ኢዴፓ የምሰጠውን መግለጫ የወያኔ ሚዲያዎች ኣዛብተው እያቀለቡ ነው ሲል ኣለቃቀሰ።
ኢዴፓ የምሰጠውን መግለጫ የወያኔ ሚዲያዎች ኣዛብተው እያቀለቡ ነው ሲል ኣለቃቀሰ። በኦሮሚያና በአማራ ክልል የተፈጠሩ ተቃውሞና ግጭቶችን አስመልክቶ የሚሰጧቸውን መግለጫዎች የመንግስት ሚዲያዎች አዛብተው ለህዝብ እያቀረቡ ነው ሲል የተቸው ኢዴፓ፤ የፓርቲዎች የጋራ ም/ቤትም ከፓርቲው እውቅና ውጪ አቋሞችን በማንፀባረቅ ደንብ እየጣሰ ነው ብሏል፡፡
ፓርቲው ለአዲስ አድማስ በላከው ደብዳቤ እንዳመለከተው፤ ባለፈው ሳምንት ነሐሴ 6 በሀገሪቱ ወቅታዊ ችግሮች ዙሪያ ለመገናኛ ብዙኃን የሰጠውን መግለጫ ኢዜአ፣ ፋና፣ አዲስ ዘመን ጋዜጣና የአማራ ብሄራዊ ክልል ቴሌቪዥን ይዘቱን አዛብተው በማቅረብ፣ ህዝብ ስለ ፓርቲው ያለው አቋም እንዲናጋ ማድረጋቸውን ጠቁሞ፤ የሚዲያ ተቋማቱ አሰራራቸውን እንዲፈትሹና እንዲያስተካክሉ አሳስቧል፡፡
በእለቱ ኢዴፓ በኦሮሚያና በአማራ ክልል የተፈጠሩ ተቃውሞና ግጭቶች፣ በውይይት ሰላማዊ መፍትሄ ማግኘት አለባቸው የሚል አቋም ማንፀባረቁን የጠቆሙት የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ወንድወሰን ተሾመ፤ የተጠቀሱት የመገናኛ ብዙኃን ግን “ፓርቲው ህገ መንግስታዊ ስርአቱን በኃይል ለመናድ የሚደረግ ጥረት ተቀባይነት የለውም” ብሏል በማለት በመግለጫው ላይ ፈፅሞ ያልተጠቀሰ ዘገባ አስተላልፈዋል ሲሉ ወቅሰዋል፡፡
ሰንደቅ አላማን በተመለከተም ኢዴፓ ሰልፈኞቹ የያዙትን ሰንደቅ አላማ እንዳወገዘ ተደርጎ በዘገባዎቹ ቀርቧል ያሉት አቶ ወንድወሰን፤ ፓርቲያችን የሰንደቅ አላማ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን በህገ መንግስቱም መሻሻል ያለባቸው አንቀፆች አሉ ብሎ ያምናል፤ ሰንደቅ አላማውም ለህዝብ ምርጫ መተው ነው ያለበት በማለት የኢዴፓን አቋም ገልፀዋል፡፡ በሌላ በኩል ፓርቲው አባል የሆነበት የፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ባለፈው ማክሰኞ ነሐሴ 10 በጠራው አስቸኳይ ስብሰባ፤ በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በተለይም በኦሮሚያና በአማራ ክልል ያለውን ሁኔታ በተመለከተ የወሰደው አቋም ኢዴፓ ልዩነት ያንፀባረቀበት እንደነበር ተመሳሳይ አቋም እንደያዘ ተደርጎ መዘገቡ የም/ቤቱን ደንብ የጣሰ ነው ብሏል። ም/ቤቱ ይህን በ3 ወር ጊዜ ውስጥ የማያስተካክል ከሆነ ኢዴፓ ከም/ቤቱ እንደሚወጣ ለአዲስ አድማስ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡
ኢዴፓ ገባም ወጣም ምንም ለውጥ አያመጣም። የተቃዋሚ ፓርቲ ነኝ ብሎ ወያኔን ሲሞግት አላየነውም። የያዘው አቋም ደግሞ ወያኔንም ላለማስቀየምና ተቃዋሚ ነኝ ለማለትም በጣም መንሽራተት የበዛበት ወላዋይነት ይታይበታል። ወይ አቋሙን አጠንክሮ ይታገል ወይንም አስታራቂ ሽማግሌ ነኝ ብሎ ተቃዋሚነቱን ይተው። ሚናውን ይለይ።
ኢዴፓ ምንም የማያጠራጥር በተቃዋሚ ስም የወያኔ ቅልብ ነው።ተጃጅላችሁ ለማሞኘት አታለቃቅሱ።የፉገራ ዘመን እያለቀበት ነው።መግለጫ ገለመሌ እርሱት።ወያኔ ስር ተንበርክካችሁ ፍርፋሪ ልቀሙ።ሆዳም ፖለቲከኛ ሊሆን አይችልም!!!ከሀዲ አፉን እያጣፈጠ በህዝብ የመቀለጃ ዘመን መዝጊያው የራቀ አይደለም።
ይሄ ነው የኢትዮጲያ ዴሞክራቲክ ፓርቲ?በህዝብ ላይ አትቀልዱ
አይ ኢዴፖ! ማን ሊስምሽ ታሞጠሙጫለሽ ያገሬ ሰው!!
No wonder edepa is amharic speaking weyane party
አይ እንዴ! የፈለገውን ይሁን ግን ያላልኩትን አሉብኝ ካለ በቃ ሰምተናል ። ጥሩ ሶስት ወር ሰጠ አራዳው ውዳዘነበለበት ለማዘንበል።ይች ናት ጨዋታ አሉ ዘፋኙ ! ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ ላይ አይወጣም። ኧረ ሶስት እግር ቢኖርም አሁንም ሁለት ዛፍ ላይ አይወጣም። ሶስተኛ ብሎ አማራጭ ካለ አድርባይነት ብቻ ነው። ለይ ! ዛሬ!!!
አይ እንዴ! የፈለገውን ይሁን ግን ያላልኩትን አሉብኝ ካለ በቃ ሰምተናል ። ጥሩ ሶስት ወር ሰጠ አራዳው ውዳዘነበለበት ለማዘንበል።ይች ናት ጨዋታ አሉ ዘፋኙ ! ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ ላይ አይወጣም። ኧረ ሶስት እግር ቢኖርም አሁንም ሁለት ዛፍ ላይ አይወጣም። ሶስተኛ ብሎ አማራጭ ካለ አድርባይነት ብቻ ነው። ለይ ! ዛሬ!!!
ወያኔ ኦሮሞንና አማራን መግደል ማባረር ህገ መንግስታዊ መብት አለው! አንድ የትግራይ የወያኔ አባል በስብሰባ ላይ የተናገረው ትክክል እየገደሉን ነው እስከ መቼ?
ቆሬ