“በግድ ወደ ሕገ አራዊት መግባት አለብን ? ” ከትናንት ወዲያ፣ ትናንትና ዛሬ - ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም
“በግድ ወደሕገ አራዊት መግባት አለብን ? ”
ከትናንት ወዲያ፣ ትናንትና ዛሬ – ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም
ዛሬ ላይ ቆሜ ወደኋላ ሳይ የትናንት ወዲያው ይናፍቀኛል፤ ትናንት ወዲያን አይቼዋለሁ፤ አውቀዋለሁ፤ ትናንትንም አይቼዋለሁ፤አውቀዋለሁ፤ ዛሬንም እያየሁትና እያወቅሁት ነው፤ ከትናንት ወዲያ በጃንሆይ ዘመን የአገዛዙ ነቃፊ ነበርሁ፤ የወደፊቱን የማየት ችሎታ ስለሌለኝ የጃንሆይን አገዛዝ ነቃፊ ነበርሁ፤ በትናንት ወዲያ ላይ በጃንሆይ ዘመን ላይ ቆሜ ዛሬን የማየት ችሎታ ቢኖረኝ የጃንሆይን አገዛዝ ነቃፊ አልሆንም ነበር፤ ትናንትን ፣ የደርግን ዘመን ከዛሬው ከወያኔ ዘመን በመሠረቱ እምብዛም የማያለይ በመሆኑ አይናፍቀኝም፤ የዛሬው የወያኔ ዘመን አስመረረኝ፤ ምርር ብሎኛል፤ እንዳልሰደድ ቀዳማዊ ምኒልክ ያለውን ተከታይ ነኝ፤ እንዲህ ብሏል፡– ‹‹እናቴንና አገሬን እተው ዘንድ አይቻለኝም፤›› እናቴ ‹‹በጡቶቿ አምላኛለችና››፡፡
እናትና አባቴ የኢትዮጵያን ምድር ሆነዋል፤ አባቴ በማይጨው ዘምተው በጥይት ቆስለዋል፤ የመርዙንም ጋዝ በትንሹ ሳንባቸውን ሳይጠብሰው አልቀረም፤ ይቺን እናትና አባቴ አፈር የሆኑላትን አገር ትቼ መሰደዱ ስለማይሆንልኝ እየመረረኝ የመድኃኔ ዓለምን ምሕረት እጠብቃለሁ፡፡
ለምን የጃንሆይ ዘመን ይናፍቅሃል? ለሚለኝ የምሰጠው መልስ የሚከተለው ነው፤ በጃንሆይ ዘመን ኢትዮጵያ የታሪክ ክብርዋ ርዝራዥ ነበረ፤ ስለዚህ የኢትዮጵያ ሕዝብ ራሱን ችሎ በነጻነት የኖረ፣ በተደጋጋሚ የመጡበትን የተለያዩ ወራሪዎች እያሳፈረ የመለሰ ቆራጥ፣ ጀግናና ኩሩ ሕዝብ መሆኑን ዓለም በሙሉ አምኖ የተቀበለው ጉዳይ ነበር፤ በዘመኑም ከተባበሩት መንግሥታት ጦር ጋር ኮሪያ የዘመተው የኢትዮጵያ ጦር ከአሥራ ሰባት አገሮች አንዱ ቢሆንም አንድም ምርኮኛ፣ አንድም ሬሳ በጠላት እጅ ሳያስገባ የተመለሰ ብቸኛ ጦር ነበር፤ ያኮራል፡፡ ከኢትዮጵያ ለመውጣት ቪዛ ማገኘት ቀላል ነበር፤ በዚያን ጊዜ ምን ዓይነት ኢትዮጵያዊ ነው ለመሰደድ የሚያስብ? አሜሪካ በየዓመቱ የሚመድበውን የኢትዮጵያን የስደት ድርሻ የሚጠቀሙበት ጥቂቶች ግሪኮችና አርመኖች ነበሩ፤ አርባ ሺህ ግድም ጦር ይዛ የምትፈራ፣ ደሀ ሕዝብ አቅፋ የምትኮራና የምትከበር፣ ጮሃ ሳትናገር የምትሰማ አገር ነበረች፤ እምነት የሚጣልበት የጨዋ ሕዝብ አገር ነበረች፤ ይህ ነው የናፈቀኝ!
ዛሬ በየጋዜጣው ላይ የማነበውና የማየው ፎቶግራፍ አሳፈረኝ! ውርደቱ አንገፈገፈኝ! ከሁሉም ይበልጥ ደግሞ ምንም ማድረግ አለመቻሌ፣ ኢምንትነቴ ያንገበግበኛል፤ አንድ ወጣት በባቡር መንገድ ላይ ወድቆ አምስትና ስድስት ፖሊሶች እየተሻሙ በዱላ ሲደበድቡት፣ በጫማቸው ቦታ ሳይመርጡ ሲረግጡት እነዚህ ከኛው የተወለዱ፣ በእኛው ባህልና እምነት ያደጉ፣ ለሕዝብ ደኅንነት የተሰማሩ ናቸው ወይ? የሚፈጽሙት ግፍ ጀግንነት ይመስላቸው ይሆን ወይ? ልጆች ያላቸው ሚስቶቻቸውና ልጆቻቸው እነዚህን የግፍ ምስሎች በጋዜጣም ሆነ በቲቪ ሲያዩ እንደሚያማቸው ይገነዘባሉ ወይ? በሚያዝያ 30/1997 በሚልዮን የሚቆጠር ሕዝብ በጨዋነት ወጥቶ በጨዋነት ተበተነ፤ ለምን አይቀጥልም? እስከመቼ ተፈራርተን እንኖራለን? በሠለጠነ መንገድ መነጋገር አልቻልንም፤ በሰላማዊ ትግል መነጋገር አልቻልንም፤ በግድ ወደሕገ አራዊት መግባት አለብን?
