ይኼ ሰውዬ ኦሊምፒክ የላክነው ለአገር ገጽታ ግንባታ ነው፡፡ቦርጩ የአገሪቷን ልማት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡ ክቡር ሚኒስትሩ
[የክቡር ሚኒስትሩ ሾፌር ፌስቡክ እያያ ይስቃል]
- አንተ ሰውዬ አበድክ እንዴ?
- ምነው ክቡር ሚኒስትር?
- ብቻህን ምን ያስገለፍጥሃል?
- ፌስቡክ እያየሁ ነው፡፡
- እንዴ መቼ ተለቀቀ?
- ደግሞ ማንን አስራችሁ ነበር?
- ፌስቡክን ማን ለቀቀው?
- ለነገሩ ፌስቡክ ራሱ ታስሮ ነበር ለካ፡፡
- እኮ ማን ለቀቀው?
- ትንሽ ቆየ እኮ ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ምኑ ነው የቆየው?
- ፌስቡክ ከተለቀቀ፡፡
- ማነው ልቀቁ ያላቸው?
- በነካ እጃችሁ ግን ሌሎቹንም ብትለቁ መልካም ነው፡፡
- እነማንን?
- በየጊዜው የምታጉሯቸውን ነዋ፡፡
- ምን አልክ?
- ግን ፌስቡክ ራሱ እንደ መብራትና ውኃ ልታደርጉት ነው ማለት ነው?
- እንዴት ማለት?
- በፈረቃ ነዋ፡፡
- በፈረቃ ሳይሆን በጨረቃ ነው፡፡
- እንዴት በጨረቃ?
- ማታ ማታ ብቻ ነዋ የሚለቀቀው፡፡
- እሷንም አታሳጣን ብንል ይሻላል፡፡
- ለመሆኑ ምንድን ነው የሚያስቅህ?
- እንኩ ይመልከቱት ክቡር ሚኒስትር፡፡
- የማነው ቦርጫም በእናትህ?
- አዩት ዓሳ ነባሪውን?
- የምን ዓሳ ነባሪ ነው?
- ቅፅል ስሙ ነው፡፡
- ይኼ ነው ያስገለፈጠህ?
- እህሳ ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ይኼ ያስለቅሳል እንጂ ምኑ ያስቃል?
- ኢትዮጵያን ወክሎ ተወዳድሮ ነው እኮ፡፡
- በምን?
- በዋና፡፡
- በዚህ ቦርጭ?
- አይገርምዎትም ክቡር ሚኒስትር፡፡
- እና እንዴት ሆነ?
- አዋረደን ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ግን ሲታይ ልማታዊ ይመስላል፡፡
- እንዴት ማለት?
- ቦርጩ የአገሪቷን ልማት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡
- ምን አሉኝ?
- አታየውም እንዴ ቦርጩ ላይ የ11 በመቶ ዕድገቱን?
- ይኼ የሚያሳየውማ ዕድገቱን ሳይሆን ውድቀቱን ነው፡፡
- ስማ ሁሌ የመፍትሔ ሰው ነው መሆን ያለብህ፡፡
- ምን ማለት ነው?
- ይኼ ሰውዬ ኦሊምፒክ የላክነው ሆን ብለን ነው፡፡
- ለምን ተላከ?
- ለአገር ገጽታ ግንባታ፡፡
- ይኼ ገጽታችንን ያፈርሰዋል እንጂ እንዴት ይገነባዋል?
- ኢትዮጵያ ዓለም ላይ የምትታወቀው በረሃብና በድርቅ ነው፡፡
- እሱማ ልክ ነው፡፡
- እና ፈረንጆቹ በልተን ጠግበን የምናድር አይመስላቸውማ፡፡
- አሁንም እኮ በልተው የጠገቡት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
- ፖለቲካህን እዛው፡፡
- እውነቴን ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ለማንኛውም እንደዚህ ዓይነት ቦርጫም ኢትዮጵያዊ ሲያዩ ፈረንጆቹ አመለካከታቸው ይቀየራል፡፡
- እንዴት ይቀየራል?
- ጠግበን እንደምናድር ያውቃሉ፡፡
- ኧረ ክቡር ሚኒስትር ኦሎምፒኩን የተሳተፈው እኮ አባቱ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ስለሆኑ ነው ይባላል?
- ታዲያ ቢሆኑ ምን አለበት?
- እ . . .
- አሁን የእኔ ዘመዶች ሁሉም የመንግሥት ባለሥልጣናት ናቸው፡፡
- እሱስ ልክ ነው፡፡
- ከባለሥልጣኖቹ ውጪ ነጋዴዎች ናቸው፡፡
- ለነገሩ አገሪቷ በእጃችሁ ናት፡፡
- ከእጃችን ልትወጣ አትችልም፡፡
- ክቡር ሚኒስትር ግን እንደዚህ እስከ መቼ ይቀጥላል?
