“የሐጎስ-ቶላ-እርገጤ” ጨዋታ (አፈንዲ ሙተቂ)

“የሐጎስ-ቶላ-እርገጤ” ጨዋታ
(አፈንዲ ሙተቂ)
—-
ከአሁኑ ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር ባልተገናኘ ሁኔታ የሐጎስ፣ የቶላ እና የእርገጤ ጨዋታን ወደ ሶሻል ሚዲያ ያመጡ ሰዎች ዓላማቸው ምን እንደሆነ አልገባንም፡፡ እኛ እንደምናውቀው በኢትዮጵያ ውስጥ በጣም ተመችቶት የሚኖር የትኛውም ህዝብ የለም፡፡ በደሉ፣ ድህነቱ፣ ረሃቡ፣ ጭቆናው በሁሉም ክልል ያለ ነው፡፡ ትግራይም ሆነ ኦሮሞ፣ አማራም ሆነ ሶማሊ በበደል ውቅያኖስ ውስጥ እየዋኙ ነው፡፡ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሐት) ሀገሪቱን እንዳሻው እየፈነጨባት ነው ስለተባለ ብቻ መላው የትግራይ ህዝብ ሌሎችን አስገብሮ በባርነት እያሳረሳቸው ማለት ነው…. ? ይህ ሃላፊነት የጎደለው የእብድ ፖለቲካ ነው፡፡
የኦሮሞ ህዝብ “እምቢኝ! አልቀበለውም” በማለት ውድቅ ያደረገው ማስተር ፕላን በትግራይ ህዝብ ሙሉ ስምምነትና እውቅና እንዳልወጣለት ያውቃል፡፡ የአማራ ህዝብም በክልሉ ያለው በደል አንገሽግሾት ለተቃውሞ ሲወጣ የበደሉ ምንጭ የትግራይ ህዝብ እንዳልሆነ ያውቃል፡፡ ሌሎች ህዝቦችም እያሰሙት ያለው ድምጽ “በመልካም አስተዳደር እጦት ተሰቃየን፣ ፍትሕና ነጻነት እንሻለን” የሚል እንጂ “ወያኔዎች አንገቴን ይዘው የትግራይ ህዝብ አሽከር አደረጉኝ” የሚል አይደለም፡፡ ጥቂቶች የራሳቸውን ፖለቲካ ከህዝብ ጥያቄ ጋር እየቀላቀሉ ባያቀያይሙን መልካም ነው፡፡
ይህ አንድን ህዝብ በጅምላ የመፈረጅ አካሄድ በምርጫ 97 ማግስት ተከስቶ ነበር፡፡ በተለይ ከፊውዳል አስተሳሰብ ያልተላቀቁ አዛውንት ፖለቲከኞችና ደቀ-መዛሙርቶቻቸው በልዩ ልዩ ዌብሳይቶች ላይ “ትግሬዎችን የምንጥልበት ጊዜ ስለደረሰ በአንድነት እንነሳ” እያሉ በአንዱ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ መርዘኛ ቅስቀሳ ሲያጣጡፉ እንደነበረ እናስታውሳለን፡፡ ታዲያ ያ አደገኛ ቅሰቀሳ ወያኔን ከመነቅነቅ ይልቅ ብዙዎች ያላሰቡትን ቀውስ አስከትሎ ነው ያለፈው፡፡ ለምሳሌ ለወትሮው ከኢህአዴግ መንግሥት ጋር እሳትና ጭድ መሆናቸውን የምናውቅላቸው የትግራይ ተወላጅ ፖለቲከኞች በዚያ ቅሰቀሳ ልባቸው በመሰበሩ ከተቃውሞ ፖለቲካው ተገልለዋል፡፡ በዚህ ረገድ በቀዳሚነት