ፕሮፌሰር መስፍን – የጨነቀው እርጉዝ ያገባል እንደሚሉት ሆኖ እንጂ የሃገራችን የፓለቲካና የህዝቦች ህብረት የፈረሰው ወያኔ የሃገር አለቃ እንደሆነ ነው። ወያኔ በበረሃ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን ለመከራና ለሞት የዳረገ አጥፊ ሃይል ነው። የሚያስበውና የሚራመደውም በጎጥ ፓለቲካ ነው። ዛሬ በሃገሪቱ የአመራር ቁንጮ ላይ ጉብ ያሉት ሁሉ እጃቸው በሰው ደም የተነከረ ስብዕና የሌላቸው የአንድ ዘር ጠባብ ብሄርተኞች ናቸው። የሚሰሩትን አያውቁም። ሞት የወሰዳቸው የወያኔ አለቃ አቶ መለስ የሃገሪቱን ስልጣን በእጃቸው ካረጉ በህዋላ ስለ ኤርትራ ነጻነት ጉዳይ አንድ ጋዜጠኛ እንዴት ሃገራችንን የባህር ወደብ አልባ ታደርጋላቹሁ ተብለው ሲጠየቁ “እኛ ጦርነት ስልችቶናል። እናንተ ከፈለጋቹሁ መንገዱን ጨርቅ ያድርግላቹሁ” ነበር ያሉት። ያው ብዙም ሳይቆይ 70 ሺህ ሰው የፈጀ ግጭት ደረሰ።
ያለፈው ዘመን የሚናፍቀው እርሶን ብቻ አይደለም። በቅርቡ ወደ ኤርትራ ብቅ ብየ ነበር። አቶ ኢሳይያስን ቀዩ መንግሥቱ ይሉታል። መልክ እንጂ የይዘት ለውጥ የለውም ለማለት ነው። እድሜ የጠገቡ ጥቂት ሴትና ወንድ ኤርትራውያን ደግሞ የሃይለሥላሴን ጊዜ ይናፍቁታል። የተለጎመ ህዝብ ስለሆነ በይፋ መናገር ግን ለመከራ ይዳርጋል። የአለም ህዝብ የወያኔ ፓሊሶች እንደ ተኩላ ያለምንም ርህራሄ ወጣቱን ሲጨፈጭፉት ማየት ይቀፋል። ራሳቸው በወያኔ ጥይት ተቦድሶ በሜዳ ላይ የወደቁት አያሌ የኦሮሞና የአማራ ተወላጆች አስከሬን የሚያመለክተው የወያኔን ጭካኔ ነው። እስቲ ትላንት የወያኔ መአከላዊ ኮሚቴ የሰጠውን መግለጫ እንይ። ሃገሪቱ በነጻንት ፍላጊዎች እየተናጋች እነርሱ በ 15 አመት ጊዜ ውስጥ አመጣን ስለሚሉት ለውጥ ያወራሉ። ወስላታ ሁሉ። መሰረት ያለው መንግሥት ቢሆን ኑሮ ህዝብን ለማረጋጋት፤ ስህተትን ለመቀበልና እንደገና ላለመድገም አርጋቢ ቃልና ተግባርን ይጠቀም ነበር። መግለጫው ግን አካኪ ዘራፍ ብሎ ሌላውን ከመወንጀል በስተቀር እዚህ ግባ የማይባል መግለጫ ነው። ወያኔ ለሃገር አይገደውም። ከተራ ወታደር እስከ ጄኔራል የራሱን ሰው ያሰለፈ፤ በዘሩ የሚነግድ ተባይ ነው። ለሃገር አንድነትና የወደፊት እድልፈንታ አስቦ አያውቅም። አራዊት ሆነው ሰውን አራዊት እንዲሆን የሚገፉትም እነዚህ አጥፊ ሃይሎች ናቸው። ያለቅጥ እንደፈራረሰው ደርግ የእነርሱም ውድቀት ቅርብ ነው። ያኔ የት ይገቡ ይሆን? ትግራይ? አይደረግም? በውጭ ሃገር የትም ቢሆን ለፍርድ እናቀርባቸዋለን። መሸሸጊያ የላቸውም።
God bless you Professor. As always thank you for your timely article. What are you going to do? It is hard for them to let go their wild mentality. They grew up in a jungle and came to power through gun and they are akways thinking the sky clear only for them. Sooner or later one day it will rain. What ever goes up must come down. This is the reality of nature. No one is hang in there for ever. God bless Ethiopia and it’s people. I wish you a healthy life prof.
pro.Mesfin is saying tommorrow you will remember weyane as Im now remembering King Haileslasse.Today ethiopia is one of the fastest growing economy in the world.The ethiopian army is keeping the peace of african brothers.After the defeat of the US army in Somalia ethiopian army is defeating the terrorists and to this day no ethiopian army fall in the hands of the savage Alshebab. Weyane is building a dam at the nile.This alone makes weyane number one ethiopian and african
Dear Professor,
You have contributed a lot and devoted your life to the betterment of this country. The past two regimes did not and are not listening to you. If they would be to listen and put into practice, your advice was the most practicable and savor of all of us, Ethiopians and would forbids us from this big mess. They had to respect your elder statesman-ship, your deep knowledge and experience about the country. Unfortunately, our country is not lucky. We live in the age of darkness and barbarism-40 years continuous infighting, kill each other, displacement leading to miserable life and hopelessness. Political and economic greed on few while leaving the majority population languish in destitution, second class citizenship and so and so forth is the practice of the day. Humanity has never lost ground in modern day Ethiopia now than ever in the country’s history. We lost our precious respect already we gained due to our fathers and grand fathers freedom struggle long before. The way our so called “Government” and our brother soldiers kill their own brothers and the people is beyond thinkable. Are they human beings?, are they Ethiopians?, are they sharing our history?Are they Christians? Are they Ethiopian Muslims? I don’t know where this much act of barbarism came and borrowed from. Wilderness, lawlessness, non-religiousness, inhumane, greed, irresponsibility and donkey-life-type-politics reigned. what stops this national failure and crisis we have dipped into is beyond imagination. How can we move on in this way is everybody’s question. Anyway, continue to contribute and fight your own fight professor for the sake of history. History will give the judgement.
ይህ ወቅት የህዝብ በደልና ግፍ ገደቡን አልፎ አደባባይ የወጣበት ጊዜ ሲሆን ሁኔታዉ የፈተነዉ ወያኔን ብቻ ሳይሆን እሱን በሀይል እንጥላለን ያሉትን ቡድኖች ጭምር ነዉ።
@ ፕሮፌሰር መስፍን
ግን እኮ ከመንግስት ሌላ እንዘጭ ያሉት እና ክብር ያጡት በተቃዋሚ ጎራ ያሉትም ጭምር ናቸው። እስቲ የተከበረ ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ሊያሰባስብ የሚችል ኣንድ የፖለቲካ ድርጅት ይጥሩልኝ? ኣደጋው ይህ መሰለኝ።
Tigrai is Tigraway.aleqe deqeqe . Besewoszum sirat siltan felgeh sayisakalih siqer meqawem meqawem…….,,.yehone dedeb shimagile
Thank you Pro. Mesfin for your wise remarks. I wish Woyane had 1% of your wisdom, amazingly their supporters have the same IQ like them because no one with a rigt mind support these beasts.
When I read the comment given by the Woyane supports above, I noticed that Woyanes think and do the same, they don’t pay attention to what is written, they don’t listen to people and they lie.
Let me give you a homework, please take time to read Pro. Mesfin’s input carefully and underline for me if there is a sentence where it says he will miss Woyane tomorrow!!
Ethiopians have come together to free themseles from blood sucker devils who kill our brothers and sisters to seure their stolen wealth.
Read histry, your time us finished, the blood of the innocent chikdren cried in front of God and He heard it from heaven.
It is done Woyane regime is hanging on a loose string.
We just give it harder pull.
It is so sour to swallow for those wealthy woyane supporters, but don’t be blinded, use the little IQ you have, your time is finished. Ethiopians are united, the army is waking up, they will soon be with the people, because now the know they are cheated and been used, you are rich and have masions and millions of dollars abroad to run to.
Adise to Woyane,
Please get out if you can now!!! I hate to see you being like the other dictetors whose bodies were dragged on the streets.
Please don’t force Ethiopians do such thing, leave now.
Take advise from a historian!!!
I hated Prof. Mesfin Wolde Mariam for two things:
1) The role he played in the downfall of Haile Selassie’s Government and the propping up of the military junta; and
2) His idiotic saying that there is no Amhara ethnic group as such during his debate with the devil Meles. By saying that, he discouraged Amharas from forming a strong organization because many misguided so- called intellectuals bought into his thinking. The result has been catastrophic for Amharas.
Having said that, I admire him for owning his mistakes.
When I think of the light treatment we got when demonstrating in Haile Selassie’s time and to what I see on videos, I do not believe my eyes even for a second. It shows how much our society has deteriorated, especially the Agazi beasts. I hope and pray Ethiopians will unite against them and drive them back to their home province.
@zewdei
Where is your home and yours home sir.
Acrobatist Mesfen all his life depend on weather, he was incaraging Meles Zenawi
Dear Prof., I agree, agree, and agree with you. I am very excited to read your introductory notes, except I left my country some 32 years ago.
Since we’re so naïve, we simply denounced Atse Haile Selassie’s regime and dreamt for Socialism (assuming that system will bring Development, Democracy, and Liberty to our beloved country). We never felt that Socialism was and is the cruelest, the most dictatorial, and the most backward social system HUMANITY ever practised. It’s a petty that the overwhelming majority of us were fooled at that time. Now, when I tell my friends that I with my generation is responsible for all the mess our country is experiencing, many do not like to take the responsibility. Well, one thing clear here is that we didn’t want all the evil to happen. We were just fooled. We’re naïve. (TESHEWEDIN!!! Big Time!!!)
አገር ልትፈርስ ነው። እስራት በዝቷል አመጽ በዝቷል ጥይት ከዚህም ከዚያም ጧጧ ማለት ዘምሯል። የስራ ማቆም አድማው በየአቅጣጫው ተጀምሯል። ወያኔም ይሁን ማንም ሊቆጣጠረው ከማይችለው ደረጃ ሊደርስ ይችላል። እንደ ፕሮፌሰር መስፍን አይነት ታዋቂ ግለሰቦች የመፍትሄ አቅጣጫ የሚጠቁሙበት ወቅቱ አሁን ነው።
ኮሎኔል ፍስሀ ደስታስ ዝምታን ለምን መረጡ? አንድ ይበሉን እንጅ
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም፤
መቼስ አለመታደል ሆነና ይህን ሁሉ እንዲያዩ እግዜር አስቀምጦዎታል። ዕድሜ ጥሩ ነው ብዙ ያሳያል ይባል የለ!
ይሁን እንግዲህ ከተሰጠን መቻል ነው ያለብን። መደማመጥ ካልቻልን፣ መከባበር ካልቻልንና አንዱ ሌላውን መዘርጠጥ ከሆነ ሥራው፣ ኢትዮጵያዊነቱ የት ላይ ነው። ዝም ብለን ነው እኮ ኢትዮጵያዊ እያልን ያለነው፣ የኢትዮጵያዊነት መገለጫው እኮ ባሁኑ ትውልድ ብቻ ሳይሆን በድሮ ነበርን ከሚሉት ጭምር እየጠፋ ስለሄድ ነው እዚህ ሁሉ ትርምስ ገብተን ያለነው።
ኢትዮጵያዊነት ማለት እኮ፣ እኔ እስከሚገባኝ አንተ/አንቺ ትብስ/ሽ ተባብሎ ተካፍሎ ችግርን የሚያሳልፍ፣ ይቅርታን የሚያደርግ፣ የእግዚአብሄር መፍራት የነበረው፣ ወዘተ… ስንት ተብሎ ይዘለቃል።
አሁን እነዚህን ነገሮች እያየናቸው ነው? ይቅር የመንግሥቱን አስተዳዳሪዎችና፣ እኛ ተራው ዜጎች እነዚህን እያደረግን ነው ወይ ያለነው?
እኛ ወንድምና እህቶቻችንን እየጠቆምን እያሳሰርን አይደለንም ወይ? ጥሩ ያልሆነ ነገር ሲሰራ ልክ አይደለም ብለን እንደመናገር፣ እየደገፍን እንቆይና ዘወር ብለን እያማን የምንውል ፈሪዎች አይደለንም?
የመንግሥቱ አስተዳዳሪዎችን ጉቦና ሌብነት በደላላነት ሆነን የምናገለግላቸው እነማን ሆነን ነው አሁን በራሳችን ድክመት ራሳችን ላይ እንደፈለጉት እንዲጨፍሩ የፈቀድንላቸውን ሰዎች ትከሻችን ተመችቷቸው እያለ ውረዱ ስንላቸው በቀላሉ የሚወርዱት?
አስመሳዮች ነን፣ ስለ ኃይማኖት ማውራት የማይሰለቸን ነገር ግን ኃይማኖቱ አድርግ የሚለውን ማድረግ ቀርቶ በብዙ ክንድ ቀድመን ሰይጣንን ለመብለጥ ውድድት የምናደርግ ስንቶቻችን ነን? ቤተ ክርስቲያን ይሁን ቤተ መስጊድ ዉስጥ የሚደረገው ሰዉን ጠልፎ ለመጣልና ራስን እንዲመች ለማድረግ የሚደረገው ክፋት ቤታችን ይቁጠረው።
ሰው አያይም ብንል እንኳን እግዜር ያየናል ብለን የማንፈራ፣ ምንድነው ከዚህ በላይ ቢመጣ የምንደነቀው? ባጠቃላይ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች የተባለው፣ እስካሁን ድረስ አልዘረጋችም ምክንያት በትዕቢት ህዝቦቿ ታጅለው እና ተወጥረው፣ የእግዚአብሄር መረገጫ የተባለች አገር የሰይጣን መፈንጫ እስክትሆን ድረስ መድረሷ፣ ገና ብዙ ነገር እናያለን። እስካሁንም ያለችው በጥቂት የእግዜር አገልጋዮች ሌት ተቀን ለቅሶና ምህላ እንጅ በኛ ተግባርና ግፍ ቢሆንማ ኖሮ፣ የለንም።
አሁንም ፕሮፌሰሩ እንዳሉት ያለፈውን እየናፈቅን እንሄዳለን እንጅ፣ ጥሩ መሥራት ካልተማርንና እንደ ወላጆቻችን ወደ እግዚአብሄር ፊታችንን መመለስ ካልቻልን፣ እንደ ህዝብ አገር የሌለው ህዝብ ሆነን በስደት ተበትነን እንደምንቀር የሚታይ ነው።
በጥላቻ ታውረን አንዱ ሊላውን ለማጥፋት ሸምቆ ዝንተ ዓለም የምንኖርንበትን አካኄድ ማቆም ይኖርብናል። እስኪ እኛ ራሳችን ጥሩ እንሁንና ቀጥለን አስተዳዳሪዎቻችንን ለመውቀስ እንሂድ!
ይቅር ባይነት፣ መቻቻል፣ ታጋሽነት መልካም ነው።
እግዚአብሄር ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይጠብቅ።
this mercenery tribe tegrea were hired by the arabe leagu to change the name from red sea to arab sea they finised thier contrat period; why they are in addis abeba or arab gave them componsation the amharaland that is why they genocide 15 million amhara or ararb told the genocide of amhara since thire blood is a mercenery weakn socite they hate every ethiopian those ugly face if i see tegrea oepole i canot eat food
ፕሮፍ አንድን መንግስት ደጋግመው ከተቹ ያ መንግስት እድሜ የለውም። ቀደም ባለው ጊዜማ ጊዜ እንስጣቸው ሲሉን አልነበረም? ክ30 አመት በሁዋላም ችግሩ ከገባቸው ጥሩ ነው። እንደውም ለነገር ማበላሹት የገቡት ንዛዜ መሰለኝ። ለማንኛውም እድሜና ጤንነት ይስጦት ምን እንላለን ኢትዮጵያዊ ስነ ስርአታችን ተሽርሺሮ አላለቀም ከዚህ በላይ ምን ይባላል?