- ምን ማለት ነው?
- በየቀበሌው ራሱ ሲኬድ ሁሉም በወንዝ ነው የተደራጀው፡፡
- ኧረ አንተስ ወንዝ ይዞህ ይሂድ፡፡
- ምን አደረኩ ክቡር ሚኒስትር?
- ወሬ ታበዛለህ፡፡
- አገራችን ተዋረደች እያልኩዎት እኮ ነው፡፡
- ገጽታ ግንባታ ነው አልኩህ?
- ታዲያ ሰውዬው ዋናተኛ መባል የለበትማ፡፡
- ምን ይባል ታዲያ?
- በላተኛ!
[ለክቡር ሚኒስትሩ ከውጭ ስልክ ተደወለላቸው]
- ምን እያደረጋችሁ ነው ክቡር ሚኒስትር?
- እያደግን ነዋ፡፡
- ኧረ ይኼ ያሳፍራል፡፡
- ምኑ ነው የሚያሳፍረው?
- እየሠራችሁት ያለው ነገር፡፡
- አገራችንን ማሳደጋችን ነው የሚያሳፍረው?
- እንደዚህ እየቀለዳችሁ ግን እስከ መቼ ነው የምትቀጥሉት?
- ገና እየጀመርን አይደል እንዴ?
- ቀልዱን ነው?
- ምን ይላል ይኼ?
- ክቡር ሚኒስትር ይህቺ የተከበረች አገር እያዋረዳችኋት ነው?
- እያከበራችኋት ነው ማለትህ ነው?
- ይኸው አንገታችንን አቀርቅረን እንድንሄድ አደረጋችሁን፡፡
- ስማ አቀርቅረህ መሄድህ እኮ ጥሩ ነው፡፡
- ምን እያሉ ነው?
- እንቅፋት እንዳይመታህ ነዋ፡፡
- ኧረ ይኼ ማላገጥ ይቅር ክቡር ሚኒስትር?
- የምን ማላገጥ ነው?
- ኦሊምፒክ የላካችሁት ሰውዬ ምንድን ነው?
- የቱ ሰውዬ?
- ዓሳ ነባሪው ነዋ፡፡
- ሆን ብለን ነው የላክነው፡፡
- ምን?
- ለአገር ገጽታ ግንባታ ነው፡፡
- ይኼ የአገር ገጽታን ያበላሻል እንጂ ምን ይገነባል?
- አየህ ፈረንጆች የሚያውቁን በድርቅና በረሃብ ነው፡፡
- አሁንስ ቢሆን ከእሱ መቼ ተላቀቅን?
- ስለዚህ እንደዚህ ዓይነት ቦርጫም ዋናተኛ ትልክና አገሪቱ ውስጥ ጥጋብ መኖሩን ታሳያለህ፡፡
- ግን እንደዚህ እየቀለዳችሁ የምትዘልቁ ይመስላችኋል?
- ምን እያልክ ነው?
- በዚህ ጉዳይ በዓለም ደረጃ አገራችን ነው የተዋረደችው፡፡
- ለምንድን ነው የተዋረደችው?
- ለነገሩ እናንተ ራሳችሁ አዋራጆች ናችሁ፡፡
- ምን አድርገን?
- ስንት ዓለም አቀፍ ውሎችና ውሳኔዎችን በሚገባ ማንበብና መረዳት አቅቷችሁ፣ አዋርዳችሁን የለ እንዴ?
- ምን ትዘባርቃለህ?
- እናንተ ፖለቲከኞቻችን ከዋናተኛው አትሻሉም፡፡
- ምን እያልክ ነው?
- እናንተም ከሌሎች የምዕራባውያን አገሮች ሚኒስትሮች ጋር ብትወዳደሩ እንደምታዋርዱ እርግጥ ነው፡፡
- ሰውዬ አደብህን ግዛ፡፡
- ለነገሩ እንደነገርኩዎ ከዚህ በፊትም አዋርዳችሁን ታውቃላችሁ፡፡
- ምን ይላል ይኼ?
- አሁን ዋናተኛው ምን እየተባለ እንደሆነ ያውቃሉ አይደል?
- ምን ተባለ?
- ሮቤል ዘ ዌል፡፡
- እ . . .
- እኔ ደግሞ ለእርስዎ ስም አውጥቼልዎታለሁ፡፡
- ምን ልትለኝ?
- ሚኒስትሩ ዘ ዌል!
