ሸገር ለምን አታምፅም? BefeQadu Z. Hailu

ሸገር ለምን አታምፅም?

BefeQadu Z. Hailu

ዛሬ ረፋዱ ላይ በመስቀል አደባባይ አለፍኩ። በርካታ የፌዴራል ፖሊስ መኪኖች እና መኮንኖች ቆመዋል። ለወትሮው በስፖርተኞች ውር-ውር ይደምቅ የነበረው ገጽታዋ ቆሌው ተገፎ ጭር ብላለች። ፖሊስ ከመቼውም የበለጠ ወደአደባባዩ በሚወስዱት መንገዶች ላይ በዝቶ ነበር። ቢያንስ ከአራት ኪሎ እስከ ቦሌ ይህን አይቻለሁ። ሌላው ቀርቶ ሰፈሬ መውጫ ላይ የሚቆሙት ሁለት ፖሊሶች ቁጥራቸው ወደ አምስት ማደጉን አስተውዬ ነበር። አዎ፣ ጥበቃው ከወትሮው የከረረ ነበር። ትላንት እና ከዚያ በፊት አፈሳ እንደነበርም ይታወቃል። አፈሳው በአካል የማውቀውን Sintayehu Chekolን ይጨምራል። ትላንት ቦሌ አካባቢ ፖሊስ ሰልፍ እንዳይወጡ ወጣቶችን ሲመክር አይቻለሁ። ማታ ላይ ወደቤቴ ስገባ በፖሊስ ከአላፊ አግዳሚው ጋር ተፈትሻለሁ። ነገር ግን ይህ ሁሉ እንደሚሆን ቀድሞ አይታወቅም ነበር? በሕወሓት/ኢሕአዴግ ባሕሪ እንኳን ጠሪው ያልታወቀ ሰልፍ፣ ፓርቲዎች “ዕውቅና ያገኙበት” ሰልፍ ሲደናቀፍ አላየንም? የሰልፍ ቦታዎችን በፖሊስ መውረር እና አስቀድሞ ተሰላፊዎችን ማፈን የነበረና የሚኖር የኢሕአዴግ ባሕሪ ነው። ስለዚህ ዛሬ (ነሐሴ 15/2008) የተጠራው ሰልፍ በፖሊስ ተደናቀፈ የሚለው ምክንያት ተቀባይነት የለውም። ባይሆን ሌላ ምክንያት እንፈልግ።

፩) መሬት ላይ የተሠራ ነገር የለም!

ጎንደር ላይ የወልቃይትን (specific) ጉዳይ ሲያስተባብሩ የነበሩ የኮሚቴ አባላት እና በዙሪያቸው ያሉ ሰዎች ነበሩ። ኦሮሚያ ላይ የማስተር ፕላኑን (አሁንም specific) ጉዳይ ሲያስተባብሩ የነበሩ የቄሮ አባላት እና ሌሎችም ነበሩ። አዲስ አበባ ላይ ሰልፍ ራሱ እንደተጠራ መጀመሪያ የሰማሁት ሐሙስ ማታ ነው። እሱም አጋጣሚ ኢሳት ላይ “ሰልፉን ለማደናቀፍ ኢሕአዴግ አፈና ጀምሯል” የሚል ዜና ሲታወጅ ነው የሰማሁት። በማግስቱ ቃሊቲ የታሰሩ ወዳጆቼን ልጠይቅ ስሔድ “የእሁዱ ሰልፍ እንዴት ነው?” አሉኝ። የሰማሁትን ነገርኳቸው። ከዚያ በኋላም በአብዛኛው የሰማሁት የሆኑ ሰዎች በዚሁ ፍርሓት እንደታሰሩ ነው። ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እዚህ ያሉ እና በአገዛዙ በጣም የተበሳጩ ጥቂት፣ በጣም ጥቂት ሰዎች ከመጻፋቸው በቀር ሌሎቹ በሐሰተኛ ሥም የሚጽፉ ወይም በውጭ አገር የሚኖሩ ናቸው ዜናውን ያስተጋቡት። በኔ አተያይ፣ በሐሰተኛ ሥም የሚጽፉት (እዚህ ያሉትም ቢሆኑ) ሰልፍ አይወጡም፤ በእውነተኛ ሥም መጻፍ ሰልፍ ከመውጣት የበለጠ አያስፈራም። እነዚያ በሥማቸው የጻፉት ደግሞ ይታፈሳሉ። ስለዚህ፣ ሰልፉን የማስተባበሩ ሒደት፣ ቢያንስ እኔ እስከማውቀው ድረስ መሬት የወረደ አልነበረም። ስለዚህ ሰልፉን የሚወጣ ሰው መኖሩ ቀድሞም አጠራጣሪ ነበር።

፪) ለአዲስ አበቤ ባዳ የሆኑ አጀንዳዎች

ሌላው ጉዳይ ሕዝብ ጋር የደረሰ ቅስቀሳም ሆነ ሰልፍ የሚያስወጣ አጀንዳ አለመኖሩ ነው። የኦሮሚያ ጉዳይ፣ ጥያቄው ብዙ ቢሆንም መነሻው [አዲስ አበባን ያስፋፋል የተባለው] ማስተር ፕላን መሆኑ ራሱ አዲስ አበባን ይገፋል። ብዙኃኑ አዲስ አበቤ ገንዘብ ካገኘ ሱሉልታ ወይም ሰበታ ላይ መሬት ገዝቶ ቤት መሥራት ነው ምኞቱ። የአማራ ጥያቄም ቢሆን ለአዲስ አበቤ ሩቅ ነው። አዲስ አበቤ ከኦሮሚያም ሆነ ጎንደር ሕዝቦች በተለየ ቅይጥ (heterogeneous) ነው፤ በቋንቋና ባሕላዊ ዳራ እንዲሁም ሃይማኖት አንድ ዓይነት (homogeneous) ሕዝብ ባለመሆኑ የቡድን ጥያቄ ሊኖረው አይችልም። ስለዚህ የአዲስ አበባን ሕዝብ ሊያስተባብሩ የሚችሉት የግለሰብ መብት ጥያቄዎች ናቸው። የአዲስ አበቤን ብሶት በአጫጭር ቃላት አሽሞንሙኖ ማንቀሳቀስ የሚቻልበት ሥራ አልተሠራም። “አማራ እና ኦሮሞ ወገኖችህ ናቸው” የሚለውም በቂ አይደለም። የአዲስ አበባ ሕዝብ ብዙ ምሬቶች አሉበት፣ የብሔር ጭቆና ትርክት ግን አደባባይ አያስወጣውም። የራሱን ችግሮች ከነመፍትሔዎቹ ቁልጭ ባለ መልኩ (specifically) ይህ ነው የሚለው ይፈልጋል። በቡድን ጉዳይ፣ አዲስ አበቤ ቢቻል የብሔር ነገር ባይወራበት ይመርጣል። የኑሮ ውድነት እና በመስፋት ላይ ያለው የመደብ ልዩነት፣ የሰብኣዊ መብት ጥሰት እና የመንግሥት ተቋማት ብልሹ አሠራር ወይም ሙስና የበለጠ ያሳስቡታል። እነዚህ ላይ ብዙ አልተባለም።

