሆኑ እናውቃለን፡፡የማህበረሰብ ዋና መሰረት የሆነውን በጋብቻ ጥምረት የሚፈጠረውን ቤተሰብ የሚባለውን የተከበረ የሰው ልጅ የቆየ ተፈጥሯዊና ማህበራዊ ተቋም ቀስ በቀስ ዋጋ እንዲያጣና እንዲፈራርስ እያደረግን ነው፡፡ስለዚህም ማህበረሰቡ በማንኛውም አቅጣጫ አንድ ሆኖ ተረጋግቶና ጠንክሮ አቅም አግኝቶ ሊታገለን አይችልም ማለት ነው፡፡በህብረተሰቡ ውስጥ የተለያዩ ጊዚያዊ አጀንዳዎችን በመፍጠር ከራሱ ውስጣዊ ማንነት እና ከአምላኩ ጋር የሚገናኝበት ማህበረሰባዊ ፋታ አሳጥተነዋል፡፡ለማህበረሰቡ ዲሞክራሲን እራሱን በራሱ ማጥፊያ እንዲሆን አድርገን አቅርበንለታል፡፡ቅድሚያ እራሱን በደንብ የማያውቅ ማህበረሰብ እንዴት ብሎ እራሱን በራሱ እንደ ሀገር ሊያስተዳድር ይቻለዋል?መንግስተ-ሰማያት እንኳን በተጋድሎ በእምነት ፅናትና በምግባር እንጂ በዲሞክራሲ ይገባል እንዴ?ዲሞክራሲና ነፃነት እንደ ተግባርህ የሃላፊነት ደረጃና መጠንህ በአቅምህ ተመጥኖልህ የምታገኘው የመብት ትሩፋት ነው፡፡እኛ የምናምነው እንደዚያ ነው፡፡ዋና ተቀናቃኞቻችንም የሚያምኑት እንደዚያ ይመስለናል፡፡ስለዚህ ዲሞክራሲ የሚባለው ቅዠት ለሁሉም ሰው ያን ያህል እንደማይሰራ ጥቂቶች ልሂቃን ብቻ ያውቁታል፡፡ዲሞክራሲ የሚባለውን ነገር ንጉሳዊ አገዛዞችና ቤተ-ክርስቲያን አንድ ሆነው የመሰረቱትን የቆየ ጠንካራ ስርአት ለመገርሰስ እንደ ዋና መሳሪያ ተጠቅመንበታል፡፡
    ምክንያቱም ህዝቡን እርስ በርሱ አስማምተው ከራሱም ከአምላክም ጋር አንድ እንዲሆን በማድረግ ለብዙ ዘመናት ዋና አስቸጋሪዎቹ ተቀናቃኞቻችን የሆኑት እነሱ ነበሩ፡፡ለማንኛውም ዲሞክራሲ የሚለውን የላም አለኝ በሰማይ ቅዠት ወይንም ኢሉዥናል ፋንታሲ በማህበረሰቡ ውስጥ ፈጥረናል፡፡የእኛ አጀንቱር ምሁራኖችና ፖለቲከኞቻችንንም ለዚህ የቅዠት ድራማ ተግባራዊነት እንዲረዱን ተባባሪ አድርገናቸዋል፡፡ህዝቡን ሳይሆን እኛን ነው የሚያገለግሉት፡፡ምክንያቱም እኛ ነን ጠቀም ያለ ገንዘብ ፈንድ የምናደርጋቸውና በምርጫ ሽፋን ለስልጣን የምናበቃቸው፡፡ በዩዘሪ እና እስፔኩሌሽን ላይ በዋናነት የተመሰረተው ዘመናዊው አለም-አቀፋዊው ፋይናንስ ካፒታሊዝም አለምን በማንኛውም አቅጣጫ በመዳፋችን ቁጥጥር ስር ለማድረግ የተጠቀምንበት የራሳችን ንብረት የፈጠራ ውጤት ነው፡፡ህውሃቶች ዶላር ከሰጠናቸውና ስልጣናቸውን ከጠበቅንላቸው ሀገሪቱን ከነህዝቦቿ አሳልፈው እንደሚሸጡሉን እንተማመናለን፡፡በእርግጥ ኢትዮጵያ ውስጥ ዜጋው በገዛ ሀገሩ የህውሃቶች የመሬት ጭሰኛ ተደርጓል፡፡በገዛ ሀገሩ ሀገሩን ተቀምቶ ከሁለተኛ ዜጋ በታች እንዲወርድ ተደርጓል፡፡ህውሃቶች መሬትና በገፍ የሚያትሙት ብራቸው ከእኛ ሁለ-ገብ ድጋፍ ጋር ተጨምሮ ሌላውን ዘር በተለይም አማራውን እያሰቃዩና እየገፈተሩ ሀገሪቱን በማንኛውም አቅጣጫ ለመቆጣጠር አስችሏቸዋል፡፡ይህ አካሄድ መጨረሻው ጥሩ እንደማይሆን እናውቃለን፡፡ነገር ግን አላማችንን እስካሳካልን ድረስ ማን ወደቀ ማን ተነሳ ግዳችን አይደለም፡፡ጦር ማዝመት ሳያስፈልገን ገንዘብና ቁሳቁስ ብቻ በማቅረብና ባህሉን ሃይማኖቱን ታሪኩን በመበረዝና በዘር በሃይማኖት በፆታ እርስ በርስ በማናከስ ብቻ ኢትዮጵያን በቁጥጥራችን ስር አድርገን ቀስ በቀስ ለማፈራረስ እድሉን አግኝተናል፡፡አላማችንን ለማሳካት ስንል ለአገልጋዮቻችን በገፍ የምናቀርበው ገንዘብና ቁሳቁስ ጠቀሜታው ወደ መታሰሪያው በረት ወይንም ወደመታረጃው የሚያመራው በሬ አሞሌ ጨው እየላሰ እንደሚሄደው ከብት ማለት ነው፡፡በተረፈ ኤትኒክ ፖለቲክስ ስለምትሉት ጉዳይ ከአላማችን ውጪ የትኛውም በሄር የሚባለው ነገር ለእኛ የተለየ ወዳጃችንም ሆነ ጠላታችን አይደለም፡፡
    ለትግሬው ያለን ጊዚያዊ ወዳጅነትም ሆነ አማራ ከሚባለው ጋር ያለን ጊዚያዊ ቅራኔ ከአላማችን እና አላማችን ጋር ብቻ የተያያዘ ነው፡፡አላማችንን እስከደገፈ ድረስ ሁሉም ጊዚያዊ ወዳጃችን ነው አላማችንንም እስከተቃወመ ድረስ ሁሉም ጊዚያዊ ባላንጣታችን ነው፡፡ለእኛ ሁሉም የአዳም ዘር አንድ አይነት ነው፡፡እኛ እንደዚያ ነው የምንመለከተው፡፡የእናንተን አመለካከት ግን አናውቅም፡፡
    እርግጥ ነው የእያንዳንዱን በሄር ወይንም ሃይማኖት ስስ ብልትና አመለካከት ለራሳችን አላማ እንደመዳረሻ በጊዚያዊ መሳርያነት በብልሃት እየተጠቀምንበት ነው፡፡ሁሉንም ነጣጥለን ተራ በተራ እየለየን ለማዳከምና ለመምታት እንዲመቸን እያንዳንዱ በየራሱ የነፃነትና የዲሞክራሲ የቅዠት አለም ኢሉዥን ውስጥ እንዲኖር እድል ፈጥረንለታል፡፡በአጭሩ ብሄር በሄረሰብን ለከፋፍለህ ግዛው ስልታችን በዘዴ እየተጠቀምንበት ነው፡፡የህውሃት ተቃዋሚ ናቸው የሚባሉቱ ብዙዎቹ ተቃዋሚ ተብዬዎችም የኢትዮጵያ ምሁራኖችና ፖለቲከኞች በፀጉር ስንጠቃ ንትርክ ጥቃቅን ልዩነቶቻቸውን እያራገቡ ለሀገራቸውም ለህዝባቸውም ትርጉም ያለው ስራ እንዳይሰሩ ዲሞክራሲ ብሄር ብሄረሰብ እያልን በአፍራሽ ተግባር ውስጥ ተብትበን ይዘናቸዋል፡፡ለምንድነው ተስማምታችሁ አንድ ትርጉም ያለው ነገር ለሀገራችሁና ለህዝባችሁ የማትሰሩት ሲባሉ የሚመልሱት መልስ አለመስማማትም ዲሞክራሲያዊ መብታችን ነው የሚል የምሁራዊ የድንቁርና መልስ እንዲሰጡ እያደርግናቸው ነው፡፡ምናልባትም መለሳችን ኢዲዬት ብሎ የሰደባቸው ለዚህ ሳይሆን አይቀርም ይባላል፡፡