የሚታወሱት አቶ አብረሃም ያየህ ናቸው፡፡ አቶ አብረሃም በወቅቱ የተናገሩት ትልቅ አባባል ነበረ፡፡ ይኸውም “መለስ ዜናዊንና ከዓለማዊ ህይወት ተገልለው በደብረ ዳሞ ገዳም የሚኖሩትን የትግራይ መነኮሳትን በአንድ ሚዛን ላይ የሚያስቀምጥ የተቃውሞ ፖለቲካ ነገ እኔን ወንጀለኛ ላለማድረጉ ምንም ዋስትና የለኝም” የሚል ነው፡፡
ያ በ1997 የታየው አሳዛኝ ክስተት በፌስቡክ ላይም ተደግሞ አይቼዋለሁ፡፡ አርአያ ተስፋማሪያምን ታውቁታላችሁ አይደለም…. ? አዎን! አርኣያ ማለት “እየሩሳሌም አርኣያ” በሚለው ዝነኛ የብዕር ስም የምናውቀው ተወዳጅ ጋዜጠኛ ነው፡፡ አርኣያ በተለይ የሚታወሰው “ኢትኦጵ” በምትባለው ሳምንታዊ ጋዜጣ ላይ “ከህወሓት መንደር ከቃረምኩት” በሚል ርዕስ ስር ሲጽፋቸው በነበሩት ተከታታይ ጽሑፎች ነው፡፡ አርኣያ ጽሑፎቹን መጻፍ የጀመረው በ1994 መጨረሻ ላይ ይመስለኛል፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ጋዜጣዋ እስከተዘጋችበት 1998 መጀመሪያ ድረስ በዚህ ርዕስ ሲጽፍ ነበር፡፡
አርኣያ በጽሑፉ ከውስጠ-አዋቂዎች የተገኙ ሚስጢሮችን ነበር የሚዘረዝረው፡፡ በህዝቡ ዘንድ መነጋገሪያ ለመሆን የበቁ በርካታ ሚስጢሮችን ለመጀመሪያ ለህዝብ ይፋ ያደረጋቸው አርኣያ ነበር (ለምሳሌ አቶ መለስ ዜናዊ በ1996 አጋማሽ ላይ በተካሄደው የኢህአዴግ ም/ቤት ግምገማ ላይ አቶ አርከበ እቁባይን “ሰባት ድስት ጥዳ ሰባቱንም በአንድ ጊዜ ለማማሰል የምትሞክር ባልቴት ትመስላለህ” ማለታቸውን ይፋ ያደረገው አርኣያ ተስፋማሪያም ነበር)፡፡ አርኣያ ሚስጢሮችን ሲነግረን መንገዱ ሁሉ ቀና አልነበረም፡፡ ብዙ ማስፈራሪያዎች ደርሰውታል፡፡ በ1996 ሚያዚያ ወር ላይ ደግሞ ያልታወቁ አካላት ከፍተኛ ድብደባ ፈጽመውበት በደም የራሰ አካሉን ቀበና ድልድይ ላይ ጥለዋል (ነገሮችን እንዲህ የማስታውሰው “ኢትኦጵ” በቋሚነት ከማነባቸው ጋዜጦች አንዷ ስለነበረች ነው)፡፡
እንግዲህ እነዚያን የኢህአዴግና የህወሓት ሚስጢሮች በየሳምንቱ ሲያጫውተን የነበረው አርኣያ ተስፋማሪያም የትግራይ ተወላጅ ነው፡፡ አርኣያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገረ አሜሪካ የሚኖር ቢሆንም አሁንም በዌብሳይቶች አማካኝነት ልዩ ልዩ መጣጥፎችን እየጻፈልን ነው፡፡ ይሁን እንጂ በሶሻል ሚዲያ ላይ በሚያነባቸው መላ-ቅጥ የሌላቸው ጽሑፎች ስሜቱ እንደተጎዳ እያየን ነው፡፡ በተለይም አምና መሳፍንት ባዘዘው እና ጓደኞቹ “እነዚህ ተባዮች፣ ተባያቸውን አራገፉብን” በሚሉ ጥሬ ቃላት ሲጽፏቸው በነበሩት መርዘኛ ጽሑፎች የተነሳ ከመሳፍንት ጋር የቃላት ጦርነት ገብቶ እንደነበረ እናስታውሳለን፡፡ አሁን በተነሳው አዋራም ሞራሉና ስሜቱ እንደተጎዳ አይተናል፡፡ እና እንዲህ ዓይነቱ የሞራል ተጎጂ ነገ በተቃውሞ ፖለቲካው ተስፋ ቆርጦ የህወሓት ደጋፊ ሆኖ ብቅ ቢል “ድሮውንም ትግራዮች የዘራችሁን ነገር አትተውትም” ልንለው ነው….? የትላንት ግብሩ በዜሮ ተባዝቶለት “ድሮውንም ለስለላ ስራ ተልከህ ነው” ሊባል ነው…?. በጭራሽ…! እርሱን የወለደውን የትግራይ ህዝብ የማያከብር መርዘኛ ጸሐፊ በርሱ ላይ ጣቱን የሚቀስርበት የሞራል መሰረት የለም፡፡
ሰርካለም ፋሲል የታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባለቤት ናት፡፡ እርሷና ባለቤቷ በጋራ በመሰረቱት የፕሬስ ድርጅት አማካኝነት ምኒልክ፣ ሳተናው እና አስኳል የተሰኙ ጋዜጦችን በኤዲተርነት ሲያዘጋጁ ነበር፡፡ ሁለቱም በምርጫ 97 ጦስ አንድ ላይ ታስረዋል፡፡ ሰርካለም በእስር ቤት እያለች የመጀመሪያ ልጇን ተገላግላለች፡፡ ከእስር ቤት ከወጣች በኋላ ደግሞ ተሰዳለች፡፡ እዚያ ሆና ባለቤቷ እንዲፈታላት ድምጿን በማሰማት ላይ ትገኛለች፡፡ ያቺ ሁለት ዓመታትን በእስር ቤት ያሳለፈችውና ባሏን በእስር የተቀማችው ሰርካለም ፋሲልም በብሄሯ የትግራይ ተወላጅ ናት፡፡ የትግራይ ተወላጅ የሆነው ሁሉ የስርዓቱ ተጠቃሚ ነው የሚባል ከሆነ ሰርካለምንና ህወሐትን የሚያያይዛቸው የጥቅም ትስስር የትኛው ነው?… “ሐጎስ-ቶላ-አዝብጤ” በሚለው አክሲስ ውስጥ ሰርካለምም ትገባለች ማለት ነውን….?
አሉላ አባነጋ፣ ባሻይ አውኣሎም፣ ሃይሉ አርኣያ፣ ግደይ ገብረዋህድ፣ ብርሃነ እያሱ፣ ረዘነ ረዳኢ፣ ገላውዴዎስ አርኣያ፣ ስብሐት ገብረ እግዚአብሄር፣ ምሩጽ ይፍጠር፣ ወርቅነሽ ኪዳኔ፣ አቤሰሎም ይህደጎ፣ ገብረ መድኅን ሃይሌ፣ ኪሮስ ዓለማየሁ፣ ነጋድራስ ገብረ-ህይወት ባይከዳኝ፣ እነዚህ ሁሉ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ አንጸባራቂ ስፍራ ያላቸው የትግራይ ተወላጆች ናቸው፡፡ ሁሉንም በጅምላ መወረፍ ከተጀመረ እነዚህ በሙሉ ታሪካቸው ይሰረዛል ማለት ነው፡፡ ህዝብን በጅምላ መፈረጅ ከመጣ ታሪክና አንትሮፖሎጂ ተሳስተዋል ማለት ነው፡፡
እስቲ በአካባቢያችን የምናውቃቸውን ምንዱባን የትግራይ ተወላጆች እናስታውስ፡፡ በዘመነ ደርግ በከተማችን የሚኖረውና ወዝ-አደር ሆኖ ለሰዎች ሸክም ያመላልስ የነበረው የማነ የሚባል ሰውዬ ዛሬም ቢሆን በዚሁ ስራ ነው የሚተዳደረው፡፡ ከገለምሶው የካምቦ ተራራ ስር አንዲት አነስተኛ ቤት ቀልሰው የሚኖሩት አቶ ገብረአምላክ አሁንም ምንም ሳያልፍላቸው በድህነት ኑሮ ህይወታቸውን እየገፉት ነው፡፡ እነዚህ ግለሰቦች የትግራይ ተወላጆች ቢሆኑም ከህወሓትና ከአመራሩ ያገኙት የተለየ ጥቅም የለም፡፡ እነዚህን ድኩማንና የሕወሓት የነፍስ አባት ናቸው የሚባሉትን ኦቦይ ስብሐት ነጋን በአንድ መነጽር ማየት ይቻላል?
ለስርዓቱ ጉድለቶችና ጥፋቶች የትግራይ ተወላጅ በሙሉ ተጠያቂ የሚሆንበት ቀመር የለም፡፡ በተመሳሳይ መልኩም ሁሉም የትግራይ ተወላጅ የስርዓቱ ተጠቃሚ ነው” የሚል ፍረጃ መዘብዘብ ውሃ አይቋጥርም፡፡ ስለዚህ ጨቅላነት የሚያጠቃቸው አክቲቪስት ነን ተብዬዎች ያልታረሙ እንኮላዎችን በፌስቡክ ላይ እየደፉ ጨዋ ጓደኞቻችንን ባያስከፉብን ይመረጣል፡፡
በሌላ በኩል አንዳንድ ካድሬዎች ይህንን ጨዋታ እያራገቡ የትግራይ ህዝብን ማስፈራራታቸውን መተው አለባቸው፡፡ እንዲህ ዓይነት ፍረጃ ከህዝብ እንዳልመጣ እየታወቀ “የአሁኑን ተቃውሞ የቀሰቀሱት እነዚህ ዘረኞች ናቸው” እያሉ መለፍለፍ በህዝብ መብትና ጥቅም መቀለድ ነው፡፡ ተቃውሞውን የሚያካሄደውና በዚህ ሳቢያም መስዋእትነት እየከፈለ የሚገኘው ብዙሃኑ ህዝብ ነው፡፡ የህዝብ ጥያቄም በግልጽ ይታወቃል፡፡ ስለዚህ ውጥረቱ እንዲረግብ ከተፈለገ ያልሆነውን አሉ እያሉ ማስወራት ሊቆም ይገባል፡፡
ባጠቃላይ ሲታይ ህወሓት የሚባለው ድርጅት እድሜው አርባ ዓመት ብቻ ነው፡፡ ኦሮሞ፣ ትግራይ፣ አማራ፣ አፋር፣ ሶማሊ፣ ስልጢ፣ ጉራጌ፣ ወዘተ… የሚባሉት ህዝቦቻችን ግን ለብዙ ክፍለ ዘመናት እዚሁ ምድር ላይ ነበሩ፡፡ አብረው ኖረዋል፡፡ ተዋልደዋል፣ ተዛምደዋል፡፡ የተለያዩ መንግሥታት በተለያዩ ዘመናት በየተራ እየተነሱ ቢወድቁም ህዝቦቻችን አብረው እየኖሩ ነው፡፡ ነገም አብረው ይኖራሉ፡፡ መንግሥታት በስማቸው ቢምሉና ቢነግዱም እነርሱን ጠቅመዋል ማለት አይደለም፡፡ ስለዚህ ስርዓትና ህዝብን ማምታታት ተገቢ አይደለም፡፡
መንግሥታት ያልፋሉ፤ ህዝቦች ግን ይኖራሉ፤ እኛ ከህዝቦቻችን ጋር ነን፡፡