፫) ሰልፉን አገር ውስጥ ያለ አካል አልጠራውም

ቅስቀሳውን በብዛት ሲያደርገው የነበረው ኢሳት ቴሌቪዥን ሲሆን፣ ኢሳት አገር ውስጥ ያለው ተዳራሽነት በጣም ውሱን ነው። እርግጥ ኢሳት የሰልፉ አስተባባሪ ሌላ እንደሆነ ቢናገርም፣ ያንን አካል (በሥም እንኳ) የሚያውቀው አልነበረም። ከዚያም በላይ፣ አዲስ አበባ ውስጥ ኢሳት በጠራው ሰልፍ ላይ የሚወጣ ወጣት አለ ብዬ አላምንም። ለዚህ አንዱና ቀላሉ ምክንያት ኢሳት የግንቦት ሰባት ልሳን ነው የሚለው ስጋት ነው። ሌላው፣ አዲስ አበቤ ሰልፍ እንዲወጣ እዚህ እንዳለ የሚያውቀው የሆነ ቡድን ሰልፉን መጥራት አለበት፤ ማለትም የሆነ የሚያውቀው ሰው ወይም ቡድን ሰልፉን አብሮት እንደሚወጣ እርግጠኛ መሆን አለበት። ስለዚህ የፈለገውን ያህል ምሬት እና ብሶት ቢኖርበትም የአዲስ አበባ ሰው ጥቂት ሆኖ ሰልፍ መውጣቱ በፖሊስ ቆመጥ ከመቀጥቀጥ በቀር የሚያተርፍለት ነገር ስላልነበር – አልወጣም። አደጋውን ለመጋፈጥ ደፍሮ እንዲወጣ ከተፈለገ አስቀድሞ የሚያውቀው፣ የሚያምነው አካል እንደሚወጣ እርግጠኛ መሆን ነበረበት ወይም ሊነገረው ይገባ ነበር። ይህ ግን አልሆነም፤ ሁሉም ሰው ‘ሌላ ሰው ይወጣ ይሆን?’ እያለ የማያውቀውን ሰው ይጠባበቅ ነበር።

እንግዲህ፣ በመንግሥት የማፈንና የማስፈራራት እርምጃ፣ እንዲሁም በተቃዋሚዎች የፍርሓትና የሽንፈት ታሪክ መብዛት መካከል ድንገት የተጠራው ሰልፍ በሰበቡ የታሰሩትን ልጆች ሕይወት አደጋ ላይ ከመጣል በቀር ያተረፈው ነገር የለም። ያልተሳኩ የሰልፍ ጥሪዎች በመጪዎቹ የሕዝብ ንቅናቄዎች ላይ የራሳቸውን የ‘አንችልም’ ተፅዕኖ ያሳርፋሉ። የተቃውሞ ሰልፍ በማንኛውም አደጋ መካከል ለመጥራት ከመወሰን በፊት፣ ‘ማንኛውንም አደጋ ተጋፍጦ ሰልፍ መውጣት ተገቢ ነው ወይ?’ ብሎ መጠየቅ ባይቻል እንኳ፣ ‘ማንኛውንም አደጋ ተጋፍጦ ሰልፍ ለመውጣት ፈቃደኛ የሆነ ሕዝብ አለ ወይ?’ ብሎ ማሰብ ያስፈልግ ነበር። ክሽፈቱ ብዙ ዋጋ ያስከፍላልና።

እንደመፍትሔ የምጠቁመው፣ መጀመሪያ ‘የአዲስ አበባ ሕዝብ ጥያቄዎች ምን፣ ምን ናቸው? የሚመለሱትስ እንዴት ነው?’ የሚለውን ማጥራት ነው። ቀጥሎ፣ ለነዚህ መልሶች መገኘት የሚሠራ/ሩ ቡድን/ቡድኖችን ማደራጀት ያስፈልጋል። በመጨረሻም፣ ለተግባራዊነቱ መንቀሳቀስ። ያኔ፣ ሸገር፣ በጉያዋ አፍና የያዘችውን ፍም አደባባይ ትበትነዋለች ብዬ አምናለሁ። ያለዚያ ግን፣ በስሜት የሚገኝ ድል የለም።