    ብዙዎቹ እርስ በርስ መጠላለፍን እንደ አዋቂነት የሚቆጥሩ ብልጣብልጥ አድርባይ ከሃዲዎችና ሆዳሞች ናቸው፡፡ስልጣንን የሚያዩት የራሳቸው ሊያደርጓት እንደሚጎመጁባት ቆንጆ ልጃገረድ ሴት አድርገው ነው፡፡የስልጣን ክብሩንና ጥቅሙን እንጂ ይዞት የሚመጣውን ሃላፊነትና መዘዝ ፈፅሞ አይረዱትም፡፡በዚህ ባህሪያቸው ለእኛ ጥሩ ታማኝ አገልጋይ መሳሪያዎች ሆነው እያገለገሉን ነው፡፡ብዙዎቹን ተቃዋሚ ተብዬዎችን ህዝቡን እንዲያደናግሩልን ህውሃቶቻችን ደግሞ እኛ በምንፈልገው መንገድ ህዝቡን እንዲገዙልን ያስቀመጥናቸው አገልጋዮቻችን ናቸው፡፡ሁለቱም በየፊናቸው የእኛኑ ስራ ነው የሚሰሩልን፡፡ከዚህ አንፃር የትግሬ ልሂቃን ባንዳዎች በብዛት ግንባር ቀደም መሪ አገልጋዮቻችን ናቸው፡፡ነገር ግን ከሁሉም ብሄር ብሄረሰብ ከአማራውም ከኦሮሞውም ከጉራጌውም ከሌላውም ተመሳሳይ አገልጋይ ልሂቃን ባንዳዎችን በየደረጃውና በየአይነቱ ለምንፈልገው ተግባር በየአቅጣጫው አሰልፈናል፡፡ነገር ግን ለእኛ አስቸጋሪ ፈተና የሆኑቱ ብሩህ አእምሮ የታደሉቱ ብልሆቹና ቀናኢዎቹ ኢትዮጵያውያኖች ጥቂቶች ናቸው፡፡እነዚህን አብዛኛዎቹን ቀናኢ ኢትዮጵያውያን ለእኛ አደገኛ ስለሆኑ ቀስ በቀስ በሂደት በዘዴ ግማሾቹን አዳክመናቸዋል ግማሾቹን አስወግደናቸዋል፡፡ለወደፊቱ ግባችን ዋና ፈተና ሆና የተጋረጠችብን ቤተ-ክርስቲያኑቱና እርሷን የመጨረሻ የህልውናቸው መሸሸጊያ ያደረጉና በእምነታቸው የፀኑ ምእመናን ብቻ ነው፡፡ለዚህ ፈተና ዋና ጋሻችን ገንዘባችን ነው ብለን እናስባለን፡፡ቤቴን የንግድ ቤት አደረጋችሁት ብሎ በጅራፍ ገርፎ የሚያባርረን ያለ አይመስለንም፡፡በገንዘብ የማንገዛው ነገር የለምና፡፡ቤተ-ክርስቲያኒቱን ልማት በሚል አሳሳች ፈሊጥ ከሃይማኖትና መንፈሳዊ ተቋምነት ወደ አለማዊ የኢኮኖሚ ተቋምነት ለመቀየር ቀስ በቀስ ጥረት እናደርጋለን፡፡በገንዘብ የገዛናቸውን የራሳችንን ሰዎች ወይንም አጀንቱር እንደተለመደው በሁሉም መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት ውስጥ በሰፊው በኢንፍልትሬሽን አስርገን አስገብተናል፡፡ሁልጊዜም እንደምናደርገው በገንዘባችን ብዙ አርተፊሻል ድርጅቶችንና ሃይማኖቶችን እንደአሸን እንዲፈሉ ማድረግ እንችላለን፡፡እውነተኛውን ጥሩውንና ንፁሁን ነገር ሁሉ የምናበላሸው የምናዳክመውና የምናጠፋው በቀጥታ ፊት ለፊት በመጋፈጥና በመቃወም አይደለም፡፡ከፊት ከኋላ ከግራ ከቀኝ ከላይ ከታች በሁሉም አቅጣጫ የውሸት ነገሮችን አመሳስለን በማቅረብና በሂደት ቀስ በቀስ በማሳሳትና አቅጣጫ በማሳት ነው፡፡እናንተ ፐርቨርዥን የምትሉትን ተግባራዊ በማድረግ ማለት ነው፡፡ሌላው ያው እንደሚታወቀው ማስመሰለንም በእጅጉ የተካንበት ነው፡፡ከውጪ ያማረ የተፃፈ የታይታ ህጋችንን ለህዝባዊ መልካም ግንኙነታችን ማሳመሪያነት አልፎ አልፎ ስንጠቀምበት በአብዛኛው በተግባር የምንፈፅመው ግን ያልተፃፈውን የውስጥ ህጋችንን ነው፡፡ላለፉት 25 ዓመታት በኢትዮጵያ ላይ የሰራነው ስራ ይኸው ነው፡፡ኢትዮጵያ እንደ አቡነ-ጴጥሮስ አይነት ቀናኢ የሃይማኖትና የሀገር ሰማእት እንደሌላት ተረድተናል፡፡ሁሉም በጥቅምና በስልጣን ሀገሩን እንደሚሸጥ አውቀናል፡፡የሚላስ የሚቀመስ ያጣ ብዙ ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ እንዳለ ሁሉ ወገኑን እየዘረፈ በሙስና ሀብት አከማችቶ የስጋ ምቾቱ ቁንጣን እረፍት የነሳውን የህብረተሰብ ክፍልም ለእኛ እንደሚታረድ ከብት ወደፈለግነው አቅጣጫ እየመራን ለራሳችን መጠቀሚያ ለማድረግ ብዙም አይከብደንም፡፡ስለዚህም በጥቅምና በስልጣን ብቻም ሳይሆን አንዳንዴም በወሲብ ቅሌት ጭምር የፈለግነውን ማንበርከክና የአላማችን አስፈፃሚ አገልጋይ ማድረግ እንችላለን፡፡በኢትዮጵያችሁ ውስጥ ድህነትንም ሀብትንም ጎን ለጎን በተቃራኒ አቅጥጫ ግራና ቀኝ ስናስፋፋ ሁለቱንም ለራሳችን መጠቀሚያ ለማድረግ እንዲመቸን አድርገን አስበን ነው፡፡ድሃውም በድህነቱ ሃብታሙም ለምቾቱ የእኛው ጥገኛ እንዲሆን በማድረግ ሁለቱንም ከአምላካቸው እንዲራራቁ ማድረግ ዋና አላማችን ነው፡፡ሃብታሙ ለምቾቱ ድሃውም ለህልውናው ሰርቫይቫል ቀጣይነት ሲል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የእኛው የእኛው ጥገኞች ሆነዋል፡፡በዚህም እያንዳንዱ የህብረተሰብ ክፍል እርካታና እርጋታ የተለየው ተቅበዝባዥ እንዲሆን ማድረግ ችለናል፡፡የሰውነት ባህሪውን እየረሳ ወደ እንስሳዊ የአውሬነት ባህሪ እንዲቀየር እያደርግነው ነው፡፡
    አንገቱ ላይ ባስገባንለት ልጓም ወደፈለግነው አቅጣጫ ልንጋልበውና ልንመራው በእጃችን ስር ነው፡፡
    እንደ ባህሪውና አመለካከቱ የእስር ገመዳችንን ያሳጠርንበትም ሆነ ያስረዘምንለት የህብረተሰብ ክፍል ዞሮ ዞሮ በእኛው በረት ውስጥ ነው ያለው፡፡አንድ ነገር ብቻ ነው ከእኛ መዳፍ ወይንም የባርነት ቀንበር ስር ሊያወጣችሁ የሚችለው፡፡እውቀታችሁ?ሃሃ ሄሄ ይህማ ከእኛ አዋቂና ጠቢብ የሆነ ላሳር ነው፡፡ያውም ግልብ የሆነው ጥራዝ-ነጠቅ እውቀታችሁና ጥበባችሁ ሊያድናችሁ? ሃሃ ሄሄ ይህማ አያድናችሁም፡፡ፈፅሞ ፈፅሞ፡፡የአለማዊ አስተሳሰብ ፍቅራችሁና አንድነታችሁ? ሃሃ ሄሄ ይህም እውቀትና ጥበብ የሌለው የቁጥር ብዛት አንድነት መንጋ መሆን ብቻውን ምንም ዋጋ የለውም፡፡
    በአምላካችሁ ላይ ባላችሁ የፀናና የጠራ ፍቅራችሁና እምነታችሁ የፀጋ ልጅነታችሁን ማስጠበቅ ስትችሉ ብቻ ነው ከእኛ ባርነት ነፃ መውጣት የምትችሉት፡፡ይህንን ፈተናችንን ተቋቁሞ ከእኛ የባርነት ቀንበር ነፃ ለመውጣት የሚችል ካለ ይህንን ካላይ ያለውን እውነት አሳውቀን ከእስራታችን ለመፈታት የሚችል ካለ እድሉን እንሰጣለን፡፡እኛም እንደ አምላካችሁና እንደ አምላካችን በነፃ-ፍቃድ ላይ የተመሰረተ የመወሰን እድል መርህን በማክበር እናምናለን፡፡እሳቱም ይኸው ውሃውም ይኸው እጅህን የፈለክበት ስደድ እንደሚባለው ማለት ነው፡፡ከዚያ ውጪ እየነካካችሁ አታናግሩን፡፡እናንተም ወደ ስራችሁ እኛም ወደ ስራችን፡

