“እንዳትረግጡት…. የኢትዮጵያን ዐፈር- መሬት! ”
‘ባካችሁ ……… ’ባካችሁ……….
እናንት በምድረ– ኢትዮጵያ ያላችሁ፤
“አትሂዱ …..በ‘ግራችሁ…”
ከቻላችሁ ….. “ብረሩ ክንፍ አው’ታችሁ።”
ግን…….. አደራ……….. ……….
አንዳትረገጡት ……. መሬቱን
እንዳታዩት……… አፈሩን፤
ብታርሱት…… አትዘሩበት
ብዘሩበት …….. አይበቅልበት፤……..
ደም ነውና – የትላንና– የዛሬ – የአሁን፣ ትኩስ…. የፈሰሰበት
አጥንት ነውና ያልደረቀ ፣ “አጸደ–ህይወት” የወደቀበት
እናንተም ከእንግዲህ ፣ ”ዐጽም – ‘ርስቴ” የማትሉት፤………..
ያውም ………………………………..
የባቶቻችሁ፣…….. የናቶቻችሁ
ያውም………………………………
የወንድሞቻችሁ፣…….. የህቶቻችሁ
ያውም……………………………………
የእቦቀቅላወቹ፣…… የታዳጊወቹ፣……..የልጆቻችሁ፤
ዓይናችሁ እያየ፣……. እየሰማ ጆሮ‘ችሁ
የተመቱ! … የቆሰሉ!….. የተወጉ! …. የተፈነከቱ!…..
የተቀጠቀጡ!…. የተዘለዘሉ!……! ……የተረሸኑ!
….. በገዛ ወገኖቻችሁ………..
ያውም …………”ወገን እኮ ነን “ እያላችሁ።
በደመዋ ልባችሁ……………………………….
“ኤሉሄ …..ላማ ሰበቅተኒ!”……. ብላችሁ
ወሰን – ድንበር ለሌለው ሰቆቃችሁ
ብትነግሩትም “ለሰማይ አባታችሁ”፤
ግን….. ለምንም – ለማንም አይመችም
ሀዘናችሁ መልክ የለውም……….
ያልተነገረ እንጅ፣ ያልተፈጸመባችሁ ግፍ የለም።
ብትጎጉጡ፣ ደም አልቅሳችሁ፣….. እየየ …ብላችሁ –
ቢያዳርስም ዓለም ….. ሲቃ – ዋይታችሁ …
መቼም– መቼም ቢሆን፣ ምንጩ አይደርቅም የ‘ምባችሁ::…..
እናማ………………………………………..
ሰላም፣ ፍትህ፣ እኩልነት – ሳታሰፍኑ – በመሀከላችሁ
አንድነትን ሳታነግሱ – በምድራችሁ
ይቅር ሳትባባሉ፣ ‘ርስ – በርሳችሁ
ሳይመለስ ክብራችሁ፣ ጠፈር – ድንበራችሁ
የድል ችቦው – ከፍ ሳይል ፣ ክብር ሰንደቅ ዓላማችሁ፤……
የወገናችሁን ደምና– አጥንት እንዳትረግጡት
“ይወጋችሁልና እሾኽ ሆኖ፣ የኢትዮጵያ ዐፈር – መሬት!”።
———//———
ፊልጶስ/ ነሀሴ 2008
E-mail: [email protected]