19 Comments on “ሸገር ለምን አታምፅም? BefeQadu Z. Hailu”

  1. የአዲስ አበባ ልጅ መሆን ቀላል አይደለም ምክንያቱም የአዲስ አበባ ልጅ ስትሆን አንተ ዘረኛ አይደለህም የአዲስ አበባ ልጅ ስትሆን ጥያቄህ የመልካም አስተዳደር አንጂ የዘር አይሆንም የአዲስ አበባ ልጅ ስትሆን ከምንም በላይ ካለፈው ስህተትህ ትማራለህ(አስገድለወህ የፈረጠጡት ደጋሚ አንዲመሩህ አትፈቅድም) የአዲስ አበባ ልጅ ስትሆን ከማንም ጋር በ ፍቅር መኖር ትችላለህ የ አዲስ አበባ ልጅ ስትሆን ከ ዘር በፊት ሰወነትን ታስቀድማለህ ከ ምንም እና ከማንም በላይ የአዲስ አበባ ልጅ ኢትዮጵያዊነቱን ያስቀድማል! ፈሪ አይደለህም ምክንያታዊ ነህ!! የ አዱ ገነት ልጅ መሆን ቀላል አይደለም…….

  2. የአድስ አበባ ልጅ ስለ ሀገርቱ ሁኔታ ጠንቅቆ ያውቃል ስለ መብቱም እንደዚያውስለዝህ ከኑግ ውስጥ የተገኘ ሰሊጥ አብረህ ተወገጥ ማለትን ጠንቅቆ ያውቃል

  3. Very disappointed not many showed up in the street so we have to work hard to increase the awareness of the people so that weyane will fall quickly. So let’s Arrange it for another time. By the way if we stop the momentum so weyane will say I win and will revenge for those people who had been in their black list. Please let’s continue our struggle to throw weyane for good

  4. ጦርነት በርቀት ለመቀስቀስ የሚተጉ የኢትዮጵያ ጠላቶች ወይም ተላላኪዎች እነ ኢሳት እና መሰሎቻቸው የሚጠሩት ብጥብጥ ላይ የአዲስ አበባ ወጣት እንደማይሳተፍና እንደማይቀበለው አስመስክሯል ማን ለህዝብ እንደቆመና ማን ከጠላት ጋር እንደወሰነ አስረግጦ ተረድቷል። ስለዚህ ነገሩ አብቅቷል አለቀ።
    እንኳን የአዲስ አበባ ወጣት የጎንደር ወጣትም ተገንዝቦ ወደ መደበኛ ኑሮው ገብቷል።
    አሁን ተላላኪ ሆይ የበላኸውን ብር አንገትህን ረግጠው እንደሚያስመልሱት ግብፆች እየተናገሩ ነው ከየት አባትክ አምጥተህ እንደምትከፍል እናያለን።።

  5. ለመሆኑ የት ሁነህ ነው ትግሉን እንበለው እንጂ ብጥብጡን የምታስቀጥለው???

  6. የአዲስ አበ ባ ህዝብ በጎንድር በባህር ዳር በኦሮሞ ውገኖቹ የመብት የዲሞክራሲ ጥያቄዎች የሱም ጥያቄዎች ናቸው!!
    የወያኔ አፈና ዋናው ምክንያቶች አንድ ነው
    ኢሳት አ አ በደንብ በ ብዙዎች። ይደመጣል ወይ?
    የ አ አ ህዝብ በሌሎች አካባ ቢ ያለውን ሁኔታ ያውቃል

  7. I don’t understand when you said the question of ethinc can’t a reason to Addis Ababa that means all ethinc have equal rights. We heard from your group that they faced many problems because of their ethinc.

  8. I heard that 30,000 people displayed in one area in a rainy season most of them they know each other what happened with them.

  9. Freedom require dedications .they know that when you see huge armed forces they make triple your fear and it helps them to covered their fear.