ዉድ ፕሮፌሰር
ወደ ህገ-አራዊትነት መግባት አለብን ነዉ ያሉት? በእዉነት የምነግርዎት ወያኔ ህገ -አራዊትነቱን የጀመረዉ ቀደም ሲል ነዉ፡፡ ብዙዉን ታሪኩን እንዳልጽፍ ለቀባሪዉ አረዱት ነዉ የሚሆነዉ ፣ ከእኔ በተሻለ እርስዎ ያዉቁታል ፡፡ በቅርቡ በባህር ዳር ህዝብ ላይ የተፈፀመዉን ግን እኔ የአይን ምስክር ስለሆንኩ ትንሽ ልንገርዎ ዕለቱ እሁድ ነሃሴ ስምንት ቀን ነዉ ፣ የባህር ዳር ከተማ ህዝብ የተለያዪ ጥያቄዎችን በማንሳት ሰላማዊ ሰልፍ አካሄደ በእርግጥም ሰልፉ ሰላማዊ ነበረ ፣ ሁሉም ሰዉ ወደ መስቀል አደባባይ ሄደ ከዚያም በከተማዊ ዋና ዋና መንገዶች ጥያቄዉን ካስተጋባ በኃላ በመጨረሻ የወያኔ ደህንነቶች አቀነባብረዉ ወጣቱን ሰልፈኞች ወደ ከተማዉ ዳርቻ ማለትም አባይ ማዶ ወደተባለዉ ሰፈር ወሰዱት ሽማጋግሌዎችና መካከለኛ እድሜ ላይ ያለነዉ ስለደከመንና ሩቅ ስለሆነ መሃል ላይ ቁጭ አልን ፣ ወጣቱ አባይን ከተሻገረ በኃላ አጋዚ ዙሪያዉን ከቦ በመትረጌስ ጨፈጨፋቸዉ በዕለቱም ከ57 በላይ ንፅሃን ሲገደሉ ከ75 ባላይ ቆሰሉ፡፡ በእዉነት ነዉ የምለዉ እንዲህ ያለ እልቁት በአንድ በአንድ ቦታ ይፈፀማል ብሎ ማንም ሊየምን አይችልም ንፅሃን ራሳቸዉ ደመወዝ በሚቆርጡላቸዉ ወታደሮች ተጨፈጨፉ፤ ከዚህ በላይ ህገ -አራዊትነት ምን አለ ፡፡ ስለዚህም ይህ መንግሥት የህዝብ መንግሥት ፣ በሥርዓት የሚገዛ መንግሥት ፣ ሰባዊነት የሚሰማዉ መንግሥት ሳይሆን በህገ-አራዊትነት የሚመራ መንግሥት ነዉ ፡፡ እርሱ የሚያዉቀዉ መግደል ፣ መጋደል ፣ መግረፍ ፣ማሳደድና በጠቅላላዉ መጨፋጨፍ ነዉ፡፡
Little point taken from Article entitled “Research in and by the Third world, By Prof. Mesfin Wolde-Mariam, March, 1985): It shows our deep root poverty & starvations
Western technological civilization is built on the uncompromising acceptance that Knowledge is Power. In backward societies the conception of knowledge is reversed and becomes power is knowledge. Political power is recognized as the fountain of all knowledge’s. That is why that in backward societies what matters is not what is said but who says it.
ተናግረህ ባታናግረን ጥሩ ነው፡፡
ስለዘገያችሁ ብዙም የምትቀይሩት ነገር አይኖርም፡፡
እርግጥ ነው ህውሃት የሚባለውን ዘረኛ ድርጅት የፈጠርነው እኛው ነን፡፡ለአላማችንም በጥሩ ሁኔታ እየተጠቀምንበት ነው፡፡ለትግራይ ልሂቃን በአጠቃላዩ ተንኮልን ያሰተማርናቸውና ያሰለጠናቸው እኛው ነን፡፡ታሪካዊ ቅድስት ኢትዮጵያን በቁጥጥራችን ስር የማድረግ የረጅም ጊዜ ህልም ነበረን፡፡የእያንዳነዱን ኢትዮጵያዊ የህብረተሰብ ክፍል ስስ ብልትና አመለካከት በቂ ጊዜ ወስደን በቅጡ አጥንተን ነው የተንቀሳቀስነው፡፡በዘር በሃይማኖት በፆታ በእድሜ በሁሉም ዘርፍ ቀዳዳዎችን አጥንተናል፡፡ህልማችንን ለማሰካት ሀ-ብለን የጀመርነው ግን ንጉሳዊ አገዛዙን በመጣል ነበር፡፡ለምን ቢባል ንጉሳዊ አገዛዙ የእውነተኛይቱ ፅዬን ሀቀኛ የበላይ ጠባቂ ነበር፡፡ንጉሳዊ አገዛዙ እውነተኛ የፅዮን ልጅ እና ቀናኢ የኢትዮጵያ ሙሽራ ባልተቤት ነበር፡፡አሁን ግን ሙሽሪት ኢትዮጵያ በውሽሞች በደላሎች የቀን ጅቦች እና ተኩላዎች እንድትተዳደር ነው ያደረግነው፡፡ንጉሱን ስንገረስስ ቀጥሎ ቤተክርስቲያኒቱንም ቀስ በቀስ ለመገዝገዝ እንደምንችል እናውቅ ነበር፡፡ምክንያቱም ንጉሳዊ አገዛዙና ቤተ-ክርስቲያን እጅና ጓንት ነበሩ፡፡ሁለቱ እጅና ጓንት ሆነው ኢትዮጵያን ጠንክረው ከውጪ ጠላት ለመከላከልና ማንነቷን ለማስጠበቅ ችለዋል፡፡ንጉሱን ለመጣል ጥራዝ-ነጠቅ ምህሩን ተጠቅመንበታል፡፡ምክንያቱም ምሁሩ ሳያገናዝብ ዝም ብሎ በመጤ አዲኦሎጂ በጭፍን የሚነዳ ከብት ነበር፡፡ሶሻሊዝም ስንለው ሶሻሊዝም ኮሙኒዝም ስንለው ኮሙኒዝም ይላል፡፡ቀጥሎ ደግሞ ካፒታሊዝም ስንለው ካፒታሊዝም ዲሞክራሲ ስንለው ዲሞክራሲ ሊበራሊዝም ስንለው ሊበራሊዝም ብሎ ይጮሃል፡፡የነገርነውን ነገር በደንብ ሳይመረምር እንደ ገደል ማሚቶ መልሶ ያስተጋባልናል፡፡የሀገሩንና የአለም ታሪክ ማገናዘብ የሚባል ነገር የለም፡፡የሰውንም ውስብስብ ባህሪ ገና በቅጡ አልተረዳም፡፡ይህንን ግልብ ምሁር እና ደርግን ተጠቅመን ንጉሳዊ አገዛዙን ስንገረስስ በዙሪያው ያለውንም የልሂቃን ስብስብ ጨምረን ነው አብረን ያዳከምነው የገረሰስነውና ያጠፋነው፡፡ንጉሳዊ አገዛዙን ብቻም ሳይሆን በዙሪያው ያለውን እርዝራዥ ልሂቃንና ወጣት ምሁሩንም ጭምር በቀይ-ሽብር ነጭ-ሽብር ለማጥፋት ደርግ የተባለውን ሃይል እስከመጨረሻው ውድቀቱ ድረስ በዘዴ ተጠቅመንበታል፡፡እንደዚህ እያደረግን የአላማችን ታማኝ አገልጋይ የሆኑትን የትግራይ ልሂቃኖችን ለስልጣን እስከምናበቃ ድረስ እውነተኛዎቹን የፅዮን ልጆችና ቀናኢ የኢትዮጵያን ባሎች ሁሉ ቀበቶ አስፈትተን ሱሪያቸውን በዘዴም በሃይልም ስናስወልቅ ቀጥሎ ኢትዮጵያንም የክብር ቀሚሷን እንደምናስወልቃት ሳይታለም የተፈታ ነበር፡፡ሀገር በሴት ትመሰላለች አይደል የሚባለው፡፡ታሪካዊት ድንግል ቅድስት ኢትዮጵያም የክብር ቀሚሷን አውልቃ በዘመኑ አባባል ሬፕ መደረግ ጀመረች፡፡በውሽሞች በደላሎች የቀን ጅቦች እና ተኩላዎች የምትተዳደረው ኢትዮጵያ የክብር ቀሚሷን አውልቃ እንደ ሴተኛ አዳሪ ክብሯን ሸጣ በምታገኘው የውጪ ዶላር ዩሮና ፓውንድ አርተፊሻል የኢኮኖሚ እድገት እንድታስመዘግብ እያደረግን ነው፡፡የሚገርመው ደግሞ 15 ሚሊዮን ልጆቼ ተራቡብኝ እርዱኝ እያለችን ነው፡፡እኛ ግን ተይ አትቀልጂ እስኪ ቀናብለሽ ተመልከቺ ፎቁን መንገዱን አድገሻል ተመንደገሻል እያልናት ነው፡፡የኢኮኖሚ ሴክተሩንም ሆነ ተመዘገበ የሚባለውን አሳሳችና አርተፊሻል የኢኮኖሚ እድገቱን ለራሳችን አላማ በሚጠቅመን አቅጣጫ አስበንበት ነው ያዋቀርነው፡፡ስለዚህ 15 ሚሊዮን ህዝብ ቢራብ እና የቀረውም በገፍ ቢሰደድ ብዙም የሚገርም አይደለም፡፡ከላይ እንደተገለፀው የእያንዳንዱን የህብረተሰብ ክፍል ስስ ብልትና አመለካከት በደንብ አድርገን ውስጣ ውስጡን መርምረን አጥንተናል፡፡ምሁሩ ምን ይፈልጋል? ፖለቲከኛው ምን ይፈልጋል? ወጣቱ ምን ይፈልጋል?ሴቱ ምን ይፈልጋል?ወንዱ ምን ይፈልጋል?እስላሙ ክርስቲያኑ ምን ይፈልጋል ? ትግሬው አማራው ኦሮሞው ወዘተ ምን ይፈልጋል? ገጠሬው ከተሜው ምን ይፈልጋል? የሁሉንም እንደበአቱ ለማጥናት ሞክረናል፡፡ማስመሰልና ምስጢራዊነት የጥንካሬያችን ዋና ምንጭ ናቸው፡፡እራሱን እውነትን ሳይሆን እውነት የሚመስልን ነገር ማቅረብ እንዳለብን እንረዳ ነበር፡፡እውነትንማ ማንም ተስማምቶት እንደማይወደው እናውቃለን፡፡ምሁሩና ፖለቲከኛው ነፃ-ፕሬስ ዲሞክራሲና ሌሎችንም አይዲኦሎጂ የሚባሉትን ቲዎሬቲካል ነገሮች በጭፍን ማራገብ እንደሚወድ ተረድተናል፡፡ብዙም ተግበራዊነት የሌላቸውን ቲዎሬቲካል ነገሮች በማቅረብ ደረጃ በማስመሰል ክህሎታችን ተጠቅመን ማህበረሰቡን ማደናገር ችለናል፡፡የኢትዮጵያ ምሁርና ፖለቲከኛ ቀስ በቀስ እግዚአብሄር የሚለውን ጉዳይ ከልቦናውና ከአእምሮው እንዲፍቅና በአለማዊ እውቀቱ ብቻ እንዲመፃደቅ ማድረግ ችለናል፡፡ዳርዊንዝምን ሴኩላር-ሁማኒዝምን ኮሙኒዝምን ካፒታሊዝምን ሊበራሊዝምን ወዘተ ተመሳሳይ አስተሳሰቦችን በምሁሩና በፖለቲከኛው አስተሳሰብ ውስጥ አስርፀናል፡፡ሁሉም አይዲኦሎጂ እጃችን ያለበት የእኛው የፈጠራ ውጤት፡፡ነገር ግን የሁሉም ቲዎሬቲካል አይዲኦሎጂ ድብቅ አላማ መጨረሻ ላይ የሰውን ልጅ ከፈጣሪ አምልኮት ማስካድና የእኛ ተከታይ ማድረግ ነው፡፡በእርግጥ ሁሉንም የምናቀርባቸው በማር የተለወሱ መርዞች አድርገን ነው፡፡ለምሳሌ ሴኩላር-ሂዩማኒዝም ስንል ሰሙና ወርቁ የተለያየ ነው፡፡ውጪያዊ ሰሙ ለሰው ልጅ ከፍተኛ ሰብዓዊነትን ማላበስ ወይንም ለሰው ልጅ ሰብዓዊ ፍቅርና አክብሮት ማሳየት የሚል ሊመስል ይችላል፡፡ውስጣዊ ቅኔው ግን ሌላ ነው፡፡ ማለትም ሰው በራሱ ለራሱ አምላክ ነው ስለዚህም ሰው የአምላኩን መመርያ ሳይከተል የራሱን ውስጣዊ ፍላጎቱንና አመለካከቱን ብቻ በመከተል እውነተኛ ማንነቱን እና የመጨረሻውን የስውነት ደረጃውን እራሱ በራሱ ማግኘት ይችላል የሚል ነው፡፡በአጭሩ እግዚአብሄር የለም ማለት እራስህን አምልክ እራስህን ተከተል ማለት ነው፡፡እንደዚህ እያደረግን ብዙውን ምሁር አሳስተናል፡፡ወደ ወጣቱ ትውልድ ስንመጣ የአውሮፓ ኳስ ፊልም ጫትና አደንዛዥ እፅ ሌላውንም ብልጭልጭ ቁሳቁስ በገፍ አቅርበንለታል፡፡ለሴቶቹ ፋሽን ኮስሞቲክ እና በአጠቃላይ ብልጭልጭ የሆነውን ማቴሪያል ነገር ሁሉ በገፍ አቅርበንላቸዋል፡፡ይህ ብቻውን ስለማይበቃ ሴቶቹ በራሳቸው የቅዠት አለም ውስጥ እየተቅበዘበዙ እንዲኖሩ ማድረግ አለብን፡፡ለዚህም እንዲረዳን ስሜታዊና የተፈጥሮ ደካማ ጎናቸውን በመጠቀም የሴቶች ነፃነት የፆታ እኩልነት የሴቶች ጥቃት የሚለውን በመርዝ የተለወሰ ማር አቅርበንላቸዋል፡፡ሴቶች በተፈጥሯቸው አቅጣጫ መሪ ጠባቂና ሃይ ባይ ከሌላቸው በቀላሉ እንደሚበላሹ ጥንቱንም እናውቃለን፡፡ለዚህ እንዲረዳንም ፌሚንዝምን በማስፋፋት በወንዶችና በሴቶች መካከል ጥላቻንና ጥርጣሬን በማራገብ በመካከላቸው የፆታ ጦርነት ከፍተናል፡፡በመካከላቸው ድልድይ ሳይሆን ግንብ ገንበተናል፡፡ሴቱን ወንድ ወንዱን ሴት አድርገነዋል፡፡በፊልሙ በሚዲያው በመዝናኛው በአካዳሚው ወዘተ አማካኝነት ልቅ ወሲብን ሽርሙጥናን ግብረ-ሰዶምንና አስፋፍተናል፡፡እውነቱን ሃሰት ሀሰቱን እውነት ጥሩውን መጥፎ መጥፎውንም ጥሩ አስመስለን አቅርበነዋል፡፡በዚህም የማህበረሰቡን የቆየ ወግ ባህል ሞራል ሃይማኖት ታሪክ ፈሪሃ-እግዚአብሄር በርዘን እያፈራረስነው ነው፡፡ወሲብ ገንዘብና ስልጣን የሰው ልጅ ደካማ ስስ ብልቶች እንደሆኑ እናውቃለን፡፡የማህበረሰብ ዋና መሰረት የሆነውን በጋብቻ ጥምረት የሚፈጠረውን ቤተሰብ የሚባለውን የተከበረ የሰው ልጅ የቆየ ተፈጥሯዊና ማህበራዊ ተቋም ቀስ በቀስ ዋጋ እንዲያጣና እንዲፈራርስ እያደረግን ነው፡፡ስለዚህም ማህበረሰቡ በማንኛውም አቅጣጫ አንድ ሆኖ ተረጋግቶና ጠንክሮ አቅም አግኝቶ ሊታገለን አይችልም ማለት ነው፡፡በህብረተሰቡ ውስጥ የተለያዩ ጊዚያዊ አጀንዳዎችን በመፍጠር ከራሱ ውስጣዊ ማንነት እና ከአምላኩ ጋር የሚገናኝበት ማህበረሰባዊ ፋታ አሳጥተነዋል፡፡ለማህበረሰቡ ዲሞክራሲን እራሱን በራሱ ማጥፊያ እንዲሆን አድርገን አቅርበንለታል፡፡ቅድሚያ እራሱን በደንብ የማያውቅ ማህበረሰብ እንዴት ብሎ እራሱን በራሱ እንደ ሀገር ሊያስተዳድር ይቻለዋል?መንግስተ-ሰማያት እንኳን በተጋድሎ በእምነት ፅናትና በምግባር እንጂ በዲሞክራሲ ይገባል እንዴ?ዲሞክራሲና ነፃነት እንደ ተግባርህ የሃላፊነት ደረጃና መጠንህ በአቅምህ ተመጥኖልህ የምታገኘው የመብት ትሩፋት ነው፡፡እኛ የምናምነው እንደዚያ ነው፡፡ዋና ተቀናቃኞቻችንም የሚያምኑት እንደዚያ ይመስለናል፡፡ስለዚህ ዲሞክራሲ የሚባለው ቅዠት ለሁሉም ሰው ያን ያህል እንደማይሰራ ጥቂቶች ልሂቃን ብቻ ያውቁታል፡፡ዲሞክራሲ የሚባለውን ነገር ንጉሳዊ አገዛዞችና ቤተ-ክርስቲያን አንድ ሆነው የመሰረቱትን የቆየ ጠንካራ ስርአት ለመገርሰስ እንደ ዋና መሳሪያ ተጠቅመንበታል፡፡
ምክንያቱም ህዝቡን እርስ በርሱ አስማምተው ከራሱም ከአምላክም ጋር አንድ እንዲሆን በማድረግ ለብዙ ዘመናት ዋና አስቸጋሪዎቹ ተቀናቃኞቻችን የሆኑት እነሱ ነበሩ፡፡ለማንኛውም ዲሞክራሲ የሚለውን የላም አለኝ በሰማይ ቅዠት ወይንም ኢሉዥናል ፋንታሲ በማህበረሰቡ ውስጥ ፈጥረናል፡፡የእኛ አጀንቱር ምሁራኖችና ፖለቲከኞቻችንንም ለዚህ የቅዠት ድራማ ተግባራዊነት እንዲረዱን ተባባሪ አድርገናቸዋል፡፡ህዝቡን ሳይሆን እኛን ነው የሚያገለግሉት፡፡ምክንያቱም እኛ ነን ጠቀም ያለ ገንዘብ ፈንድ የምናደርጋቸውና በምርጫ ሽፋን ለስልጣን የምናበቃቸው፡፡ በዩዘሪ እና እስፔኩሌሽን ላይ በዋናነት የተመሰረተው ዘመናዊው አለም-አቀፋዊው ፋይናንስ ካፒታሊዝም አለምን በማንኛውም አቅጣጫ በመዳፋችን ቁጥጥር ስር ለማድረግ የተጠቀምንበት የራሳችን ንብረት የፈጠራ ውጤት ነው፡፡ህውሃቶች ዶላር ከሰጠናቸውና ስልጣናቸውን ከጠበቅንላቸው ሀገሪቱን ከነህዝቦቿ አሳልፈው እንደሚሸጡሉን እንተማመናለን፡፡በእርግጥ ኢትዮጵያ ውስጥ ዜጋው በገዛ ሀገሩ የህውሃቶች የመሬት ጭሰኛ ተደርጓል፡፡በገዛ ሀገሩ ሀገሩን ተቀምቶ ከሁለተኛ ዜጋ በታች እንዲወርድ ተደርጓል፡፡ህውሃቶች መሬትና በገፍ የሚያትሙት ብራቸው ከእኛ ሁለ-ገብ ድጋፍ ጋር ተጨምሮ ሌላውን ዘር በተለይም አማራውን እያሰቃዩና እየገፈተሩ ሀገሪቱን በማንኛውም አቅጣጫ ለመቆጣጠር አስችሏቸዋል፡፡ይህ አካሄድ መጨረሻው ጥሩ እንደማይሆን እናውቃለን፡፡ነገር ግን አላማችንን እስካሳካልን ድረስ ማን ወደቀ ማን ተነሳ ግዳችን አይደለም፡፡ጦር ማዝመት ሳያስፈልገን ገንዘብና ቁሳቁስ ብቻ በማቅረብና ባህሉን ሃይማኖቱን ታሪኩን በመበረዝና በዘር በሃይማኖት በፆታ እርስ በርስ በማናከስ ብቻ ኢትዮጵያን በቁጥጥራችን ስር አድርገን ቀስ በቀስ ለማፈራረስ እድሉን አግኝተናል፡፡አላማችንን ለማሳካት ስንል ለአገልጋዮቻችን በገፍ የምናቀርበው ገንዘብና ቁሳቁስ ጠቀሜታው ወደ መታሰሪያው በረት ወይንም ወደመታረጃው የሚያመራው በሬ አሞሌ ጨው እየላሰ እንደሚሄደው ከብት ማለት ነው፡፡በተረፈ ኤትኒክ ፖለቲክስ ስለምትሉት ጉዳይ ከአላማችን ውጪ የትኛውም በሄር የሚባለው ነገር ለእኛ የተለየ ወዳጃችንም ሆነ ጠላታችን አይደለም፡፡
