የህዝብን ቁጣ በሃይል መግታት እንደማይቻል ከታሪክ መማር አስተዋይነት ነዉ!!! (ፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን )

የህዝብን ቁጣ በሃይል መግታት እንደማይቻል ከታሪክ መማር አስተዋይነት ነዉ!!!

ፈርስት ሂጅራ በአሜሪካ ከዛሬ ሃያ አመታት በፊት ሲመሰረት አንግቦ ከተነሳባቸው አላማዎች አንዱ ለኢትዮዽያ ሙስሊሞችና ብሎም ለመላው ኢትዮዽያዊ ወገናችን አጋር ለመሆንና በጎ ለመስራትም ነዉ። ታዲያ በነዚህ ባሳለፍናቸዉ አመታት በተለይ ከ1991 ለዉጥ ወዲህ እንደማንኛዉም ኢትዮዾያዊ ያገራችን የተስፋ ብርሃን ጭላንጭል እየታየን ሲጠፋ ከዛሬ ነገ ይሻላል በሚል ቆይተን ነበር። ነገር ግን አገሪቱን እያስተዳደረ ያለዉ አምባገነናዊ ስርአት ከአራት ዐመታት ወዲህ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ላያ ይህ ነዉ የማይባል ህገወጥ የግፍ እርምጃ በመውሰድና በገሃድ በእምነቱ ጣልቃ በመግባት ሙስሊሙ በአገሩ ላይ ያለዉን ተስፋ ድቅድቅ ባለ ጨለማ ዉስጥ ጥሎታል።

በአገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ውስብስብ ሰው ሰራሽ ችግሮች እንዳሉ ይታወቃል። ከዛሬ አራት አመታት በፊት ሙስሊሙ ህብረተሰብ ለመብቱ ሲል የጀመረዉን ሰላማዊ እንቅስቃሴን አስከትሎ በአምባ ገነኖች የደረሰበት ጭፍጨፋና መከራ ዛሬ በሌላዉ ወገን ላይ በአስከፊ ሁኔታ እየደረሰ ነዉ። በተለይ በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያና በአማራ ክልል ያለው ሁኔታ እጅግ አስደንጋጭ እና አሳማሚ ደረጃ ላይ ደርሷል። አማራ እና ኦሮሞ ወገኖቻችን በአሰቃቂ ሁኔታ በመንግስት ሀይሎች እየተገደሉ ነው።

ጭፍጨፋው በቀላሉ የሚገመት አይደለም። መጠነ ሰፊና በቁጥር በውል የማይታወቁ ወገኖች ህይወታቸውን እንደዋዛ ሰውተዋል። ደማቸው ፈሷል። አሁንም የማፈንና የመግደል ዘመቻው በሰፊው እንደቀጠለ ነው። ለጀግናዉ የኦሮሞና የአማራ ወገኖቻችን ያለንን አድናቆት ከልብ በመነጨ ምስጋና ለመግለፅ እንወዳለን። በተለይ ባደረጉትና በሚያደርጉት ትእይንተ ህዝብ ላይ የሙስሊሙን የፍትሕ ጥያቄዎችን በማንሳታቸዉ ምን ጊዜም ዉለታችሁን እንደማንረሳ እናሳዉቃለን።

የፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን አሁንም ቢሆን ከዚህ በፊት በአምባ ገነኑ የወያኔ ሰራዊት የተገደሉትን ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነት እና ፍትሕ ሲሉ ህይወታቸውን የሰጡትን ሰማዕታት ሁልጊዜም በጸሎት (በዱዓዕ) እናስታውሳቸዋለን። ለሞቱለት ዓላማም ያለጥርጥር ፈለጋቸውን እንከተላለን። ለሙታን ቤተ ሰቦችም ትዕግስትን እና መጽናናትን እንመኛለን።