  10. የአድስ አበባን ህዘብ ጠፍሮ የያዘና በየቆርቆሮ ቤቱ ተከራይቶ እየኖረ ያለ ድብቅ ኃይል አለ፡፡
    ይህ ኃይል ፖሊስ ወይም አጋአዚ አይደለም
    ይህ ኃይል በሄድንበት ሁሉ እንደጥላ እየተከታተለ ሪፖርት የሚያቀርብ በተለያዮ ስራዎች ላይ (ስራ ከተባለ)እየሰራ ያለና በመሀበር ሳይቀር የተደራጀ ኃይል ነው
    ማንኛውም የአድስ አበባ ኗሪ ዛሬ አያወራም አይወያይም ለምን ቢባል በወያኔ በርካሸ የሚሸመቱ “ሎቲዎች” በተለያየ ቀለም ተዘጋጅተው ጆሮው ላይ ተንጠልጥለውበት ነው የሚውሉት ታክሲ ሰለፍ ላይ እነሱ አሉ፣ታሲ ውስጥ አሉ ካፌ ውስጥ አሰተናጋጆች ናቸው፣ድራፍት ቤት ወየተር ናቸው ድለላ ቦታ የሰው ልጆችን የሚቸበችቡ እነሱ ናቸው መሬት የሚደልሉ እነሱ ናቸው የሰራነውን ቤት ሳይቀር በነሱው ዋጋ የሚያከራዩልን እነሱ ናቸው ፡፡ እንደት እንወያይ ጎበዝ ፡፡ የወንድ አያቴ በአንድ ወቅት ሰለ አርበኞችገድል ሲነግሩኝ ባጋጣሚ በዛን ጊዜ አጠራር “ሴትኛ አዳሪዎች ” በአሁኑ ደግሞ የቱሪዝም መስዕቦች ይሏቸዋል አርበኞች በጠላት እንዳይጠቁ ይሰጡት የነበረ ሸፋን ትልቅ አስተዋጽኦ ነበረው አሁን ግን አነዚህ እህቶች አራሳቸው ገበያ የሚያገኙት በደላላ ሰለሆነ የታዘዙትን ይሰራሉ አንደውም ጥሩ ሎቲዎች ናቸው ፈረንጅ ፈረንጁ ሚደለለው ለነሱ ነው በዛውም በነጋታው ጫት እየተቃመ ሪፖርት ይዘገባል ሪፖርቱን የሚመዘግበው የትርፍ ግዜ ባል ተብዬ የወያኔ ካድሬ ነው እባካችሁ የአድስ አበባ ኑዋሪ ብዙ ጉድ ውሰጥ ነው ያለው፤፤የታክሲውን ሰልፍ ሲፈልጉ ያሰረዝሙታ ደስ ካላቸው ያሳጥሩታለ አስፈላጊ ከሆነ አትጭንም ብለው ታክሲውን ያባርሩታል ለምን ስንል ስራቸውን ይጀምራሉ ውድ የአድስ አበባ ወጣት ሆይ አንተ በሁኔታዎች እየተማረርክ ውጭውን አለም በመመኘት የውሃ እራት ሆነህ እየቀረህ ነው የጨርኮስና የጨው በረንዳ ወጣት ልጆች በውሃ ተበልተው የቀሩት ምሳሌ ይሁንህ አድስ አበባ ሃገርህ ናት ከባንዳ ምንደኞች አንተ ነጻ ካላወጠሃት እና እንደቀድሞው ሰርተህ የማትኖርበት ከሆነና በሎቲዎች ክትትል ስር ሆነህ አየቆዘምክ የምትኖር ከሆነ ተበልተሃል ሞተሃል