20 Comments on ““የሐጎስ-ቶላ-እርገጤ” ጨዋታ (አፈንዲ ሙተቂ)”

  1. I agree with you 100% and no need to repeat anything here.
    furthermore, people are expecting from the Tigreans to come forward and say “the spade a spade”.

  2. Thank you for sharing your humble heart Brother!!

    Like it is written in almost every religion and philosophical dicourse “don’t do unto others what you don’t want others to do unto you”

  3. Dear,you are right like Dr.Aregawi and others Tigraians ,Tsadkan and Abebe started to condem the The TPLF rule others also join this people as a bench mark when woyane in the name of Tigrai shed the blood of young oromo and Amhara on the street of Oromia Gonder Gojam. It’s good to differentiate the innocent from spy and supporter of Woyane. How ever spy, and the property of Nazi TPLF will continue to attack and destroy in any corner of the Republic.

  4. Negeru tikikile new abezgnawin yetekwamewoch saihon anitem satawikew
    ayikerim ke weynne endehum andand selam adefirashoch endalu metawek alebet.Be atekalai beahun seat hulum gazetgna, amidegna yehonebet
    gize selehone hulunim beand ain mayet ëna hodina jeriba mehone yelebinem.

  5. Ok Melkam gn ahunm chigru budnu alamaw yetgrien lemagnoch banda minstir madreg new ena pure tgrie negn yemil kewoyanie yirak! If he/ she is Ethiopian?

  6. በሳሉና አስተዋዪ አፈንድ በተወደደ ሰአተ ብቅ እልክ የምትሰጣቸው አስተያየት ከልቤ ያረካኛል፡፡በተለይም 1983/84ዓም ዘረኛው ወያኔ በገለምሶና አካባቢው የህዋትን ዘረኝነት በቅጢ ያልገባቸው እንደ ዲማ ነገዎና ተከታዮቻቸው አብሮ በኖረው አማራ ላይ የደረሰውን በደል እኔም አንተም የተመለከትነው ኦነግ የወያኔ ከፋፋይ ስርአት መሆኑን ሁላችንም የተመለከትከው ነው፡፡እኔም የገለምሶ ልጅ በመሆኔ ያ ችግር ትልቅ ነገር አስተምሮን ሲያልፍ ዳግም እነግ በዛ መንገድ የሚመጣ ይሆናል ብዬ አላስብም፡፡አብሮ ለዘመኔት የኖረን ህብረተሰብ ወደፊት አብሮ የሚኖርን ህብረተሰብ ግዜ አምጥቶ ከጣለብን ግዜም መጥቶ ከሚወስደው ጋር እኩል ማየት እንደ ሌለብን ነገን ማስብ እንድንችልና አርቆ ማስተዋልን እንዲሰጠን ይጠይቃል፡፡የህዝብ ጠላትን ከህብረተሰብ ጋር ነጥለን ማየትና የሁላችንም ጠላት የሆነውን ዘረኛና የለየለት ዘራፊ ሁላችንም በአንድ ላይ አይኖቻችንን ከፍተን በማየትና በማስተዋል ወያኔ ላይ ክንዳችንን ማንሳት አለብን፡፡ይብቃን በወኔ፡፡ወያኔ ሁሉ ትግሬ ፤ሁሉም ኦሮሞ ገላሳ ዲልቦና ሌንኞ ለታ አይደሉም፡፡ሁሉም ኦሮም ለአውሰይዱ፣ለጢርሶ ገደል፤ለበደኖ፣ለእንቁፍቱ ተጠያቂ አይደሉም፡፡በእነዚህ እኩይ ስራ ተሳታፊ አልነበረም፡፡፡አሁንም ሁላችንም በላያችን ላይ የተጣበቀውን መዠገር በአንድ ላይ ተባብረን ማስወገድ አለብን፡፡ተወደደም ተጠላ ወያኔ ከነእርግማኑና ክፋቱ የሚወገድበት ግዜ ቅርብ ነው፡፡ትውልድ ለዘላለም ይህች አለም እስክትጠፋ ድረስ ይኖራል፡፡ስለዚህ የትግራይ ህዝብ በየትም ያለህ ነገ ለታራክ ተወቃሽና ፍርድ ከመሆንህ በፊት ከወገንህ ጎን ለትግል ተነስ፡፡ነገን አስብ፡፡ቤተሰብህን አስብ ፡፡ ለልጆችህ ታሪክህን አስተምር፡፡፡ሀገርህን እምዬን አትርሳ፡የፍርድ ቀን አስብ፡፡አፈንዲ በርታ፡፡እኔም ገለምሶን አንተንም አልረሳምና፡፡ ሞት ለወያኔና ባሪያዎቺ

