ጎንደር በሕዝብ ማዕበል ተጥለቅልቃለች!ፎቶዎችን ይመልከቱ
ምንም እንኳ ራዲዮ ፋናና የሕወሃት ካድሬዎች የሕዝቡን ሕገ መንግስታዊ መብት ለማፈን ቢሯሯጡ ሕዝቡ ግን መብቱን ከማስከበር ወደ ኋላ አላለን። የፍርሃት ቀንበርን ሰባብሮ ጥሎ ከአራቱም ማእዘናት ወደ አደባባይ በመምጣት ፍጹም ጨዋነት በተላበሰ ሁኔታ ድምጹን እያሰማ ነው። ሕወሃቶች ይህን ህዝብ የሻእቢያ አሸከር እያሉ ሲሳደቡባ ሲያጥላሉት እንደነበረ ይታወቃል። አስር ጊዜ “ሕግ፣ ስርዓት..” እያሉ ለሕግና ለሰላም የቆሞ ለመምሰል የሞከሩበት ሁኔታ አለ። ሕዝቡ ግን ሕግ አክባሪ ሰላማዊ መሆኑን በይፋ እያስመሰከረ ነው።እስከ አሁን ባለው የሰልፍ ሂደት ፍጹም ስነ ስርዓት የነበረው ሲሆን፣ ምንም አይነት ችግር አልተፈጠረም።
ሰልፈኞቹ በሚያስደንቅ ሁኔታ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ከፍ አድርጎ በማውለብለብ የአንድነትን ደቁል ደዉለዋል።