የቀበና ፤የቡልቡላና፤የአቃቂ ወንዞችን ተጠቀም ከዚህ በታች በሰራቸው የተጠቀሱ የህብረተሰብ ክፍሎችን ጆሮህ ላይ ሲንጠለጠሉና ከአፍህ እየቀለቡ የሚያቀብሉትን ለይተህ ተጠንቀቀህ ተወልደህ ያደግክባትን አዲስ አበባ ነክምንደኞች ነጻ አውጣ እኛ አድስ አበቤዎች የብሄር ክፍፍል የለብንም ስናድግም በተለይ የበፊቶቹ ከየት መጣህ አንባልም ምክነያቱም ኦሪጅናችን ሳሪስ፤ፒያሳ፤ አቃቂ፤መገናኛ፤መርካቶ፤ለገሃር፤ካሰንችስ ፈረንሳይ ሽሮሜዳ አድሱ ገበያ፤ቄራ፤ጎተራ ወዘተረፈ ነውና እዚህ ላይ ቦሌና ሓያሁለትን ለባንዳዎች ሰለአስረከብን የኛ ሰፈር አልለውም ቅንብቢቶችም ከምስራቅ አጠቃላይ በታች አይዎርዱም የነ ስብሃት ነጋ ጎላጎል እነሱን አያስተናግድም ከዚህ በታች ካሉ የጆሮ ሎቲዎች የሃገሬ ልጅ አድስ አበቤው
    • ከታክሲ ወያላና አልፎ አልፎ ሹፌር
    • ከታክሲ ተራ አስከባሪዎች
    • የቤት ፤የመሬት፤የቤትሰራተኛ፤የተሸከርካሪ፤የሴትኛ አዳሪ ደላሎች
    • ከካፌ ቤት አስተናጋጆች
    • ከድራፍትቤት አስተናጋጆች
    • ከጭፈራ ቤት ጥበቃዎች
    • በየመስሪያቤትህ ከጥበቃ እና ጽዳት ቀጣሪና አስቀጣሪ የሚቀርቡ እና ዩኒፎርም ከሚለብሱ ሰራተኞች እዚህ ጋር ወያኔ በመርዝም ሊያሰገድልህ ይችላልና ውሃ የምትጠጣበትን እቃ ሳይቀር ቆልፈህ ውጣ
    • ከቡና ቤትና በምሽት በየመንገዱ ከሚቆሙ የቱሪስት መስእቦች
    አጅግ ብዙ ናቸው ባንዳው ወያኔ ምንደኞች የውስጥ ቅኝ ግዛት ላይ እንዳለህ ሳትዘነጋ በምናውቅበት መንገድ ወንዞቹን እየተጠቀምቅ ምሽግሀን ስራ አለአስፈላጊ መስዋዕትነት ከሚያስከፍሉህ የመንደር ውስጥ ግርግርና ጽብ ውስጥ አትግባ ከላይ በገለጽኳቸው ክፍሎች እጅ ትወድቃለህና የትላንትናውም ሰልፍ በእነዚህ ምንደኞች የጨናገፍ ዘንድ ገዥዎቻችን በሚገባ ጠጠቅመውባቸዋል አስተውለሀ ከሆነ ጆሮህ ላይ ነበር ተንጠልጥለው የዋሉት ያራዳ ልጅ ሆይ እነዚህ የህብረተሰብ ከፍሎች አድሰአበባን የሚያውቁዋት ቅርብ ጊዜ ሲሆን በተለያየ ስልጠና ተቆጣጥረውሃል ሰሞኑን የአድስ አበባ ልጅ የሆኑትን አባረዋቸዋል አላመኑዋቸውምና
    ለለውጥ እንነሳ

