በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ለተቀሰቀሱ ተቃውሞዎችና ውጥረቶች የአለም አብያተ ክርስቲያናት ም/ቤት ውይይት እንዲደረግ ጠየቀ

በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ለተቀሰቀሱ ተቃውሞዎችና ውጥረቶች የአለም አብያተ ክርስቲያናት ም/ቤት ውይይት እንዲደረግ ጠየቀ

የአለም አብያተ ክርስቲያናት ም/ቤት ውይይት እንዲደረግ ጠየቀ

የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ህገ-መንግስታዊ መብቶች ይከበሩ ብሏል

የአለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ባለፉት ሳምንታት በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ለተቀሰቀሱ ተቃውሞዎችና ውጥረቶች ምክንያት በሆኑ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እንዲያደርጉ ለኢትዮጵያ መንግስት፣ ለጸጥታ ሃይሎችና ለተቃዋሚዎች ጥሪ አቀረበ፡፡
በኢትዮጵያ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች በላኩልኝ መረጃ፣ ተቃውሞውን ተከትሎ በአገሪቱ የተፈጠረው ውጥረት አሁንም አለመርገቡንና በተቃዋሚዎችና በጸጥታ ሃይሎች መካከል የሚከሰቱ ግጭቶች እንደቀጠሉ መሆናቸውን ተገንዝቤያለሁ ብሏል – ምክር ቤቱ ትናንት ባወጣው መግለጫ፡፡ የፀጥታ ሃይሎች ባልታጠቁ ዜጎች ላይ ተመጣጣኝ ያልሆነ ሃይል እንዳይጠቀሙ የጠየቀው ምክር ቤቱ፣  ተቃዋሚዎችም ለግጭቱ መንስኤ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ከመንግስት ጋር ግልጽ ውይይት የሚደረግበትን መንገድ መሻት አለባቸው ብሏል፡፡
“በተቃውሞዎቹ ለህልፈተ ህይወት በተዳረጉት ዜጎች እንዲሁም በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በተቃዋሚዎች ላይ በተፈጸመው እስርና ድብደባ ማዘናችንን እንገልጻለን” ብለዋል፣ የምክር ቤቱ የአለማቀፍ ጉዳዮች ኮሚሽን ዳይሬክተር ፒተር ፕሮቭ፡፡
በጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሰብዓዊ መብቶች ፖሊሲና እርዳታ ኮሚሽነር ባረቤል ኮፍለር በበኩላቸው ባለፈው ረቡዕ ባወጡት መግለጫ፣ በአገሪቱ የተከሰቱት ግጭቶች በእጅጉ እንደሚያሳስቧቸው ጠቁመው፣ ሁሉም ወገኖች ከቀጣይ ግጭቶች እንዲታቀቡና በውይይት ችግሮችን በጋራ እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡
የአገሪቱ ህገ- መንግስት ለዜጎች ያጎናጸፋቸው ሃሳብን በነጻነት መግለጽና ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግን የመሳሰሉ መብቶች መከበር አለባቸው ያሉት ኮሚሽነሩ፤ የጸጥታ ሃይሎች በተቃዋሚዎች ላይ የወሰዷቸው እርምጃዎችም የተመጣጣኝነት መርህን መጣስ አልነበረባቸውም ብለዋል፡፡

7 Comments on “በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ለተቀሰቀሱ ተቃውሞዎችና ውጥረቶች የአለም አብያተ ክርስቲያናት ም/ቤት ውይይት እንዲደረግ ጠየቀ”

  1. ወሪኞች ህዝብ ካለቀ በኃላ ነው የሚባንኑት እግዚአብሄር ይፈርዳል።

  2. i am superior tegrea i will do what i want do i born to rule the ethiopian people are my slave i iwant kill them i have a wright i you oppose why don’t you fight the cowerd

  3. It is a stupid and belated gesture.
    1. Where was this church when thousands were being slaughtered at he behest of TPLF?

    2. Did it not know how an ethnocentric outfit representing 5% of the Ethiopian population is ruling the country virtually excluding 95% of the population?
    Is the World Council of Churches unaware that every noteworthy head of Ethiopia’s Orthodox church is from the minority Tigre ethnic group appointed by the Tigre state contravening the established church doctrine? Every parish, monastery is manned by politicized and Ignorant Tigre clerics.

    Is it not disingenuous to say all parties should avoid violence when it knows that violence is the prerogative of the terrorist state which gunned down over 700 unarmed demonstrators in the last couple of months alone?
    Does it not know that the minority regime of Godless heathens has killed several priests violently, imprisoned the entire leadership of Muslims who resisted interference in their religious affairs, desecrated the oldest monastery by converting it into a private sugar plantation?
    You are Cowards and agents of the powerful but morally bankrupt nations.

  4. ይህ መግለጫ የእኛን እስረኛውን አብያተ ክርስቲያን ቦታቸውን ያሳያል።

  5. we not to expect anything from anyone because they are not bearing our people but we have to face challenges.

  6. Hypocrats where have you been all this time when our people slaughtered like a chicken by this evil regime in every corner

  7. Who is the guy who wrote this: ” በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ለተቀሰቀሱ … ” ?

    1. The ” የአለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ” ?

    If so tell them to forget their divisive agenda !

    The retards should talk about: ” በኢትዮጵያ ለተቀሰቀሱ … ” !

    2. The author of the article ?

    If so expose the retard and tribalist with anti-Ethiopian agendas !

    We should kick their asses hard whenever tribalist Ethiopians and anti-Ethiopia foreigners address Ethiopians as member of this or that tribe.

    We should have zero tolerance for tribalist Ethiopians and divisive foreigners.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*