አሁን ባለው አስከፊ አምባገነናዊ አገዛዝ ብዙ ወገኖቻችን ማለትም የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች፤ ጋዜጠኞች፤ ጦማሪዎች፤ የሙስሊሙ ህዝብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች፤ የሀይማኖት መሪዎች፤ ምሁራን እና የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች እስካሁን ድረስ በእስር ቤት እየተሰቃዩ ነው። ምንም ወንጀል ያልሰሩ በአገሪቱ የሰፈነውን ጨቋኝ መንግስት በመቃወማቸውና ለሰላምና ለፍትሕ በመጮሀቸው ብቻ የታሰሩት የሀገሪቱ ውድ ልጆች በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቁ ድርጅታችን በጥብቅ ይጠይቃል።
የህወሀት መንግስት የሰይጣን ጥይቱን ያነጣጠረው በሁሉም ሀይማኖቶች፤ ብሄረስቦች፤ ክልሎች፤ ባጠቃላይ በሁሉም ወገኖቻችን ላይ በመሆኑ በኢትዮዽያ ላይ ፍትሕን ለማስፈር በሚደረገዉ ትግል የዜጎች ተሳትፎ ስለሚጠይቅ ክፍፍልን በመተው ድል እንድንቀዳጅ አብረን በጋራ እንድንታገል እናመላክታለን።

ለዚህ ሁሉ ግፍ ያለጥርጥር የወያኔ መንግስት አገዛዝ ተጠያቂ ነው። የስርዓቱ መሳሪያ የሆነው የታጠቀው ሰራዊት አቅፎና ተንከባክቦ ያሳደገውን ኢትዮጵያዊ ወንድሙን እህቱን አባቱን እና እናቱን በአሰቃቂ ሁኔታ ከመግደል እንዲቆጠብ ከዚያም አልፎ መንግስትን ሳይሆን ህዝብን የማገልገል ሀላፊነት እንዳለበት አጥብቀን እንመክራለን።
ፍትሕ ለሁሉም ዜጎች!

ትግላችን ባንድነት እስከድል በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!!

አሏህ አክበር !!!

ፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን
ዋሽንግተን ዲሲ

6 Comments on “የህዝብን ቁጣ በሃይል መግታት እንደማይቻል ከታሪክ መማር አስተዋይነት ነዉ!!! (ፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን )”

  1. Thank you the terrorist Jihaddist
    Dimtsachin Yesema . No fertile ground
    for slaughtering Christians .
    Go and preach this in Aleppo Syria where
    your brothers and enjoing .

  2. A comprehended all round struggle is needed in the country this tyrant mafia gang group undermined the Muslim umma, if people asks their right in a Muslim majority location like Arisi, Bale etc accuses them as terrorist by ignoring the common question of oromiya. After this on wards it should be stop to undermine Muslims & looking them us a second citizens enough is enough!

  3. Ayalkbet
    What are saying by the kings and derg time moslims are better.so polotika and religion are different.

  4. First Hijra deseerves appreciation for pointing out the abuse of human rights by the current oppressive regime in Ethiopia.

    However, First Hijra itself needs to apologize to the Ethiopian people. It will always be remembered that a few years ago, First Hijra had written a letter to the then leader of the Ethiopian regime, Meles Zenawi, claiming that Ethiopia was 65% Muslim and that certain changes be made in the country to reflect the religious allegation. First Hijra’s claim is based on a dangerous line of thought, religious fundamentalism, that would set the country on another highly dangerous course of action.

    First Hijra’s recent statements are, therefore, merely a case of presenting itself as “the enemy of my enemy” to the Ethiopian people unless it declares an apology and a statement rejecting its previous wrong claims.

  5. እናንተም ይሄ የዘር የሀይማኖት ምናምን ነጻነት ድምጻችን ይሰማ የምትሉትነ ተረት አቁሙ ቀደም ብላችሁ መንግስታችንን አትንኩ ስትሉን ነበር ዛሬ ተገልብጣችሁ ለራሳችሁ የተለያየ ስም እይሰጣችሁ ትግሉ መልክ እንዳይዝ ታደርጉታላችሁ። አንድነት እና የግለሰብ ነጻነት የሁሉም ጥያቄ መልስ መሆን አለበት። ሀጂ ነጂብ ጁዋርን ጠርተዉ ሰዉ እረዱ ሲል አላህ አኩበር ትላላችሁ ሀጂ ነጂብ ኢሳት መስኮት ላይ ደግሞ ይሄንን አጥፈዉ ሌላ ሌላ ይናገራሉ ስለዚህ፡ተረቱን፡ተዉትና የአባቶቻችሁን፡ስርአት፡አክብሩ፡ከኢትዮጵያዊነት መስፈርት አትጉደሉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*