  11. አዲስ አበባ ለዘረኛ የትግራይ ወራሪዎች እና ለሆዳቸው ባደሩ የትግሬ ነፃ አውጪ ባሪያዎች ተሸጣ እና ተቸብችባ አልቃለች!!

    አዲስ አበባን የተቀራመቷት ትግሬዎችና ሆድ አደር የወያኔ ባሪያዎች በቢዝነስ ሥራ እና በህንፃ ግንባታ ሥራ ተወጥረው ነው ያሉት!!

    ለመብት ለነፃነት፣ ለዲሞክራሲ፣ ለሀገር ክብር እና የወደፊት እጣ ፋንታ ደንታ የሌለው ትውልድ የበዛባት የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ሆናለች !!

    ወጣቱ በአጠቃላይ ለጥቅም ብቻ የሚሯሯጥ፣ በጫት እና በተለያየ አደንዛዥ እፅ ነፍዟል!!

    የድሮዋን አዲስ አበባ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ምን ጊዜም እንዳናገኛት/እንዳናያት የትግራይ ነፃ አውጪ ቡድንና ሆድ አደር ባሪያዎቹ በደንብ ሥራቸውን ሠርተው ጨርሰዋል !!

    የድሮውን ወኔ ያለው አዲስ አበቤን በዶዘር እየፈነቀሉ በታትነውት ለማኝ፣ ስደተኛ፣ ወዘተ በማድረግ የተረፈውንም በተለያየ ሱስ አደንዝዘው ሽባ አድርገው አስቀምጠውታል!!

    ዛሬ አዲስ አበባ ማለት የትግሬዎች መናኸሪያ ዋና ከተማ ማለት ነች !!

    ዛሬ የኦሮሞ ልጆች፣ የአማራ ልጆች፣ የደቡቡ ልጆች የምሥራቁ፣ የምእራቡ፣ የሰሜኑ ወዘተ ልጆች ግንባራቸውንና ደረታቸውን ለአግአዚ ጥይት እየሰጡ ለእናት ሃገራቸው ለኢትዮጵያ በአሰቃቂ ሁኔታ ሲወድቁላት አዲስ አበቤዎች ግን ገና የአግአዚ ወታደር በአይናችን አየን ብለው ዙርባ ጫታቸው እና ሺሻቸው ላይ ተጋድመው ይውላሉ ያሳዝናል !!

    እባካችሁ አዲስ አበቦች ሆይ !!

    ከባርነት ነፃነት ይቅደም !!

    ከሆድ ነፃነት ይቅደም !!

    በተለያየ ጥቅም ራሳችሁን መሸጥ ማለት ነፃነታችሁን ወገናችሁን ለሚጨፈጭፈው ለትግራይ ነፃ አውጪ ቡድን መሸጥ ማለት ነው !!

    ባርነትን እንደ ሌሎቹ የኢትዮጵያ ጀግኖች ልጆች አጥብቃችሁ ተፀየፉት፣ ተዋጉት !!

    ካለመሥዋዕትነት ድል አይገኝም !!

    እናት ሃገራችን ኢትዮጵያ በእግዚአብሔር ሐይል እና በተባበሩት ጀግኖች ልጆቿ ድልን ትጎናፀፋለች !!

  12. A spying net work in Addis diffuse the tension They are organized & can do every evil for a misery profit. Look it is not Addis Ababa’s budget exceed the budget of Amara? This is not for for their spying agent, weyane in addis following just the system of mubarek of Egypt, requiring every despaired citizens as their spying agent organizing them in the name of ‘tiqaqin’ some other more reason may be found, this is the major. To be effective another strategy may be needed like 1. Giving warning for those spying agent by noticing their name & phone number with media & taking action, closing all rod to addis refusing of paying tax for the tyrant solder etc. May be remedy!

  13. I like your articles but some of your decision contradicts as you said ESAT can reached only for very few people then the probability of protest is 0 even if any legal or illegal party (movement) has called the protest. It’s not the question of ownership. My other question is how a people in prison can get the information before you have it ? Maybe you are busy because of your personal problems that makes you far from information. The responsibility of all Ethiopian for their freedom is equal.

  14. ሸገር ጥበት አያውቅም አቦ፣
    አማራና ኦሮሞ ተባብሮ ካላችሁ በኋላ፣ እንዴት ነው ሸገር የሁሉ መኖሪያ የሆነችውን አብራችሁን ተሰለፉ የሚል ጥሪ ያላስተላለፋችሁት?
    እኛ አማራና ኦሮሞ የሆንን የሸገር ልጆች፣ ዜማው ይቀየርልንማ፦
    ለምን ቢባል ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች ተነሱ ተብሎ ቢስተካከልልን፣ ነው የሚመቸን። ወያኔ የነጣጠለን እንዳይበቃ ደግሞ አዲሱ ታሳቢ መንግስቶች የዚህ ነጠላ ዜማ ይዛችሁ ከሆነ የምትመጡት፣ አንድ አፍታው የጠገበው ጅብ ሳይሻለን የሚቀር አይመስላችሁም?

    ዜማው ይቀየርልንማ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*