[ክቡር ሚኒስትሩ ከአማካሪያቸው ጋር እያወሩ ነው]
- የተናደዱ ይመስላሉ ክቡር ሚኒስትር፡፡
- አንዱ እኮ ሰድቦኝ ነው፡፡
- ለምንድን ነው የሰደበዎት?
- በዚህ በዋናተኛው የተነሳ ነዋ፡፡
- ታዲያ እርስዎ ምን አደረጉ?
- ፖለቲከኞቻችንም ያው ናችሁ ብሎ ነዋ፡፡
- ምን ብሎ ሰደበዎት?
- ሚኒስትሩ ዘ ዌል፡፡
- ኪኪኪ . . .
- ምን ያስገለፍጥሃል?
- ስድቡ አስቆኝ ነው፡፡
- ወይኔ፡፡
- ወያኔ ነው ያሉኝ?
- ምን ትቀባጥራለህ?
- ግን ተዋረድን እኮ፡፡
- በምንድን ነው የተዋረድነው?
- በኦሊምፒክ ነዋ፡፡
- እንዴት ሆኖ?
- ይኸው በወንዶች አሥር ሺሕ ሜትር አሸነፈን እኮ፡፡
- ማን ነው ያሸነፈን፡፡
- ሞ ፋራህ ነዋ፡፡
- ኃይሌ የት ሄዶ?
- ክቡር ሚኒስትር እርሱ ውድድር ካቆመ ቆየ እኮ፡፡
- ቀነኒሳስ?
- እሱም የመመረጫ ውድድሩ ላይ አቋርጦ ወጣ፡፡
- ታዲያ ማን ነበር የተሳተፈው?
- አይ ክቡር ሚኒስትር በደንብ አላቃቸውም፡፡
- እና ምንድን ነው ችግራቸው?
- ያው በወንዶች እንደ ድሮ ማሸነፍ ተስኖናል፡፡
- ለምንድን ነው ማሸነፍ የተሳነን?
- እኔን’ጃ ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ለመሆኑ ሯጮቻችን ልማታዊ ናቸው?
- አዎን ክቡር ሚኒስትር፡፡
- በምን አወቅህ?
- ሁሉም እኮ ሕንፃ እየገነቡ ነው፡፡
- አየህ ውስጣቸው ግን ልማታዊ ላይሆን ይችላል፡፡
- ምን እያሉ ነው?
- ለመሆኑ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ተጠምቀዋል?
- እነሱ እኮ ፖለቲከኞች ሳይሆኑ ሯጮች ናቸው፡፡
- አየህ ችግሩ ይኼ ነው፡፡
- የምኑ ችግር?
- የማያሸንፉት ለዛ ነው፡፡
- እንዴት ሆኖ?
- አብዮታዊ ዴሞክራሲ ማለት ሌላ ትርጉሙ አሸናፊ ማለት ነው፡፡
- በለው፡፡
- እኛ በፓርላማ መቶ ፐርሰንት ያሸነፍነው ለዛ ነው፡፡
- ይኼ እኮ ታይቶ የማይታወቅ ነው፡፡
- አየህ አትሌቶቻችንም ታይቶ የማይታወቅ ድል እንዲያገኙ መጠመቅ አለባቸው፡፡
- በምን?
- በአብዮታዊ ዴሞክራሲ!
[ክቡር ሚኒስትሩን የውጭ ጋዜጠኛ ኢንተርቪው ሊያደርጋቸው ቢሯቸው ገባ]
- ይህንን ቃለ መጠየቅ ለማድረግ ስለተስማሙ አመሰግናለሁ፡፡
- እኛ የምንደብቀው ነገር ስለሌለ ችግር የለውም፡፡
- ጥያቄዬን መጀመር እችላለሁ?
- ቀጥል፡፡
- በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ሕዝቡ ድምፁን እያሰማ ነው፡፡
- እንግዲህ አገራችን እያስመዘገበችው ባለው ዕድገት ሕዝቡ ደስተኛ ስለሆነ በየቦታው የደስታ ድምፅ ሊሰማ ይችላል፡፡
- አልገባዎትም ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ምኑ ነው ያልገባኝ?
- ሕዝቡ በተለያዩ አካባቢዎች የተቃውሞ ድምፅ እያሰማ ነው?
- እንዳልኩህ አገሪቱ 11 በመቶ እያደገች ስለሆነ ሕዝብ የእልልታ ድምፅ በየቦታው ያሰማል፡፡
- ክቡር ሚኒስትር እኔ ሕዝብ ስለሚያሰማው ተቃውሞ ነው የምጠይቀዎት?