  6. Good points. It is important to take in to consideration this message. I appreciate every body who is making effort to create a peaceful and democratic way of solving this crisis. Killing innocent civilians in whatever situation must be stopped and all who are jailed due to their opinion must be released without any precondition. This is first stop to solve the crisis our country is facing.

  7. ውያኔ ግደሉ ብሎ ያዘዛቸውን በመካድ አሳልፎ ለፍርድ ማቅረብ ከዘህ በላይ የሚቀለው የለም አሳልፎ የሚስጣቸውም ገደዩቹን ሳይሆን አንገልም ያሉ ጠላቶቸን ማስውገጃ ያደርገዋል በራሱ ፖሊስ በራሱ ዳኛ
    ውያኔ የዚህ አይነት ቅሌት ዋና ባለቤት ነውና

  8. Thank you Pastor Daniel
    I have respect for you,

    this is not his first time, he all ways show solidarity, to his people he gave an interview on ESAT, he was beside our people in DC on demonstration for those whom suffer in middle east.

    by the way im Born again Christian like him,& not happy with our church leaders. because of that I don’t go to Ethiopian church I attend some where else.

    Ethiopian churches preach to stay away from politics or not mix religion with politics.but where I go we are all ways told to participate in politics, to support or to oppose Government, to give voice, to involve in election….and so on..

    sadly our church leaders fell to speak the truth,
    one time I heard respected Pastor Tollosa Gudina preaching in Addis Ababa stadium, how late Meles is the only leader who left the palace in peace, blessing Azeb Mesfin, the other time he ask his church to pray for the country, because the young generation is throwing,
    stone, okay the young people have stone is facing Agazi snaiper who is killing, pregnant women, from 7yrs to 80, 90…yrs old,
    judge me comparing, stone with life bullet…

    let me ask you Dr. Pastor Tollosa I don’t know better than you, is it what our Bible teach? I want learn from you, the bible I read says our past prophets gave their life for the truth, they stood by peoples side, Saul killed many prophets who stood with David and did the thing there are many examples from mosses to John …

    God bless our people.

  9. I agree with some of the recommendations of the Pastor. However everyone of us should understand and underline that peace without freedom is meaningless as well as useless. The saying “give me freedom or give me death” is both timely and relevant. People who fight and recommend peace should be also be the first to fight for freedom. The TPLF/Woyane leaders and members have been arrogantly deaf to the cry of Ethiopians for justice, democracy, and equally for all from north to south and from east to west. Twenty five is a very long time for anyone to repent and apologize for the wrongs perpetuated on 95 percent of Ethiopians by the minority group. As it is, currently the time is not for peace but to the fight for democracy, rule of law, equality, and respect for Ethiopians. At this point Ethiopians are not interested for one sided peace when they are murdered, tortured, kidnapped, and ethnic cleansing, genocide, racism and treasons perpetuated by TPLF/Woyane criminals. No peace until Ethiopians are liberated and the criminals get what they rightly deserve.

  10. Tenefa hodame kase anten belo sebake how match money weyane give it to you. for this propaganda arfehe tekemete yant kene eskemeta mote lante ena lante aynetu mote leweyane God bless Ethiopia

  11. ወሬኛ ነህ!ትግሉ ባንተ ብጤዎች የፅሁፍ መጠይቅ ወይም መግለጫ ባለፈ ሄዷል።አሁን በመላው ኢትዮጵያ ትግሉን ማቀጣጠል የሚጠይቅበት ግዜ ነው።አንተ ዝም ብለህ ጌታ ተናገረኝ። ምናምን እያልክ መድረክ ላይ ጩህ።አሁን የሚያስፈልገው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በቀጥታ በሚችለው መንገድ ትግሉን መቀላቀል ነው!አለቀ!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*