  7. Certainly, it is a terrible mistake to paint Woyanes with Tigres with the same brush in revenge.

    But one thing must be clear. Insulting the filthy, lice-infested Woyanes soldiers who invaded Ethiopia to partition it, divide it along any divisive line and completely deconstruct Ethiopia, should not be perceived as an affront to Tigres.
    The question of arguing that we should not raise a finger at Woyanes because ” not all Tigres benefited from TPLF’ occupation” is ludicrous.
    T
    The fact is Tigres represent only 1 Ethiopian in 20. However, as evidenced by the data on the ground all the 9 Sport Federation’s officials are zombie Tigres. Of the 65 Woyane’s so-called generals, 62 are Tigres, while their rightful representation should have just been 3 or 4.
    Why should any Tigre be offended if we say, these people have no shame culture.
    Nobody in his right frame of mind vilifies all Tigres for the crime of Woyanes. But we cannot in all honest deny that hundreds of thousands of Tigre elites, even those who have nothing to fear by way of Woyane retribution, have the courage to condemn TPLF. I dare say, many in fact wholeheartedly support it. Let us not pretend. Woyanes are enemies of Ethiopia. What many Tigreans fail to realize is that TPLF a greater enemy to the people it claims to represent.The proof of the pudding is in the eating.

    Let Tigre elites show their revulsion. Only 16 manifested their solidarity with the rest of their compatriots. Every time Woyanes hold a meeting in any major American or European cities thousands converge. Let us not be hypocrites.
    If I were a Tigrean, who has the interest of my country at heart, I would gloss over the few silly remarks some dudes make in the heat of the moment.
    Enduring such minor inconveniences is a patriotic duty some Tigreans should be able to bear with equanimity.
    Of the hundreds and thousands of Ethiopians who are genuinely battling the enemy regime tirelessly, only 3 noble men of Tigrean origin come to mind. They are anamely, the Australia-based Gebre Medhin Araya, Getachew Redda, (the brilliant and conscientious patriot based in the USA), and the brave home-based Dr. Hailu Araya.

  8. Hi Dr.Aregawi sometime I find you in a situation of uncertain. When you were
    at the top of power in TPLF you believed Amhara people specially the people of Gonder is number one enemy of Tigre. After you left the tplf group I have never and ever heard you repentance of what you did and planted the hatred and bitterness against the amhara people of Gonder.
    Dr. Aregawi I HAVE NEVER HEARD YOU APOLOGIZING the people of Ethiopia for what you did against Ethiopia.
    I appreciate for your struggle and recently what you suggested for the formation of transitional government composed of all civil society and communities.
    TPLF is an Enemy ,Once an enemy is always Enemy,the only way to peace is an absolute removal of TPLF FROM Tigrie province and from Ethiopia.
    iF tplf is removed the people of Ethiopia fr.north to south and from eas to west naturally will come together and peace will prevail.

  9. Yep, truly humble heart
    heart felt thankfulness bro. we expect more from u that would make us love one another

  10. Ok we all agree, but where are the tegreans when Oromo,Amhara, Gambela and other people killed every day, instead of sitting quite, why they don’t come out and say no to their cousins who slaughter Ethiopians, when you see teagrens holding all the power, economy, security and so on what are you expecting from other people who is suffering in their own country and birthplace, when you see the tegreans in every police each offices, airlines,business, sport federation and news agencies like TVs, radios and news papers. I don’t know your answer but you can not deny the truth what they doing. Yes we were waiting all this time hoping one day they feel the suffering of others as Ethiopians, and this was the right time to be one with others Ethiopians, but they send agazies to kill the son and doughter of Oromo’s,Amhara’s, Gambela’s and so on. What do you expect ? A kiss !!!

  11. The tigrians have the right to not protest do you think all amhara oromo gurage somalia afar….are protesting from 100,000,000 population how much is protesting at this time. you don’t have to blame someone because not supporting you. I don’t like politics so I don’t want to say anything that doesn’t mean I support EPRDF. you gain when you show love and respect to others.

  12. Affendi Muteki! you are a liar. Can you name any one from the kinijit leaders who said, during the the 2005(1997EC) election, to target Tigrayans? They were saying Weyane not Tigrayan. You are repeating what the Woyane and Meles were telling the people during that time. I do not know the reason why this web site is allowing liars to post such articles.

