ሰሜን ጎንደር በተለያዩ አከባቢዎች በህዝቡና በወያኔ ወታደሮች መሀል ውጊያ እየተካሄደ ነው ከሙሴ ባምብና ከሳንጃ ሰራዊቱ ለቆ ሄዷል
ሶሮቃ ከፍተኛ ውጊያ እየተካሄደ ነው። አይምባ ላይም እንዲሁ በጣም ከባድ ውጊያ። በሶሮቃ ውጊያው ሕወሃት ታንክ ጭምር እየተጠቀመ ነው። የአገሬ ሰው ተወልዶ ያደገበትን መሬት በሚገባ እየተጠቀመበት ነው። የጦርነት ቦታወችን በማብዛት ህወሃትን እያስጨነቀው ነው። እየተደረጉ ባሉ ዉጊያዎች ታንክን ጨምሮ በርከት ያሉ የጦር መሳሪያ የጫኑ የጦር ተሽከርካሪወች ተማርከዋል። በዳንሻ የገበሬ ጦርና ወታደሮች ተፋጠዋል። ብዛት ያለው የገበሬ ጦር ከእያካባቢው እየተሰባሰበ ነው። ወልቃይት ጠገዴን ጨምሮ በሰሜን ጎንደር ነገሮች ከቁትጥር ዉጭ ሆነዋል ለሕወሃቶች።
