በኦባማ የዓመቱ ምርጥ መጻሕፍት ዝርዝር ውስጥ የተካተተው ዲናው መንግሥቱ ማነው?
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ የ2024 ምርጥ መጻሕፍት ዝርዝር ውስጥ ካካተቷቸው መጻሕፍት መካከል የዲናው መንግሥቱ ‘Someone Like Us’ ይገኝበታል። ኦባማ እአአ በ2019 የዲናውን ‘How to Read the Air’ የተባለ ልብ ወለድ የዓመቱ ምርጥ መጻሕፍት ዝርዝር ውስጥ አስገብተዋል። ኢትዮጵያዊ-አሜሪካዊው ዲናው ማነው?