  13. ወያኔ ኦሮሞንና አማራን መግደል ማባረር ህገ መንግስታዊ መብት አለው! አንድ የትግራይ የወያኔ አባል በስብሰባ ላይ የተናገረው ትክክል እየገደሉን ነው እስከ መቼ?
    ቆሬ

  14. Tiruneh, esti yichin gitim simat be 97 yetetsafech nech. “tigre wede mekelle eka wede kebele” lelam lingerih eski “kefabrica endeweta samuna lemin hulachihum tplf tilalachu?” mesfin w/mariam mekelle 97. “wedemetabet yimelesal” yekinijit self lay parlama yeneberu yekinijit kefitegna amerar. tadiya yewashew manew? tsehafiw weyis ante? kelay yetsafkulih esat atiwawasu, buna atitetu abrachu yetebalewin tiche new

  15. It is simply nonsense. What ever you do you cann’t push the Tigres to join the anti-government movement. It is you and the likes who pour cold water on the struggle. TPLF is loading you to locomote its interests. All Tigres have no differences in the case of the current situation in Ethiopia. They all need Woyane to continue on power oppressing and looting.

  16. The article seems interesting. The writer seems blame the victims. Frankly speaking who is a master mind Ethnic based politics the answer is easy Weyna in the name Tigrynes. OK why the tigrnay show the courage to protest this the last 25 years like Oromo, Amahar and other ethnics did . In short, the writer miss a big picture!

  17. አንኳር ሀሳቡ የፓለቲካውን መዘውር ለጨበጡት የዚህ ባንክና ታንክ ደረቅ ማስል አለ በሚሉ ጥቂት ግለሰቦች የተፈጠረውን በጥብጥ፣በዝብዝ ገዝ ስርአት ለማራቅ ለማረቅ ነው።ይቻላል።ሁሉም ጊዜ በተለይ እንደ አፍሪካ አይነት አሁግር በደም የሚንቆረቆር የሚመነዘር ለውጥ ከሚደረግበት መንግስት የእድሜውን ርዝመት በህዝብ ብሶትና ምሬት በሚያይበት መነፅር አይቀሬው ተፋጅ በሚንጠፈጠፍ ደም ይቀርባል። አንድ እና አንድ ተጠያቂ ስርአቱ ነው።ህዝብ ያነቀረውን ስርአት ህዝብ ያመረረበት ከግለሰቦች የእንካ ሰላምቲያ በላይ የገፋ ምክንያት ነው።ሰው ሞተ።ህይወት ተቀጠፈበት።የሚገባኝ የመንግስት ጨርቁን ከመጣሉ በፊት ትኩረቱ የግለሰቦች ሳይሆን ከህዝብ ውስጥ ይህን ያን ሳይሆን ስርአቱ በዋነኝነት የገመደው እያደረገ ያለው አደጋ የፍጨው ግጨው ማኪያቬሊ ጉዳይ አክብዶ ማጋለጥ ነው።እስቲ ስርአት ይፈጠር የመስከንና የመቻቻል ጉልበት ይፈጠር ከሚያባላን ጨበሬ እምነት አዲስ ሰው ሊቀረፅ ከማይችልበት አስተሳሰብ እንውጣ። እስኪ ጨፌው ላይ ሰላማችን እና ሳቃችን ደምቆ ይታይ።በፍስሀ እናሸብሽብ።ስርአቱ በየትኛውም መልኩ ቋፍ ላይ ያለ ይበልጡንም መቀበሪያውን በራሱ እያዘጋጀ የመጨረሻውን ደቂቃ እየጠበቀ ነው።ትክክል ያልሆነው ተራውን ዜጋ አንድ ሙቀጫ በስመ ገዢ መውቀጥ ስህተት ነው።በጣም ስህተት።ጥያቄም አያስነሳ።ትልቁ ስእል ግን መገለፅ መገለብ ያለበት እንዲህ ጧት ማታ ዜጋ በአረር ሲታጨድ የዚህን እኩይ ተግባር ረግጦ ገልፆ ማሳየት ማጋለጥ ነው።ይህ ከዚሁ ከሰውነት ተፈጥሯዊ የማይገሰስ መግለፅ በህይወት መኖር መሰረታዊ ነገር ነው። አቻ የለውም።ሰላማችን ይብዛ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*