ለትግሬው ያለን ጊዚያዊ ወዳጅነትም ሆነ አማራ ከሚባለው ጋር ያለን ጊዚያዊ ቅራኔ ከአላማችን እና አላማችን ጋር ብቻ የተያያዘ ነው፡፡አላማችንን እስከደገፈ ድረስ ሁሉም ጊዚያዊ ወዳጃችን ነው አላማችንንም እስከተቃወመ ድረስ ሁሉም ጊዚያዊ ባላንጣታችን ነው፡፡ለእኛ ሁሉም የአዳም ዘር አንድ አይነት ነው፡፡እኛ እንደዚያ ነው የምንመለከተው፡፡የእናንተን አመለካከት ግን አናውቅም፡፡
እርግጥ ነው የእያንዳንዱን በሄር ወይንም ሃይማኖት ስስ ብልትና አመለካከት ለራሳችን አላማ እንደመዳረሻ በጊዚያዊ መሳርያነት በብልሃት እየተጠቀምንበት ነው፡፡ሁሉንም ነጣጥለን ተራ በተራ እየለየን ለማዳከምና ለመምታት እንዲመቸን እያንዳንዱ በየራሱ የነፃነትና የዲሞክራሲ የቅዠት አለም ኢሉዥን ውስጥ እንዲኖር እድል ፈጥረንለታል፡፡በአጭሩ ብሄር በሄረሰብን ለከፋፍለህ ግዛው ስልታችን በዘዴ እየተጠቀምንበት ነው፡፡የህውሃት ተቃዋሚ ናቸው የሚባሉቱ ብዙዎቹ ተቃዋሚ ተብዬዎችም የኢትዮጵያ ምሁራኖችና ፖለቲከኞች በፀጉር ስንጠቃ ንትርክ ጥቃቅን ልዩነቶቻቸውን እያራገቡ ለሀገራቸውም ለህዝባቸውም ትርጉም ያለው ስራ እንዳይሰሩ ዲሞክራሲ ብሄር ብሄረሰብ እያልን በአፍራሽ ተግባር ውስጥ ተብትበን ይዘናቸዋል፡፡ለምንድነው ተስማምታችሁ አንድ ትርጉም ያለው ነገር ለሀገራችሁና ለህዝባችሁ የማትሰሩት ሲባሉ የሚመልሱት መልስ አለመስማማትም ዲሞክራሲያዊ መብታችን ነው የሚል የምሁራዊ የድንቁርና መልስ እንዲሰጡ እያደርግናቸው ነው፡፡ምናልባትም መለሳችን ኢዲዬት ብሎ የሰደባቸው ለዚህ ሳይሆን አይቀርም ይባላል፡፡
ብዙዎቹ እርስ በርስ መጠላለፍን እንደ አዋቂነት የሚቆጥሩ ብልጣብልጥ አድርባይ ከሃዲዎችና ሆዳሞች ናቸው፡፡ስልጣንን የሚያዩት የራሳቸው ሊያደርጓት እንደሚጎመጁባት ቆንጆ ልጃገረድ ሴት አድርገው ነው፡፡የስልጣን ክብሩንና ጥቅሙን እንጂ ይዞት የሚመጣውን ሃላፊነትና መዘዝ ፈፅሞ አይረዱትም፡፡በዚህ ባህሪያቸው ለእኛ ጥሩ ታማኝ አገልጋይ መሳሪያዎች ሆነው እያገለገሉን ነው፡፡ብዙዎቹን ተቃዋሚ ተብዬዎችን ህዝቡን እንዲያደናግሩልን ህውሃቶቻችን ደግሞ እኛ በምንፈልገው መንገድ ህዝቡን እንዲገዙልን ያስቀመጥናቸው አገልጋዮቻችን ናቸው፡፡ሁለቱም በየፊናቸው የእኛኑ ስራ ነው የሚሰሩልን፡፡ከዚህ አንፃር የትግሬ ልሂቃን ባንዳዎች በብዛት ግንባር ቀደም መሪ አገልጋዮቻችን ናቸው፡፡ነገር ግን ከሁሉም ብሄር ብሄረሰብ ከአማራውም ከኦሮሞውም ከጉራጌውም ከሌላውም ተመሳሳይ አገልጋይ ልሂቃን ባንዳዎችን በየደረጃውና በየአይነቱ ለምንፈልገው ተግባር በየአቅጣጫው አሰልፈናል፡፡ነገር ግን ለእኛ አስቸጋሪ ፈተና የሆኑቱ ብሩህ አእምሮ የታደሉቱ ብልሆቹና ቀናኢዎቹ ኢትዮጵያውያኖች ጥቂቶች ናቸው፡፡እነዚህን አብዛኛዎቹን ቀናኢ ኢትዮጵያውያን ለእኛ አደገኛ ስለሆኑ ቀስ በቀስ በሂደት በዘዴ ግማሾቹን አዳክመናቸዋል ግማሾቹን አስወግደናቸዋል፡፡ለወደፊቱ ግባችን ዋና ፈተና ሆና የተጋረጠችብን ቤተ-ክርስቲያኑቱና እርሷን የመጨረሻ የህልውናቸው መሸሸጊያ ያደረጉና በእምነታቸው የፀኑ ምእመናን ብቻ ነው፡፡ለዚህ ፈተና ዋና ጋሻችን ገንዘባችን ነው ብለን እናስባለን፡፡ቤቴን የንግድ ቤት አደረጋችሁት ብሎ በጅራፍ ገርፎ የሚያባርረን ያለ አይመስለንም፡፡በገንዘብ የማንገዛው ነገር የለምና፡፡ቤተ-ክርስቲያኒቱን ልማት በሚል አሳሳች ፈሊጥ ከሃይማኖትና መንፈሳዊ ተቋምነት ወደ አለማዊ የኢኮኖሚ ተቋምነት ለመቀየር ቀስ በቀስ ጥረት እናደርጋለን፡፡በገንዘብ የገዛናቸውን የራሳችንን ሰዎች ወይንም አጀንቱር እንደተለመደው በሁሉም መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት ውስጥ በሰፊው በኢንፍልትሬሽን አስርገን አስገብተናል፡፡ሁልጊዜም እንደምናደርገው በገንዘባችን ብዙ አርተፊሻል ድርጅቶችንና ሃይማኖቶችን እንደአሸን እንዲፈሉ ማድረግ እንችላለን፡፡እውነተኛውን ጥሩውንና ንፁሁን ነገር ሁሉ የምናበላሸው የምናዳክመውና የምናጠፋው በቀጥታ ፊት ለፊት በመጋፈጥና በመቃወም አይደለም፡፡ከፊት ከኋላ ከግራ ከቀኝ ከላይ ከታች በሁሉም አቅጣጫ የውሸት ነገሮችን አመሳስለን በማቅረብና በሂደት ቀስ በቀስ በማሳሳትና አቅጣጫ በማሳት ነው፡፡እናንተ ፐርቨርዥን የምትሉትን ተግባራዊ በማድረግ ማለት ነው፡፡ሌላው ያው እንደሚታወቀው ማስመሰለንም በእጅጉ የተካንበት ነው፡፡ከውጪ ያማረ የተፃፈ የታይታ ህጋችንን ለህዝባዊ መልካም ግንኙነታችን ማሳመሪያነት አልፎ አልፎ ስንጠቀምበት በአብዛኛው በተግባር የምንፈፅመው ግን ያልተፃፈውን የውስጥ ህጋችንን ነው፡፡ላለፉት 25 ዓመታት በኢትዮጵያ ላይ የሰራነው ስራ ይኸው