- በመስኮት እንደምትመለከተው ይኼ ሁሉ የሕንፃ ጫካ የልማቱ መገለጫ ነው፡፡
- ክቡር ሚኒስትር የተግባባን አይመስለኝም፡፡
- እንዴት እንግባባለን?
- የጠየኩዎትን ጥያቄ ለምን አይመልሱልኝም?
- መለስኩልህ እኮ፡፡
- ምን ብለው?
- እያደግን ነው፡፡
- አሁን የሕዝብ ችግር እየገባኝ ነው፡፡
- ምንድን ነው?
- የሚያዳምጠው የለም!
በፍጹም በወያኔ ጊዜ የሚጻፉ ቀልዶች አስቀውኝ አያውቁም። በምንም ታአምር።
አይ ክቡር ሚንስትር!?እንደ እርስዎ ያሉ ስልጣኑን ይዘውት ዕድገት በቁጥር ጭማሬ የሚሆን መስሎዋቸው እኮ ተቸገርን።
well done kebur minster!!
Entertaining as well as informative.
እነዚህ ጡት ነካሾች የተሰባሰቡት ኢትዮጵያን አደክመው፣አዋርደው፣ሃገሪቱን ድንበር አልባ አድረገው፣ ለማጥፋት የተሰጣቸው የቤት ስራ አድርገው ጡት የጣሉት ኢትዮጵያን በመጥላት ላይ የተመሰረቱ ናቸው!
በአሁኑ ጊዜ በሃገሪቱ ውስጥ ከፍተኛውን የሥለላ እና የግድያ ስራ የሚሰሩት እነዚህ የመንደር ስብስቦች የበላነታቸውን አረጋግጠው ሌላውን ባሪያና ሰውን እንደሸቀጥ ለመሽጥ ሃብት ለማካበት ዋና አላማቸው ስለሆነ ነው፡፡
ሳሚ
የእኛ ጀግና ወንዳታ ተመስገን እናት አንትን ወልዳለች! በእውነት ኮራሁብህ ወንድምህ ከእስር ስትፈታ አይን ፊትለፊት እንገናኛለን አክባሪ ወንድምህ ነኝ!
ወያኔ ምን ነው አንድነት ፈራ? ሕብረትን ፈራ ወያኔ? ወንድም ወንድሙ ገድሎ ሃውልት ከበሮ ጭፈራ እስከ መቼ? ሃገርን አስገንጥሎ የጎንደርን መሬት ለትግራይ ሕዝብ ከሳ ነው አማራ ከጎንደር ለቅህ ውጣ ያሉ ፍጡራን
ሳሚ
ይህ ዘወትር የምናነሳው ጉዳይ ነው የዘረኛው የወያኔ መንግስት የደህንነት አባላት አደገኛ ቦዘኔና ሌባ እንደሆኑና ከትግራይ ትምህርት አልገባ ያላቸው የስርአቱ አልበኛ አባላት ልጆች ናቸው ይህን ጉዳይ ለማስታወስ በአንዋር መስኪድ ከፈነዳውና ፒያሳ ባንክ አጥር ስር የወያኔ አባላት የጣሉትን የመጨረሻው ፈንጂን እናስታውሳለን ሆኖም ህዝቡ ይህን በጥንቅልቄ እየተገነዘበው ያለ ጉዳይ ነው አይረሳም ሆንም አሁን ዝግጅቱን አጠናቆ የሰላም ባስን ከጥቃት አሽሾ በደሀ ንብረት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ አድርሶ የጥፈት ተላላኪ ታርጋ ለመለጠፍ የትምክህተኛ እና ጠባብ ህዝብ የተባሉትን የአማራና የኦሮሞን ህዝቦች ዳግም በእስር ለመቅጣት ተዘጋጅቷል ሁላችንም የህወሀት ጠላቶች ነን ኢትዬጵያውያን አናንቀላፋ የማይተኛ ትል ከሆነብን ስርአት ለመላቀቅ መንገዳችንን ይዘናልና ወደሃላ አንመልከት መጭው ግዜ ኢትዬጵያን ዳግም ወደ ጥንት ማንነቷ የምንመልሳት ግዜ ላይ ነን በብሄር በጎሳ እንዳናስብ ከተፈለገ ወያኔን ከስሩ መንቀል ነው የበሠበሰ ስርአት ይወድቃል ይህን እንመን ድል ለኢትዬጵያ ህዝብ።
ሞት ለወያኔ!!!
የትግሉ ባለቤት የትግራይ ዘረኛ ቡድን ሳይሆን የኢት.ህዝብ ነው።
የሌባው መለስ ዜናዊ ሬሳ ከፊንፊኔ ይነሳል እመኑኝ።
———————————***——————————
tgrea they sold ethiopia for the cheapest buyer and the are enjoythem selfes