ነው፡፡ኢትዮጵያ እንደ አቡነ-ጴጥሮስ አይነት ቀናኢ የሃይማኖትና የሀገር ሰማእት እንደሌላት ተረድተናል፡፡ሁሉም በጥቅምና በስልጣን ሀገሩን እንደሚሸጥ አውቀናል፡፡የሚላስ የሚቀመስ ያጣ ብዙ ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ እንዳለ ሁሉ ወገኑን እየዘረፈ በሙስና ሀብት አከማችቶ የስጋ ምቾቱ ቁንጣን እረፍት የነሳውን የህብረተሰብ ክፍልም ለእኛ እንደሚታረድ ከብት ወደፈለግነው አቅጣጫ እየመራን ለራሳችን መጠቀሚያ ለማድረግ ብዙም አይከብደንም፡፡ስለዚህም በጥቅምና በስልጣን ብቻም ሳይሆን አንዳንዴም በወሲብ ቅሌት ጭምር የፈለግነውን ማንበርከክና የአላማችን አስፈፃሚ አገልጋይ ማድረግ እንችላለን፡፡በኢትዮጵያችሁ ውስጥ ድህነትንም ሀብትንም ጎን ለጎን በተቃራኒ አቅጥጫ ግራና ቀኝ ስናስፋፋ ሁለቱንም ለራሳችን መጠቀሚያ ለማድረግ እንዲመቸን አድርገን አስበን ነው፡፡ድሃውም በድህነቱ ሃብታሙም ለምቾቱ የእኛው ጥገኛ እንዲሆን በማድረግ ሁለቱንም ከአምላካቸው እንዲራራቁ ማድረግ ዋና አላማችን ነው፡፡ሃብታሙ ለምቾቱ ድሃውም ለህልውናው ሰርቫይቫል ቀጣይነት ሲል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የእኛው የእኛው ጥገኞች ሆነዋል፡፡በዚህም እያንዳንዱ የህብረተሰብ ክፍል እርካታና እርጋታ የተለየው ተቅበዝባዥ እንዲሆን ማድረግ ችለናል፡፡የሰውነት ባህሪውን እየረሳ ወደ እንስሳዊ የአውሬነት ባህሪ እንዲቀየር እያደርግነው ነው፡፡
አንገቱ ላይ ባስገባንለት ልጓም ወደፈለግነው አቅጣጫ ልንጋልበውና ልንመራው በእጃችን ስር ነው፡፡
እንደ ባህሪውና አመለካከቱ የእስር ገመዳችንን ያሳጠርንበትም ሆነ ያስረዘምንለት የህብረተሰብ ክፍል ዞሮ ዞሮ በእኛው በረት ውስጥ ነው ያለው፡፡አንድ ነገር ብቻ ነው ከእኛ መዳፍ ወይንም የባርነት ቀንበር ስር ሊያወጣችሁ የሚችለው፡፡እውቀታችሁ?ሃሃ ሄሄ ይህማ ከእኛ አዋቂና ጠቢብ የሆነ ላሳር ነው፡፡ያውም ግልብ የሆነው ጥራዝ-ነጠቅ እውቀታችሁና ጥበባችሁ ሊያድናችሁ? ሃሃ ሄሄ ይህማ አያድናችሁም፡፡ፈፅሞ ፈፅሞ፡፡የአለማዊ አስተሳሰብ ፍቅራችሁና አንድነታችሁ? ሃሃ ሄሄ ይህም እውቀትና ጥበብ የሌለው የቁጥር ብዛት አንድነት መንጋ መሆን ብቻውን ምንም ዋጋ የለውም፡፡
በአምላካችሁ ላይ ባላችሁ የፀናና የጠራ ፍቅራችሁና እምነታችሁ የፀጋ ልጅነታችሁን ማስጠበቅ ስትችሉ ብቻ ነው ከእኛ ባርነት ነፃ መውጣት የምትችሉት፡፡ይህንን ፈተናችንን ተቋቁሞ ከእኛ የባርነት ቀንበር ነፃ ለመውጣት የሚችል ካለ ይህንን ካላይ ያለውን እውነት አሳውቀን ከእስራታችን ለመፈታት የሚችል ካለ እድሉን እንሰጣለን፡፡እኛም እንደ አምላካችሁና እንደ አምላካችን በነፃ-ፍቃድ ላይ የተመሰረተ የመወሰን እድል መርህን በማክበር እናምናለን፡፡እሳቱም ይኸው ውሃውም ይኸው እጅህን የፈለክበት ስደድ እንደሚባለው ማለት ነው፡፡ከዚያ ውጪ እየነካካችሁ አታናግሩን፡፡እናንተም ወደ ስራችሁ እኛም ወደ ስራችን፡
Yebesebese mot ayferam . He is on the verge of death,
ጓድ/ብጻይ ፕሮፌሰር ኢትዮጵያውያንን የሚገርማቸው ያለመሰደድዎ ሳይሆን ከየዘመኑ አምባገነኖች ጋር በሰላም መኖርዎ ነው። እነ ፕሮፌሰር አስራትና ሌሎች ሰማእታት እንዴት እንደርስዎ አላውቅበት አሉ? ለማንኛውም ይህን የሰለቸና ቀፋፊ ወሬዎን ትተው ከመሞትዎ በፊት (ደደብ ቲፎዞዎችዎን እንደሸወዱት ሞትን እስከዘለአለም ሸውደው መኖር አይችሉምና) ለተከታይዎችዎ ደርግና ወያኔን ከመሳሰሉ ነብሰ በላ ስርአቶች ጋር እንዴት ተገዝቶና ተዋርዶ መኖር እንደሚቻል መጽሐፍ ይጻፉላቸው። መቼም እርስዎ የአርበኝነትና የአልገዛም ባይነት ቅርስ ማውረስ አይችሉምና። ባንድ ወቅት አንድ ጸሐፊ `እድሜ ሁሌም ጸጋ አይደለም` ያሉት ከማንም በላይ እርስዎን ገላጭ ነው። ታሪክዎ ከነስብሐት ነጋ፡ ጓደኛዬ ከሚሉት አረመኔው ጸረ ኢትዮጵያዊ ክንፈ ገብረ መድህን እና ባንዳዎቹ ክፍሌ ወዳጆ፡ እንድሪያስ እሸቴና ፋሲል ናሆም ወዘተ አይነቶቹ ጋር ያስታውሶታል።
Professor bergit ye janhoy zemen ayegegnem.gin “Kehager Alsededm “yalut..Lijochwon bemulu American likew yele ende? Demo erswom selareju new meseded yemayfelgut enji hagerwon wedew aydelem.sew be ergina zemen sewash des aylem. Ethiopia west weshtam hizb beztoal.